የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፮


ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፮፥፳፭–፳፱።ማቴዎስ ፲፮፥፳፬–፳፮ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ “የአንድን መስቀል ማንሳት” የሚለው ትርጉም ምን እንደሆነ ገለጸ፥ ኀጥያተኝነትን እና የአለም ስግብግብነትን መካድ እና የእርሱንም ትእዛዛት መጠበቅ ናቸው።

፳፭ ከእዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፣ ማንም ሰው ወደ እኔ ከመጣ፣ እራሱን ይርሳ፣ እና መስቀሉን ያንሳና ይከተለኝ።

፳፮ አሁን ሰው መስቀሉን ለማንሳት ሁሉንም ኃጢአተኝነትንና እያንዳንዱን ዓለማዊን ምኞት መካድ፣ እና ትእዛዛቴን መጠበቅ ማለት ነው።

፳፯ ነፍሳችን ለማዳን ብላችሁ ትእዛዛቴን አተተላለፉ፤ በዚህች አለም ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ በሚመጣው አለም ያጠፋታል።

፳፰ ስለ እኔ ግን በዚህች አለም ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ በሚመጣው አለም ያገኛታል።

፳፱ ስለዚህ አለምን ቱ፣ እና ነፍሳችሁን አድኑ፤ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?