የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፬–፮።ማቴዎስ ፪፥፬–፮ ጋር አነጻፅሩ

ነቢያት ቤተ ልሔም መሲህ የሚወለድበት ቦታ እንደሆነ አቅድመው ተናገሩ።

የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ በማለት ጠየቃቸው፥ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ በነቢያት የተጻፈበት ቦታ የት ነው? ምክንያቱም ታላቅ ፍርሀት ነበረው፣ ግን በነቢያት አያምንም ነበር።

እነርሱም በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና፣ በይሁዳ ቤተ ልሔም ይወለዳል፣ እንደዚህ ብለዋልና አሉት፣

የጌታ ቃል ወደ እኛ እንዲህ በማለት መጣ፣ እናም አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ በአንቺ ውስጥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ ታናሽ ያልሆነ መስፍን ይወለዳል፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚያድን መስፍን ከአንቺ ይወጣልና።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፳፬–፳፮።ማቴዎስ ፪፥፳፫ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ አደገ እናም አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ጌታን ጠበቀ።

፳፬ እና እንዲህ ሆነ ኢየሱስ ከወንድሞቹ ጋር አደገ፣ እና ጠነከረ፣ እና የአገልግሎቱ ጊዜ እስከሚመጣም ጌታን ጠበቀ።

፳፭ እና ከአባቱ በታች አገለገለ፣ እና እንደ ሌሎች ሰዎች አልተናገረም፣ ወይም ሊማርም አልቻለም፤ ምንም ሰው እንዲያስተምረው አላስፈለገውምና።

፳፮ እና ከብዙ አመቶች በኋላ፣ የአገልግሎቱ ሰዓት ቀረበ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፴፬–፴፮።ማቴዎስ ፫፥፰–፱ ጋር አነጻፅሩ

የመጥምቁ ዮሐንስ መልእክትን የማይቀበሉ ክርስቶስን አይቀበሉም። እግዚአብሔር ከእስራኤል ያልሆኑን የቃል ኪዳን ህዝቦች ለማድረግ ይችላል።

፴፬ እግዚአብሔር ራሱ የላከውን ስብከት ለምንድን ነው የማትቀበሉት? ይህብ በልባችሁ ካልተቀበላችሁ፣ እኔን አትቀበሉም፤ እናም እኔን ካልተቀበላችሁ፣ እኔ እንድመሰክርበት የተላኩትን አትቀበሉም፤ እናም ለኃጢያቶቻችሁ ምንም መሸፈኛ የላችሁም።

፴፭ እንግዲህ፣ ንስሀ ግቡ፣ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤

፴፮ በልባችሁም የአብርሐም ልጆች ነን እና ወደ አባታችን አብርሐም ፍሬ እናምጣ በማለት አታስቡ፤ እላችኋለሁና፣ ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፴፰–፵።ማቴዎስ ፫፥፲፩–፲፪ ጋር አነጻፅሩ

መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ለመጥመቅ ሀይል እንዳለው መስክሯል።

፴፰ እኔስ ንስሐ ከገባችሁ በኋላ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ እናም ስለእርሱ ምስክር የምሰጠው፣ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ፣ (ወይም ቦታውን ለሞምላት የማልችለው) ሲመጣ፣ እንዳልኩት፣ እርሱ ከመምጣቱ በፊት አጠምቃችኋለሁ፣ እርሱ ሲመጣም በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል።

፴፱ እና የምመሰክርበት፣ መንሹም በእጁ የሆነው እርሱ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት በጊዜው ሙላት ያቃጥለዋል።

በዚህም ዮሐንስ በዮርዳኖች ወንዝ በመስበክ እና በመጥመቅ መጣ፤ ከእርሱም በኋላ የሚመጣው መንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ለመጥመቅ ሀይል እንዳለው እየመሰከረም።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፫፥፵፫–፵፮።ማቴዎስ ፫፥፲፭–፲፯ ጋር አነጻፅሩ

ዮሐንስ ኢየሱስን በማጥለቅ አጠመቀ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ ሲወርድ አየ፣ እናም የአብን ድምፅ ሰማ።

፵፫ እና ኢየሱስም መልሶ፣ በአንተ እንድጠመቅ ፍቀድልኝ፣ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።

፵፬ እና ዮሐንስ ወደ ውሀው ገባ እና አጠመቀው።

፵፭ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ ዮሐንስም አየ፣ እና አስተዋለ፣ ሰማያት ተከፍተውለት ነበር፣ እና የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በኢየሱስ ላይም ሲመጣ አየ፤

፵፮ አስተዋለም፣ ከሰማይም ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማ፣ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው። አድምጠው።