የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፱


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፱፥፲፰–፳፩።ማቴዎስ ፱፥፲፮–፲፯ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ የፈሪሳውያንን ጥምቀት አስወገደ፤ ይህም ምንም ዋጋ የለውም ምክንያቱም እነርሱ እርሱን አይቀበሉትምና። እርሱ የሙሴ ህግን የሰጠ እንደሆነ አወጀ።

፲፰ ከእዚያም ፈሪሳዊያን አሉት፣ ህጉን በሙላት እንደምንጠብቅ እያየህ፣ በጥምቀታችን ለምን አትቀበለንም?

፲፱ ነገር ግን ኢየሱስ አላቸው፣ ህግን አትጠብቁም። ህግን የምትጠብቁ ከሆናችሁ፣ ትቀበሉኝ ነበር፣ እኔ ህግን የሰጠሁት ነኝና።

በጥምቀታችሁ አልቀበላችሁም፣ ምክንያቱም ምንም አይጠቅማችሁምና።

፳፩ አዲስ የሆነው ሲመጣ፣ የድሮው ለመውጣት የተዘጋጀ ነውና።