ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፫፥፴፱–፵፬። ከማቴዎስ ፲፫፥፴፱–፵፪ ጋር አነጻፅሩ፤ ደግሞም ት. እና ቃ. ፹፮፥፩–፯ ተመልከቱ
ከአለም መጨረሻ (ከክፉዎች መደምሰስ) በፊት፣ ከሰማይ የተላኩ መልእክተኞች ጻድቅን ከክፉዎች መካከል ይሰበስባሉ።
፴፱ መከሩም የዓለም መጨረሻ፣ ወይም የክፉዎች መደምሰስ ነው።
፵ አጫጆችም መላእክት፣ ወይም የሰማይ መልእክተኞች ናቸው።
፵፩ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ፣ ወይም በክፉዎች መደምሰስ እንዲሁ ይሆናል።
፵፪ ምክንያቱም የሰው ልጅ ከመምጣጡ ከዚያ ቀን በፊት፣ መላእክቱን እና የሰማይ መልእክተኞቹን ይልካል።
፵፫ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፣ በክፉዎች መካከልም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨትም ይሆናል።
፵፬ ምክንያቱም አለም በአቶነ እሳት ትነዳለችና።