ቅዱሳት መጻህፍት
ሙሴ ፰


ምዕራፍ ፰

[የካቲት ፲፰፴፩ (እ.አ.አ.)]

ማቱሳላ ተነበየ—ኖህና ልጆቹ ወንጌልን ሰበኩ—ታላቅ ጥፋት በዛ—ወደ ንስሀ መጠራትም አልተሰማም—እግዚአብሔርም ሰጋዎችን በሙሉ በጥፋት ውሀ ለማጥፋት አወጀ።

ሄኖክም የኖረበት ቀናት ሁሉ አራት መቶ ሰላሳ ዓመት ነበሩ።

እንዲህም ሆነ የሔኖክ ልጅ ማቱሳላም የጌታ ቃል ኪዳን ይሟላ ዘንድ አልተወሰደም ነበር፤ በእውነትም ኖህ የወገቡ ፍሬ እንደሚሆን ቃል ገብቶለት ነበርና።

እንዲህም ሆነ ማቱሳላም ከወገቡ (በኖህ በኩል) የአለም መንግስታት ሁሉ እንደሚመጡም ተነበየ፣ እና በራሱም ላይ ክብርን ወሰደ።

እና በምድር ላይ ታላቅ ርሀብ መጣ፣ እና ጌታም ምድርን በታላቅ ርግማን ረገመው፣ እና በዚያም ብዙ ኗሪዎቹም ሞቱ።

እንዲህም ሆነ ማቱሳላም መቶ ሰማንያ ሰባት ዓመት ኖረ፣ ላሜሕንም ወለደ፤

ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤

ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።

ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፣ ልጅንም ወለደ፣

ስሙንም እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው።

ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ የኖረው አምስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።

፲፩ ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።

፲፪ ኖህም በአራት መቶ ሀምሳ አመቱ ያፌትን ወለደ፤ እና ከአርባ ሁለት አመት በኋላ ሴምን ከያፌት እናት ወለደ፣ እናም በአምስት መቶ አመቱም ካምንን ወለደ።

፲፫ ኖህና ልጆቹም ጌታን አደመጡ፣ እና ምክሩንም ተቀበሉ፣ እና የእግዚአብሐርም ልጆች ተብለው ተጠሩ።

፲፬ እነዚህ ወንዶች በምድር ገፅ ላይ እየተባዙ ሄዱ፣ እና ሴት ልጆችም ለእነርሱ ተወለዱላቸው፣ የሰው ወንዶችም እነዚህ ሴት ልጆች ቆንጆ እንደሆኑ አዩ፣ እና እንደፍላጎታቸውም እነዚህን ሚስቶቻቸው አደረጓቸው።

፲፭ ጌታም ለኖህ እንዲህ አለው፥ የወንድ ልጆችህ ሴት ልጆች ራሳቸውን ሸጠዋል፤ እነሆ፣ ቁጣዬ በሰው ልጆች ላይ ተቀጣጥላለች፣ ድምጼን አያደምጡምና።

፲፮ እንዲህም ሆነ ኖህም ተነበየ፣ እናም የእግዚአብሔርን ነገሮች፣ እንዲሁም በመጀመሪያው እንደነበረው፣ አስተማረ።

፲፯ ጌታም ለኖህ እንዲህ አለው፥ መንፈሴ ከሰው ጋር ሁልጊዜም አይቆይም፣ እርሱ ሁሉም ስጋ መሞት እንዳለበት ያውቃልና፤ ነገር ግን እድሜው አንድ መቶ ሀያ ይሆናል፤ እና ሰዎች ንስሀ ካልገቡ፣ ጎርፉን እልክባቸዋለሁ።

፲፰ በዚያም ቀናት ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ፣ እና ኖህን ለመግደልም ፈለጉ፤ ነገር ግን ጌታ ከኖህ ጋር ነበር፣ እና የጌታ ሀይልም እርሱ ላይ አርፎ ነበር።

፲፱ ጌታ በስርዓቱም ኖኅን ሾመው፣ እና፣ ለሔኖክ እንደተሰጠው፣ ወደ ሰው ልጆች እንዲሄድ እና ወንጌሉን እንዲሰብክ አዘዘው።

እንዲህም ሆነ ኖህ የሰው ልጆች ንስሀ እንዲገቡ ጠራቸው፤ ነገር ግን የእርሱን ቃላትን አላደመጡም።

፳፩ ደግሞም፣ ከሰሙትም በኋላ፣ ወደ ፊቱ መጥተው እንዲህ አሉ፥ እነሆ፣ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ የሰውን ሴት ልጆች ለራሳችን አልወሰድንም? እና እየበላን እየጠጣን፣ እና እያገባንና በጋብቻ እየሠጠን አይደለንምን? ሚስቶቻችንም ልጆችን ወልደውልናል፣ እና እነዚህም እንደ ቀደሙት ሰዎች የታወቁ ጠንካራ ሰዎች ናቸው። እና የኖህን ቃላት አላደመጡም።

፳፪ እግዚአብሔርም የሰዎች ጥፋት በምድር ላይ የበዛ እንደሆነ አየ፤ እና የእያንዳንዱ ሰው የልቡ ሀሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ ሆነ።

፳፫ እንዲህም ሆነ፣ ኖህም ለህዝቡ መስበክን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥ አድምጡ፣ እና የቃላቶቼን ምክር ተቀበሉ፤

፳፬ እንደ አባቶቻችሁም እመኑ ለኃጢአታችሁም ንስሀ ግቡ እና በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፣ እና ሁሉንም ነገሮችን ይገለፅላችሁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ትችላላችሁ፤ እና ይህን ካላደረጋችሁ፣ የጥፋት ውሀ ይመጣባችኋል፤ ይህም ቢሆንም አላደመጡትም።

፳፭ ኖህም በዚህ ተጸጸተ፣ እናም በምድር ላይ እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠሩ ልቡ ተጨነቀ፣ እና ይህም ልቡን እጅግ አሳዘነው።

፳፮ ጌታም እንዲህ አለ፥ የፈጠርሁትን የሰው፣ ሰውና እንስሣት፣ ተንቀሳቃሾች ፍጡራን እስከ ሰማይ ወፎች፣ ከምድር ገፅ አጠፋለሁ፣ ስለፈጠርኳቸው እና ስለሰራኋቸው ኖህ ተጸጽቷልና፤ እና ህይወቱን ለማጥፋትም ስለሚፈልጉ እኔን ጠርቶኛል።

፳፯ እንዲሁም ኖህ በጌታ አይኖች ውስጥ ፀጋን አገኘ፤ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ፍጹምና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ እና ሶስቱ ልጆቹ ሴም፣ ካምንና ያፌት እንዳደረጉት፣ አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ።

፳፰ ምድርም በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች፣ እናም በአመጽም ተሞልታለች።

፳፱ እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ እና እነሆ ረክሳ ሁሉም ስጋዎች ለባሽ አካሄዱን በምድር ላይ አበላሽቶ ነበርና።

እግዚአብሔርም ኖህን እንዲህ አለው፥ የስጋ ለባሽ ሁሉ መጨረሻ በፊቴ መጥቷል፣ ምድርም በአመፅ ተሞልታለችና፣ እናም እነሆ ስጋን ሁሉ ከምድር ውስጥ አጠፋለሁ