የቤተክርስትያኗ ኦዲት ክፍል ሪፖርት፣ 2023 (እ.አ.አ)
ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ቀዳሚ አመራ
ውድ ወንድሞች፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳን ክፍል 120 ላይ እንደተመዘገበው በራዕይ በመመራት፣ የቀዳሚ አመራርን፣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድንን፣ እና የኤጲስ ቆጶስ አመራርን ያቀፈው የአስራት አጠቃቀም መወሠኛ ምክር ቤት ለቤተክርስቲያኗ ከተመደበ ገንዘብ ላይ የሚወጡ ወጪዎችን ይፈቅዳሉ፡፡ የቤተክርስቲያኗ አካላት የተመደበውን ገንዘብ በፀደቀው በጀት፣ መመሪያ እና የአሰራር ደንብ መሠረት ያከፋፍላሉ፡፡
በቂ የትምህርት መረጃ ያላቸው ሞያተኞች እና ከሌሎች የቤተከርስቲያኗ ክፍሎች እና አካላት ነፃ በሆነ ሁኔታ የተዋቀረው የቤተክርስቲያኗ የኦዲት ክፍል፣ የተሰበሰቡ መዋጮዎችን፣ ወጪ የተደረጉ ገንዘቦችን፣ እና የቤተክርስቲያኗን ሀብት መጠበቅን በሚመለከት አስተማማኝነት ያለው ኦዲት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
በተከናወነው ኦዲት መሠረት፣ ሁሉም ቁሣቁሶች፣ የተሰበሰቡ መዋጮዎች፣ ወጪ የተደረጉ ገንዘቦች፣ እና የ2ዐ23 (እ.አ.አ) ዓመተ ምህረት የቤተክርስቲያኗ ንብረቶች፣ ቤተክርስቲያኗ ባፀደቀቻቸው በጀቶች፣ የኦዲት ልምድ እና መመሪያዎች መሠረት በአግባቡ የተመዘገቡ ስለመሆኑ የቤተከርስቲያኗ ኦዲት አስተያየት ያሣያል፡፡ ቤተክርስቲያኗ አባላቶቿ በበጀት ስለመኖር፣ እዳን ስለማስወገድ እና አስፈላጊ ለሆነ ጊዜ ስለመቆጠብ ያስተማረቻቸውን ልምዶች ትከተላለች፡፡
በአክብሮት የቀረበ፣
የቤተክርስትያኗ ኦዲት ክፍል
ጄርድ ቢ. ላርሰን
የአስተዳደር ዳይሬክተር