አጠቃላይ ጉባኤ
የአጠቃላይ ባለስልጣኖች፣ የክልል ሰባዎች እና አጠቃላይ መሪዎች ድጋፍ
የሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


8:44

የአጠቃላይ ባለስልጣናት፣ የክልል ሰባዎች እና አጠቃላይ የመሪዎች ድጋፍ

ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን፣ የአጠቃላይ ባለሥልጣናትን፣ የአካባቢ ሰባዎችን፣ እና የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ ሀላፊዎች ስም፣ የድጋፍ ድምፅ ትሰጧቸው ዘንድ ስለማቀርብ ዕድለኛ ነኝ፡፡

እባካችሁ ድጋፋችሁን በተለመደው መንገድ ግለጹ። ማንኛውንም ለድጋፍ የቀረቡ ጥቆማዎች የሚቃወሙ ካሉ፣ የካስማቸውን ፕሬዘደንት እንድታነጋግሩ እንጠይቃለን።

ራስል ማሪዮን ኔልሰን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነብይ፣ ገላጭ፣ እና ባለራዕይ፤ ዳለን ሄሪስ ኦክስ የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ፤ እንዲሁም ሔንሪ ቢኒየን አይሪንግ የቀዳሚ አመራር ሁለተኛ አማካሪ በመሆናቸው እንድንደግፋቸው ይቀርባሉ።

ይህንን የምትደግፉ ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ይህን የምትቃወሙ ካላችሁም እንደዚሁ አሳውቁ።

ዳለን ኤች. ኦክስን እንደ የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ፕሬዚዳንት፣ እንዲሁም ጀፍሪ አር. ሆላንድን ደግሞ እንደ አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን ጊዜአዊ ፕሬዚዳንት አድርገን እንድንደግፍ ቀርቧል።

ይህን የምትደግፉ እባካችሁን አሳዩ።

ይህን የምትቃወሙ እንደዚሁ አሳውቁ።

የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባላት በመሆን የሚከተሉትን እንድንደግፍ ቀርቧል፦ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ ክውንተን ኤል. ኩክ፣ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ ኒል ኤል. አንድርሰን፣ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ፣ ጌሪ ኢ. ስቲቨንሰን፣ ዴል ጂ. ሬንላንድ፣ ጌሪት ደብልዩ ጎንግ፣ ዮልሲስ ሶሬስ እና ፓትሪክ ኪሮን።

ይህን የምትደግፉ እባካችሁ አሳዩ።

ይህን የምትቃወሙ፣ በተመሳሳይ መልኩ አሳዩ።

የቀዳሚ አመራርን እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባላትን እንደ ነቢይ፣ ባለራዕዮች እና ገላጮች አድርገን እንድንደግፍ ቀርቧል።

ይህን የምትደግፉ ሁሉ እባካችሁ አሳዩ።

የምትቃወሙም በተመሳሳይ አይነት ምልክት አሳዩ።

የሚከተሉት አጠቃላይ ባለስልጣናት ከነሐሴ 1 ቀን 2024 (እ.አ.አ) ዓ.ም. ጀምሮ ከተመደቡባቸው ቦታዎች ይሰናበተሉ እንዲሁም የክብር ሀላፊነታቸውን ይቀጥላሉ። ሽማግሌ ኢያን ኤስ. አርደርን፣ ሼን ኤም. ቦወን፣ ፖል ቪ. ጆንሰን፣ ኤስ. ጊረርድ ኒልሰን፣ ብሬንት ኤች. ኒልሰን፣ አድሪያን ኦቻዎ፣ ጋሪ ቢ. ሴብን እና ኤቭን ኤ. ሽሙትዝ።

ለእነዚህ ወንድሞች እና ለሚስቶቻቸው በመላው ቤተክርስቲያን ላገለገሉባቸው ዓመታት ያላችሁን ምስጋና ለመግለጽ የምትፈልጉ እጅ በማንሳት ማሳየት ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ሽማግሌ ካርሎስ ኤ. ገዶይ የሰባዎቹ አመራር አባል በመሆን ከማገልገል እናሰናብታለን። ይህም ከነሀሴ 1 ቀን 2024 ዓ.ም (እ.አ.አ) ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።

ሽማግሌ ገዶይ በዚህ ረገድ ላከናወኑት አገልግሎት ያላችሁን ምስጋና ለመግለጽ የምትፈልጉ ሁሉ እንዲሁ በተመሳሳይ መልኩ አሳዩ።

አገልግሎታቸውን የሚያጠናቅቁትን እና ስማቸው በቤተክርስቲያኗ ድረ ገጽ ላይ ሊገኝ የሚችለውን የክልል ሰባዎች በምስጋና እናስታውሳለን።

እነዚህ ወንድሞች እና ቤተሰቦቻቸው ለዓመታት ላደረጉት ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነ አገልግሎት ያላችሁን አድናቆት ለመግለጽ የምትፈልጉ ይህንኑ ማሳየት ትችላላችሁ።

የሰንበት ትምህርት ቤት አጠቃላይ አመራር የሆኑትን ማርክ ኤል ፔስ ፕሬዘደንት፣ ሚልተን ካማርጎ የመጀመሪያ አማካሪ፣ እና ጃን ኢ. ኒውማን ሁለተኛ አማካሪ እናሰናብታለን። ይህም ከነሐሴ 1፣ 2024 (እ.አ.አ) ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል።

እነዚህ ወንድሞች ለሠጡት መለኮታዊ አገልግሎት ያላችሁን ምስጋና ለመግለጽ የምትፈልጉ ሁሉ ይህንኑ ማሳየት ትችላላችሁ።

የሚከተሉትን የሰባዎቹ አመራር አባል አድርገን እንድንደግፍ እናቀርባለን፦ አገልግሎታቸውን በጥር 2024 (እ.አ.አ) የጀመሩት ሽማግሌ ማርከስ ቢ ናሽ፣ እንዲሁም አገልግሎታቸውን በነሐሴ 1፣ 2024 (እ.አ.አ) የሚጀምሩት ሽማግሌ ማይክል ቲ. ሪንግውድ፣ አሙልፎ ቫሌንዙኤላ፣ እና ኤድዋርድ ዱቤ።

ይህንን የምትደግፉ ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ይህን የምትቃወሙ እንደዚሁ አሳውቁ።

የሚቀጥሉን አጠቃላይ ባለስልጣኖች እንዲደገፉ እናቀርባለን፦ ዴቪድ ኤል. ባክነር፣ ግሪጋሪዮ ኢ. ካሲያስ፣ አሮልዶ ቢ. ካቫልካንቴ፣ አይ. ሬይመንድ ኢግቦ፣ ዲ. ማርቲን ጋውሪ፣ ካርል ዲ. ኸርስት፣ ክሪስቶፈር ኤች. ኪም፣ ሳንዲኖ ሮማን፣ ስቲቨን ዲ. ሻምዌይ፣ ማይክል ቢ. ስትሮንግ እና ሰርጂዮ አር. ቫርጋስ።

ይህን የምትደግፉ ሁሉ እባካችሁ አሳዩ።

የምትቃወሙም በተመሳሳይ ምልክት አሳዩ።

ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን(እ.አ.አ) ባካሄድነው የጠቅላላ ጉባኤ የአመራር ስብሰባ 64 አዳዲስ የአካባቢ ሰባዎች እንደተጠሩ እና በቤተክርስቲያኗ ድረ-ገፅ ይፋ እንደተደረጉ እናሳስባለን። እነዚህን ወንድሞች በአዲሱ ምድባቸው እንድትደግፏቸው እንጋብዛችኋለን።

ይህን የምትደግፉ እባካችሁ አሳዩ።

የምትቃወሙም በተመሳሳይ ምልክት አሳዩ።

የሚቀጥሉት የሰንበት ትምህርት ቤት አጠቃላይ አመራር እንዲሆኑ እንዲደገፊ እናቀርባለን፦ ፖል ቪ. ጆንሰን እንደ ፕሬዚዳንት፣ ቻድ ኤች ዌብ እንደ መጀመሪያ አማካሪ፣ እና ጋብሪኤል ደብሊው. ሪድ እንደ ሁለተኛ አማካሪ። ይህም በነሐሴ 1፣ 2024 (እ.አ.አ) ተግባራዊ ይሆናል።

ይህንን የምትደግፉ ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ይህን የምትቃወሙ በተመሳሳይ መልኩ አሳዩ።

ወንድም ሪድ አሁን እንደ አውስትሬሊያ ስድኒ ሚስዮን ፕሬዚዳንት እያገለገሉ እንደሆኑ እና ስለዚህ በሶልት ሌክ ስቲ ውስጥ ለጉባኤው እንዳልተገኙ እናመለክታለን።

ለአጠቃላይ ባለስልጣኖች፣ የክልል ሰባዎች እና አጠቃላይ መሪዎች ድጋፍ እንድናሳይ ሃሳብ ቀርቧል።

ይህን የምትቀበሉ እጃችሁን አንስታችሁ አሳዩ።

ይህን የምትቃወሙ ካላችሁ እንደዚሁ አሳዩ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ለቤተክርስቲያኗ አመራር ያላችሁን እምነት እና ጸሎታችሁን ስለምትቀጥሉ እናመሰግናችኋለን።

በአካባቢ ሰባዎች የሚደረጉ ለውጦች

የሚቀጥሉት የአካባቢ ሰባዎች በአጠቃላይ ጉባኤ ክፍል በሆነው የመሪዎች ክፍለ-ጊዜ ተረጋግጠዋል፦

ዳንኤል ኤ. አቤኦ፣ ሞሪሲዮ ኤ አራውጆ፣ ራንዲ ቲ. ኦስቲን፣ ሚሼል ዲ አቬኞን፣ ፊሊፕ ጄ ብራቮ፣ ሁዋን ጂ ካርዴናስ፣ ሳንቾ ኑ ቹኩኩ፣ ማርክ ጄ ክሉፍ፣ ዳኒሎ ኤፍ. ኮስታሌስ፣ ዳንኤል ኤ. ክሩዛዶ፣ ግሪጎሪዮ ዳቫሎስ፣ ጁሊዮ ኤን. ዴል ሴሮ፣ ራያን ኢ. ዶብስ፣ እስጢፋኖስ ደብሊው ዳየር፣ ብሪክ ቪ. ኤይር፣ ዴኒ ፋአሎጎ፣ ጢሞቴዎስ ኤል. ፋርነስ፣ ማርቲን ፒ. , ኒልስ ኦ. ጄንሰን፣ ፍሪትዝነር ኤ. ጆሴፍ፣ ኪዮኒ ካሶንጎ፣ ጆን ኤስ.ኬ. ካውዌ III፣ ዳን ካዋሺማ፣ ጄ. ጆሴፍ ኪህል፣ ካርል ኤፍ. ክራስስ፣ ዬው ሙን ኩን፣ ዎ ቼኦል ሊ፣ ዋይ ሁንግ ማክ፣ ዴቪድ አር. ማሪዮት፣ ኢግናቲየስ ማዚዮፋ፣ ዴሪክ ቢ ሚለር፣ አልበርት ሙታሪስዋ፣ ማርቪን አይ. ፓሎሞ፣ ኪዩንግ ዮል ፓርክ፣ ዶሚንጎ ጄ. ፔሬዝ፣ ኦስካር ኤ. ፒሬዝ፣ ራውል ፔሬዝ፣ ጋይሌ ኤል. ፖሎክ፣ ፒየር ፖርትስ፣ ማርኮ ኤ. ክዌዛዳ፣ ስቴፈን ቲ ሮክዉድ፣ ጊለርሞ ሮጃስ፣ ኬጎሞሶ ቲ. ሰህሎሆ፣ ሳንድሮ አሌክስ ሲልቫ፣ ጁስዋን ታንዲማን፣ አሱኩ ኢ. ኡዶቦንግ፣ ዳዋይን ጄ. ቫን ሄርደን፣ ሺህ ኒንግ (ስቲቭ) ያንግ፣ ሁዋን ኤፍ. ዞሪያ፣ ለኦፖልዶ ዡዋኚጋ።

የሚቀጥሉት የአካባቢ ሰባዎች በነሀሴ 1 ቀን 2024 (እ.አ.አ) ጀምሮ ከሀላፊነታቸው ይለቀቃሉ፦

ሰለሞን አይ. አሊቼ፣ ጊለርሞ ኤ. አልቫሬዝ፣ ዳረን አር. ባርኒ፣ ጁሊየስ ኤፍ. ባሪንቶስ፣ ጄምስ ኤች. ቤከር፣ ዴቪድ ኤል.ባክነር፣ ግሌን በርጌስ፣ ማርኮስ ካብራል፣ ግሪጎሪዮ ኢ. ካሲላስ፣ ዱንስታን ጂ ቢ ቲ ቻዳምቡካ፣ አላን ሲ ኬ. ቼንግ፣ ፖል ኤን. ክላይተን፣ ሚካኤል ቺዝላ፣ ሂሮዩኪ ዶሞን፣ ሜርናርድ ፒ. ዶናቶ፣ አይ. ሬይመንድ ኢግቦ፣ ዛካሪ ኤፍ ኢቫንስ፣ ሳፔሌ ፋአሎጎ ጁኒየር፣ ሳሎ ጂ. ፍራንኮ፣ ዴቪድ ፍሪሽክኔክት፣ ጆን ጄ ጋሌጎ፣ ኤፍራይን አር. ጋርሺያ፣ ሮበርት ጎርደን፣ ማርክ ኤ. ጎትፍሬድሰን፣ ዲ.ማርቲን ጎሪ፣ ሚካኤል ጄ. ሄስ፣ ብሀኑ ኬ. ክሪስቶፈር ኤች ኪም፣ ኤች.ሞሮኒ ክላይን፣ ስቴፈን ቼ ኮንግ ላይ፣ ቪ.ዳንኤል ላታሮ፣ ታቦ ሌቤቶአ፣ ታርሞ ሌፕ፣ ኢትዝኮትል ሎዛኖ፣ ኬቨን ሊትጎ፣ ክሌመንትኤም. ማትስዋጎታታ፣ ኤድጋርፒ. ሞንቴስ፣ ሉዊዝ ሲ.ዲ. ኪይሮዝ፣ ኢፋኖ ራሶሎንድራይቤ፣ ኤድዋርዶ ዲ. ሬሴክ፣ ቶማስ ጂ. ሮማን፣ ራሞን ኢ. ሳርሚየንቶ፣ ስቲቨን ዲ ሹምዌይ፣ ሉዊስ ስፒና፣ ያሬድ ደብሊው ስቶን፣ ሚካኤል ቢ ጠንካራ፣ ድጃሮት ሱቢያንቶሮ፣ ካርሎስ ጂ. ሱፈርት፣ ቮይ አር. ታኦአሊ፣ ካሪም ዴል ቫሌ፣ ሰርጂዮ አር. ቫርጋስ፣ ሄልሙት ዎንድራ።