ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፯፥፫–፮። ከማቴዎስ ፳፯፥፫–፭፤ ከሐዋርያት ስራ ፩፥፲፰ ጋር አነጻፅሩ
የይሁዳ ሞት ተገልጿል።
፫ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፣ እና ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፣
፬ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ።
፭ እነርሱ ግን ለእርሱ እንዲህ አሉት፣ እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤ ኃጢያትህም በራስህ ላይ ይሁን።
፮ እና ብሩንም በቤተ መቅደስ ጣለ፣ እና ሄደና እራሱን በዛፍ ላይ አነቀ። ወዲያውም ወደቀ፣ እና ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፣ ሞተም።