ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፩፥፴፫። ከማቴዎስ ፳፩፥፴፪–፴፫ ጋር አነጻፅሩ
ሰው በኢየሱስ ከማመኑ በፊት ንስሀ መግባት አለበት።
፴፫ ዮሐንስ እኔን በሚመለከት ያለውን የማያምን ንስሀ ካልገባ በስተቀር አያምነኝም።
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፩፥፵፯–፶፮። ከማቴዎስ ፳፩፥፵፭–፵፮ ጋር አነጻፅሩ
ኢየሱስ ዋና የማዕዘኑም ድንጋይ እንደሆነ ገለጸ። ወንጌሉ ለአይሁድ ይቀርባል፣ ከዚያም ለአህዛብ። ክፉዎች ኢየሱስ ሲመለስ ይደመሰሳሉ።
፵፯ እና ካህናት እና ፈሪሳዊያን የእርሱን ምሳሌዎች ሲሰሙ፣ ስለእነርሱ እንደተናገረ ገባቸው።
፵፰ እና እንዲህ ተባባሉ፣ ይህን ታላቅ መንግስት እርሱ ብቻውን አበላሻለሁ ብሎ ያስባል? እና በእርሱም ተናደው ነበር።
፵፱ ነገር ግን ሊይዙትም ሲፈልጉት ሳሉ ሕዝቡ ፈሩአቸው፣ ምክንያቱም ህዝቡ እንደ ነቢይ እንደሚያዩት ስላወቁ።
፶ አሁንም ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ፣ እና ኢየሱስ አላቸው፣ ለእነርሱ በተናገርኩት የምሳሌ ቃሎቼ ተደንቃችኋል?
፶፩ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔ አለት ነኝ፣ እና ክፉዎቹ ተቃወሙኝ።
፶፪ የማዕዘን ራስ ነኝ። እነዚህ አይሁዶች ይወድቁብኛል፣ እና ይሰበራሉ።
፶፫ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእነርሱ ትወሰዳለች፣ ፍሬዋንም ለሚያመጣ ሕዝብ ትሰጣለች፤ (ይህም ማለት አህዛቦች)።
፶፬ ስለዚህ፣ ድንጋዩ የሚወድቅበት ይፈጨዋል።
፶፭ እና የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ፣ እነርሱ የማይረቡ ክፉ ሰዎችን ያጠፋቸዋል፣ እና የወይኑንም አትክልት ስፍራውን፣ እንዲሁም በመጨረሻው ቀናት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል።
፶፮ ከእዚያም ጌታ ከሰማይ ምድር ወደሆነው ወደ ወይን አትክልቱ እና በእርሷ ውስጥ ወደሚኖሩት ሲወርድ፣ አህዛቦችም ደግመው እንደሚጠፉ የነገራቸው ምሳሌ ገባቸው።