የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፩


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፩፥፲፫–፲፭።ማቴዎስ ፲፩፥፲–፲፩፣ ፲፫–፲፬ ጋር አነጻፅሩ

መጥምቁ ዮሐንስ ለአዳኝ መንገድን ለማዘጋጀት የሚመጣው ኢልያ ነው።

፲፫ ነገር ግን ረባሾች ሀይል የማይኖራቸው ቀናት ይመጣሉ፤ ነቢያት ሁሉና ሕጉ እንደተነበዩት እስከ ዮሐንስ ድረስ እንዲህ ይሆናል።

፲፬ አዎን፣ የተነበዩት ሁሉ ስለእነዚህ ቀናት አስቀድመው ተናግረዋል።

፲፭ ይህን ከተቀበላችሁ፣ በእውነትም፣ ሁሉንም ነገሮች የሚያዘጋጅ እና ሁል ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነበር።