የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፯


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፯፥፩–፪።ማቴዎስ ፯፥፩–፪ ጋር አነጻፅሩ

ፃድቅ ባለመሆን አትፍረዱ።

አሁን እነዚህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ለህዝቦቹ እንዲሏቸው ያስተማራቸው ቃላቶች ናቸው።

እንዳይፈረድባችሁ ፃድቅ ባለመሆን አትፍረዱ፤ ጻድቅ በሆነ ፍርድ ፍረዱ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፯፥፬–፰።ማቴዎስ ፯፥፫–፭ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቶቹን ከጸሀፊዎች እና ፈሪሳውያንን፣ ካህናትን፣ እና ሌዋውያንን በግብዝነታቸው ምክንያት እንዲጋጠሟቸው አስተማራቸው።

እናም እንደገና፣ እንዲህ ትሏቸዋላችሁ፣ በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?

ወይም ወንድምህን፣ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ፤ እና በዓይንህ ምሰሶ እንዳለ አታይምን?

እናም ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አለ፣ ጸሀፊዎችን እና ፈሪሳውያንን፣ ካህናትን፣ እና ሌዋውያንን ትመልክታችኋልን? በምኩራባቸው ያስተምራሉ፣ ነገር ግን ህግን፣ ትእዛዛትን አይጠብቁም፤ እናም ሁሉም ከመንገዱ ወጥተዋል እናም በኃጢያት ስር ናቸው።

ሂዱ እናም እንዲህ በሏቸው፣ እናንተ ራሳችሁ የብክለት ልጅች ሆናችሁ ሰዎችን ህግን እና ትእዛዛትን ለምን ታስተምሯላችሁ?

እንዲህም በሏቸው፣ አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፯፥፱–፲፩።ማቴዎስ ፯፥፮ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ንስሀን እንዲሰብኩ እና የመንግስትን ሚስጥሮች ከአለም ጋር እንዳይካፈሉ አስተማረ።

ንስሀ ግቡ መንግስተ ሰማያት ወደ እናንተ ቀርባለችና ንስሃ ግቡ በማለት ወደ አለም ሂዱ።

እና የመንግስት ሚስጥሮች በውስጣችሁ አስቀሩ፤ ምክንያቱ ይህን በእግራቸው እንዳይረግጡት፤ የተቀደሰውን ለውሾች ለመስጠት ብቁ አይደለም፣ ወይም ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።

፲፩ አለም እናንተ እራሳችሁ ልትሸከሙት የማትችሉትን ሊቀበሉት አይችሉምና፤ ስለዚህ ዕንቁዎቻችሁን አትስጧቸው፣ አለበለዚያም ዞረውባችሁ ያጠቋችኋል።

ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፯፥፲፪–፲፯።ማቴዎስ ፯፥፯–፰ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ለሚጠይቁት ሁሉ አብ ራዕይ እንደሚሰጥ ለደቀመዛሙርቶቹ አስተምሩ።

፲፪ እንዲህም በሏቸው፣ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።

፲፫ የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።

፲፬ ከዚያም ደቀ መዛሙርቶቹ እንዲህ አሉት፣ እንዲህ ይሉናል፣ እኛ ራሳችን ጻድቅ ነን፣ እናም ማንም ሰው እንዲያስተምረን አያስፈልገንም። እግዚአብሔር ሙሴን እና አንዳንድ ነቢያትን እንደሰማ እናውቃለን፤ እኛን ግን አይሰማም።

፲፭ እናም እንዲህ ይሉናል፣ ለደህንነታችን ህጉ አለን፣ እናም ያም ለእኛ ብቁ ነው።

፲፮ ከዚያም ኢየሱስ መለሰ፣ እናም ለደቀ መዛሙርቱ አለ፣ እንደዚህ ለእነርሱ ትመልሳላችሁ፣

፲፯ በእናንተ መካከል፣ ልጅ እያላችሁ፣ እናም እርሱ ተነስቶ፣ አባ፣ እንድገባ እና ከአንተ ጋር እንድመገብ ቤትህን ክፈት ሲል፣ ልጄ ሆይ፣ ግባ፤ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፣ እና የአንተም የእኔ ነው የማይል ሰው ማን ነው?