ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፳፮፥፳፪፣ ፳፬–፳፭። ከማቴዎስ ፳፮፥፳፮–፳፰፤ ከጆ.ስ.ት.፣ ማርቆስ ፲፬፥፳–፳፭ ጋር አነጻፅሩ
ኢየሱስ መጀመሪያ የቅዱስ ቁርባንን እንጀራ ቆረሰ እናም ባረከው። ቅዱስ ቁርባን የኢየሱስ ስጋ እና ደም መታሰቢያ ነው።
፳፪ ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ቆርሶም ባረከ፣ እናም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና አላቸው፣ እንካችሁ፣ ብሉ፣ ይህ ለእናንተ በቤዛነት የሰጠሁትን ሥጋዬ ለማስታወስ ነው።
፳፬ ይህም በስሜ ለሚያምኑት ሁሉ ለኃጢአታቸው ስርየት የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜን ለማስታወስ ነው።
፳፭ እና ትእዛዝም እሰጣችኋለሁ፣ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን ነገሮች በትጋት አድርጉ፣ እና እስከመጨረሻም ስለእኔ መስክሩ።