አጠቃላይ ጉባኤ
ቃላት ዋጋ አላቸው
የሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


13:58

ቃላት ዋጋ አላቸው

ቃላት ስሜትን ይመሰርታሉ። ጥሩ ይሁን መጥፎ፣ ሃሳባችንን፣ ስሜታችንን እና ልምዳችንን የናገራሉ።

በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ወንድሞች፣ እህቶች እና ጓደኞች፣ ብዙዎቹ የቤተክርስቲያናችን አባል የሆኑትን እንዲሁም ብዙዎቹ ጓደኞች እና ለዙህ የጉባኤ ስርጭት አዲስ አድማጮች የሆኑትን ይህንን ሰፊ ታዳሚ ለመናገር በመቻሌ ክብር ይሰማኛል። እንኳን ደህና መጣችሁ!

ከዚህ መናገሪያ ቦታ ላይ የሚካፈሉት መልዕክቶች በቃላት አማካኝነት ነው የሚደረጉት። በእንግሊዝኛ ነው የሚደረጉት እናም አንድ መቶ ወደሚጠጉ ቋንቋዎች ይተረጎማሉ። ሁሌም መሰረቱ ተመሳሳይ ነው። ቃላት። እናም ቃላት በጣም ዋጋ አላቸው። እንደገና ልድገመው። ቃላት ዋጋ አላቸው!

እንዴት እንደምንግባባ ወሳኝ መሰረት ናቸው፣ እምነታችንን፣ ስነ ምግባራችንን እና አመለካከታችንን ይወክላሉ። አንዳንዴ ቃላትን እንናገራለን፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እናዳምጣለን። ቃላት ስሜትን ይመሰርታሉ። ጥሩ ይሁን መጥፎ፣ ሃሳባችንን፣ ስሜታችንን እና ልምዳችንን የናገራሉ።

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ቃላት፣ ግድየለሽ፣ የተጣደፉ እና ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዴ ከተናገርናቸው በኋላ፣ መልሰን መውስድ አንችልም። ሊያቆስሉ፣ ሊቀጡ፣ ሊሰነጥቁ እና ወደ አፍራሽ ተግባሮች ሊመሩ ይችላሉ። እንደ ሸክም ሊጫኑን ይችላሉ።

በሌላ መልኩ፣ ቃላት ድልን ማክበር ይችላሉ፣ ተስፋ ያላቸው እና የሚያበረታቱ መሆን ይችላሉ። መንገዳችንን እንደገና እንድናስብ፣ እንድናድስ እና እንድንቀይር ሊገፋፉን ይችላሉ። ቃላት አእምሯችንን ወደ እውነት መክፈት ይችላሉ።

ለዚያም ነው በመጀመሪያው እና በዋነኛ ደረጃ የጌታ ቃላት ዋጋ ያላቸው።

በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ ነቢዩ አልማ እና ህዝቦቹ በጥንቷ አሜሪካ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ችላ ካሉ፣ ልባቸውን ካደነደኑ እና ባህላቸውን ከበከሉ ሰዎች ጋር ማለቂያ የሌለው ጦርነት አጋጠማቸው። ታማኞች ለመዋጋት ይችሉ ነበር፣ ነረግ ግን አለማ እንዲህ ምክር ሰጠ፦ “እናም አሁን፣ የቃሉ መሰበክ ህዝቡ ትክክለኛውን እንዲሰራ የሚመራ ታላቅ ዝንባሌ ስላለው—አዎን፣ ይህም ከጎራዴ፣ ወይም ከሚሆንባቸው ማንኛውም ነገር፣ የበለጠ በአዕምሮአቸው ላይ ውጤት ይኖረዋል—ስለዚህ አልማ ኃያል ውጤት ያለውን የእግዚአብሔር ቃል በጎነት መሞከራቸውአስፈላጊነቱን አሰበ።”

“የእግዚአብሔር ቃል” ሁሉንም ሌላ አባባሎች ይበልጣል። እንደዚህም ሆኖ ነበር ምድር ከመፈጠሯ ጀምሮ ጌታ “ብርሃን ይሁን [ሲል]፤ ብርሃንም [ሲሆን]።”

በአዲስ ኪዳን ውስጥ እንደነዚህ አይነቶቹ ማረጋገጫዎች ከአዳኙ መጡ፦ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።”

እና እንደዚህ አይነቱ ፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።”

እንዲሁም ከማርያም፣ የኢየሱስ እናት፣ ይህ ትሁት ምስክርነት መጣ፦ “እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ።”

የእግዚብሔርን ቃል ማመን እና ማዳመጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ ያደርገናል። ፕሬዝዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ቃል ገቡ፣ “የእርሱን ቃላት ካጠናችሁ፣ እንደ እርሱ የበለጠ የመሆን አቅማችሁ ይጨምራል።”

“የበለጠ የተባረክን እና የተቀደስን—እንደ አዳኝ የበለጠ እንሁን” እንደሚለው መዝሙር ሁላችንም መሆን አንፈልግምን?

ወጣት ጆሴፍ ስሚዝ ተንበርክኮ እንዲህ የሚለውን የሰማይ አባቱን ቃላት ሲሰማ በአእምሮዬ እስላለው፦ “[ጆሴፍ፣] የምወደው ልጄ ይህ ነው። እርሱን ስማው!”

እኛ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ውስጥ “እርሱን [እንሰማለን]” ነገር ግን በገጹ ላይ እንዲቀመጡ ብቻ ነው የምንፈቅደው ወይስ እርሱ እየተናገረን እንደሆነ እንገነዘባለን? እንቀየራለን?

በግል ራዕይ እና በመንፈስ ቅዱስ መነሳሳት ውስጥ፣ በጸሎት መልሶች ውስጥ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በሃጥያት ክፍያው ሃይል አማካኝነት ሸክማችንን በሚያነሳበት፣ ይቅርታን እና ሰላምን በሚሰጠን፣ “በፍቅር ክንዶቹ” በሚያቅፈን ወቅት “እርሱን [እንሰማለን]።”

ሁለተኛ፣ የነቢያት ቃላት ዋጋ አላቸው።

ነቢያቶች ስል ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትዊነት ይመሰክራሉ። የእርሱን ወንጌል ያስተምራሉ እናም እርሱ ለሁሉም ያለውን ፍቅር ያሳያሉ። በሕይወት ያሉት ነቢያችን ፕሬዚዳንት ረስል ኤም ኔልሰን የጌታን ቃል እንደሚሰሙ እና እንደሚናገሩ ምስክርነቴን እሰጣለው።

ፕሬዚዳንት ኔልሰን አንደበተ ርትዑ ናቸው። እንደዚህ ተናግረዋል፣ “በቃልኪዳን መንገድ ላይ መጓዛችሁን ቀጥሉ፣” “እስራኤልን ሰብስቡ፣” “እግዚአብሔር ያሸንፍ፣” “የመረዳት ድልድዮችን ገንቡ፣” “ምስጋናን ስጡ፣” “በኢየሱስ ክርስቶስ እምነትን ጨምሩ፣” “የምስክርነታችሁን ሃላፊነት መውሰድ፣” እና “አስታራቂዎች ይፈለጋሉ።”

በጣም በቅርቡ “ሰለስቲያል [እንድናስብ]” ጠይቀውናል። እንዲህ ብለዋል፣ “አጣብቂኝ ውስጥ ስትገቡ ሰለስቲያል አስቡ!” በፈተና ስትፈተኑ፣ ሰለስቲያል አስቡ!” ህይወት ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ሲያሳዝኗችሁ ስለ ሰለስቲያል አስቡ! አንድ ሰው ያለጊዜው ሲሞት ስለ ሰለስቲያል አስቡ። …የህይወት ጫናዎች ሲደራረቡባችሁ፣ ሰለስቲያል አስቡ!” ሰለስቲያል ስታስቡ፣ልባችሁ ቀስ በቀስ ይቀየራል፣ … ፈተናዎችን እና ተቃውሞዎችን በአዲስ መልኩ ታያላችሁ፣ … [እንዲሁም] እምነታችሁ ይጨምራል።”

“ሰለስቲያል ስናስብ፣ ነገሮችን በርግጥ እንዳሉ እናም በርግጥ እንደሚሆኑ እንመለከታለን።” የግራ መጋባት እና የጸብ ሸክም በሞላበት በዚህ ዓለም ውስጥ፣ ሁላችንም ያ አመለካከት ያስፈልገናል።

ሽማግሌ ጆርጅ አልበርት ስሚዝ፣ የቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት ከመሆናቸው ከረጅም ጊዜ በፊት፣ ነቢዩን ስለመደገፍ እና ቃላቶቹን ስለመከተል እንዲህ ብለዋል። እንዲህ አሉ፦ “እጃችንን ከፍ ስናደርግ የምንወጣው ግዴታ… በጣም የተቀደሰ ነው። … ይህም ማለት … እንደግፋቸዋለን፤ እንጸልይላቸዋለን …እና ጌታ እንደሚመራቸው፣ መመሪያቸውን ለማከናወን እንጥራለን።” በሌላ አባባል፣ የነቢያችንን ቃላት በትጋት ተግባራዊ እናደርጋለን።

ትላንትና በአለም አቀፉ ቤተክርስቲያናችን ከ15 ነቢያት፣ ገላጮች እና ባለ ራዕዮች አንዱ በመሆን ድጋፍ በማግኘቴ፣ ነቢዩን በመደግፍ እና ቃላቱን በመቀበል ከልምዶቼ መካከል አንዱን ላካፍላችሁ እፈልጋለው። ለእኔ “የጌታ ድምፅ በቃሉ ሲናገረኝ ሰምቻለሁ” ብሎ እንደተናገረው እንደ ነቢዩ ያዕቆብ ነበር።

ሽማግሌ እና እህት ራስባንድ በታይላንድ።

ባላፈው ጥቅምት የቤተክርስቲያኗ 185ኛ ቤተመቅደስ የሚሆነው ለመመረቅ እየተዘጋጀሁ ስለነበር፣ ባለቤቴ ሜለኒ እና እኔ በታይላንድ፣ ባንኮክ ውስጥ ነበርን። ለእኔ፣ ይህ የማይታመን እና ትሁት የሚያደርግ የሥራ መደባ ነበር። ይህ በደቡብ ምስራቅ እስያ ባሕረ ሰላጤ ላይ የመጀመሪያው ቤተመቅደስ ነበር። የጌታ ቤት ይሆን ዘንድ ረቂቅ በሆነ መንገድ የታነፀ—ባለ ስድስት ፎቅ፣ ባለዘጠኝ የሾሉ መዋቅሮ ያሉት ፣ “የተጋጠመ” ነበር። ለወራቶች ያህል፣ ስለምረቃው አሰላስዬ ነበር። በነፍሴ እና በአእምሮዬ ውስጥ የሰፈረው ነገር፣ አገሪቷ እና ቤተመቅደሷ በነቢያት እና በሐዋርያት ክንዶች ውስጥ እንደታቀፉ ነው። ቤተመቅደሱ እንደሚገነባ ያስተዋወቁትፕሬዚዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ነበሩ ምረቃውን ያስተዋወቁት ደግሞ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ነበሩ ።

የባንኮክ ታይላንድ ቤተመቅደስ

የምረቃውን ጸሎት ያዘጋጀሁት ከወራት በፊት ነበር። እነዚያ ቅዱስ ቃላት ወደ 12 በሚሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል። ዝግጁ ነበርን። ወይም እንደዛ ብዬ ነበር ያሰብኩት።

ምረቃው ከሚከናወንበት ቀን በፊት፣ ስለምረቃ ጸሎቱ ባልተረጋጋ አስቸኳይ በሆነ ስሜት ከእንቅልፌ እንድነሳ ተደረኩኝ። ጸሎቱ ተዘጋጅቷል ብዬ በማሰብ፣ መነሳሳቱን ወደ ጎን ለማለት ሞከርኩኝ። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሊተወኝ አልቻለም። የተወሰኑ ቃላት እንደጎደሉ ተሰማኝ፣ እና በመለኮታዊ ንድፍ ቃላቱ በራዕይ ወደ እኔ መጡ፣ እና እንደዚህ የሚሉትን ቃላት በጸሎቱ መጨረሻ አካባቢ አስገባኋቸው፦ “በህይወታችን ውስጥ ያንተ መንፈስ እንዲያሸንፍ እየፈቀድን እና ሁሌም አስታራቂዎች ለመሆነ በመጣር ሰለስቲያል እናስብ።” “ሰለስቲያል አስቡ፣” “[መንፈስ] ያሸንፍ፣” “አስታራቂዎች ይፈለጋሉ” የሚሉትን በሕይወት ያሉትን የነብያችንን ቃላት እንድሰማ ጌታ እያስታወሰኝ ነበር። የነብይ ቃላት ለጌታ እና ለእኛ ዋጋ አላቸው።

ሶስተኛ፣ በጣም አስፈላጊ የሆኑት የእኛ የራሳችን ቃላት ናቸው። እመኑኝ፣ ስሜት ገላጭ ምስሎች በሞሉበት አለማችን ውስጥ ቃላቶቻችን ዋጋ አላቸው።

ቃላችን የሚያግዙ ወይም ቁጡ፣ ደስተኛ ወይም መልካም ያልሆኑ፣ ሩህሩህ ወይም ግድ የለሽ ሊሆኑ ይችላሉ። በንዴት ወቅት፣ ቃላት ሊነድፉ እና በሚያም ሁኔታ በነፍስ ውስጥ ጠልቀው ሊገቡ እና እዛ ሊቀመጡ ይችላሉ። በበይነመረብ፣ በመልክት ጽሁፍ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በትዊቶች ላይ የምናሰፍራቸው ቃላቶቻችን እኛ ካሰብነው የተለየትርጉም ሊይዙ ይችላሉ። ስለሆነም የምትናገሩትን ነገር እና የምትናገሩበትን መንገድ ተጠንቀቁ። በቤተሰባችን ውስጥ፣ በተለይም ከባሎች፣ ከሚስቶች እና ከልጆች ጋር፣ ቃላችን አንድ ሊያደርገን ወይም በመካከላችን ሽብልቅን ሊሰድ ይችላል።

ችግሮችን እና ልዩነቶችን ለማስወገድ፣ ከፍ ለማድረግ እና እርስ በእርስ ለማጽናናት ልንጠቀማቸው የምንችላቸውን ሶስት ቀላል ሃረጎች ሃሳብን ላቅርብ።

“አመሰግናለሁ።”

“አዝናለሁ።”

እና “እወድሻለው/ካለው።”

እነዚህን ትሁት ሃረጎች ለተለየ ክስተት ወይም ለአደጋ ጊዜ አታስቀምጧቸው። በተደጋጋሚ እና ከልብ በሆነ መልኩ ተጠቀሟቸው፣ ምክንያቱም ለሌሎች ክብርን ስለሚያሳዩ። ንግግር እርካሽ እየሆነ ነው፤ ያንን ፈለግ እንዳትከተሉ።

በአሳንሰር ላይ፣ በመኪና ማቆሚያ ውስጥ፣ በገበያ ውስጥ፣ በቢሮ ውስጥ፣ በሰልፍ ላይ ወይም ለጎረቢታችን ወይም ለጓደኛችን “አመሰግናለሁ” ማለት እንችላለን። ስህተትን ስንሰራ፣ ስብሰባ ሲያመልጠን፣ ልደትን ስንረሳ ወይም አንድን ሰው በህመም ውስጥ ስናይ “አዝናለሁ” ማለት እንችላለን። “እወድሻለው” ማለት እንችላለን እናም እነዛ ቃላት የሚከተሉትን መልዕክት ይሸከማሉ፣ “ስለአንቺ እያሰብኩኝ ነው፣” “ስለአንቺ እጨነቃለሁ፣” “አለውልሽ፣” ወይም “ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነሽ።”

ግላዊ ምሳሌን ላካፍል። ባሎች፣ ስሙ። እህቶች፣ ይህ እናንተንም ይረዳል። በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሙሉ ጊዜ ምደባዬ በፊት፣ ለኩባንያዬ በስፋት ተጓዝኩኝ። ለረጅም ጊዜ ወደ ዓለማችን እሩቅ ቦታዎች ሄጃለው። በቀኔ መጨረሻ ላይ፣ የትም ብሆን ሁሌ እቤት እደውላለው። ባለቤቴ ሜለኒ ስልኩን ስታነሳ እና ዘገባዬን ሳቀርብ፣ ንግግራችን ሁሌም “እወድሻለሁ/ሃለሁ” ወደማለት ይመራን ነበር። በየቀኑ፣ እነዚያ ቃላት የነፍሴ እና የባህሪዬ መልህቅ በመሆን አገለገሉኝ፤ ለእኔ ከክፋት ዕቅድ መከላከያዎች ነበሩ። “ሜለኒ፣ እውድሻለሁ” የሚለው ቃል በመካከላችን ያለውን ውድ የሆነ እምነትን ገለጸ።

ፕሬዚዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣፣ “እንዳይወላውሉ የሚደረጉ እግሮች፣ የሚያዙ እጆች፣ የሚበረታቱ አእምሮዎች፣ የሚነሳሱ ልቦች፣ እና የሚድኑ ነፍሶች አሉ።” ይሉ ነበር “አመሰግናለሁ፣” “አዝናለሁ፣” “እውድሻለሁ/ሃለሁ” ማለት ያንን ያደርጋል።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ቃላት ዋጋ አላቸው።

ወደ ደህንነት፣ ወደሚመራን እና ወደሚያበረታታንን የነቢያችን ቃላት እና ማን እንደሆንን እና ምንን እንደምንወድ ወደሚናገረው የገዛ ቃላችንን የሚያመራውን “የክርስቶስን ቃል [ከተመገብን]” የሰማይ ሃይል በላያችን ላይ እንደሚፈስ ቃል እገባለው። “የክርስቶስ ቃል ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ ይነግራችኋልና።” እኛ የሰማይ አባት ልጆች ነን እና እርሱም የእኛ እግዚአብሔር ነው እና እኛ “በመላዕክት ልሳን” ማለትም በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንድንናገር ይጠብቃል።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ። በብሉይ ኪዳን ነቢይ ኢሳይያስ ቃላት መሰረት፣ እርሱ “ድንቅ፣ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ” ነው። እናም ሐዋርያው ዮሐንስ ግልጽ እንዳደረገው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ ቃል ነው ።

ለክርስቶስ መለኮታዊ አገልግሎት፣ ቃላቱን ለማወጅ፣ እና እንደ የእርሱ የተለየ ምስክር ለመቆም እንደተጠራ ሐዋርያ ይህን እመሰክራለሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።