አጠቃላይ ጉባኤ
ዘላቂ ፍሬ
የሚያዝያ 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


11:39

ዘላቂ ፍሬ

ተስፋ የተገቡልንን በረከቶች ለዘለዓለም ለማግኘት ከፈለግን መንፈስ ቅዱስ ስርአቶቻችንን እንዲያትም ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ትንሽ ልጅ እያለሁ የበሰለ ኮክ እወድ ነበር። አሁንም ድረስ፣ ሃይለኛ ጣእሙ እንዲሁም እርጥበት ያለውን የበሰለ ኮክ የመጉመጥ ሃሳብ አፌን በምራቅ ይሞላዋል። በደንብ የበሰለ ኮክ፣ ከተለቀመ በኋላ ሳይበላሽ ከሁለት እስከ አራት ቀናት ይቆያል። የተሰበሰበ ኮክ ለመጪው ክረምት እንዲቆይ በጠርሙስ ውስጥ ለማሸግ፣ በኩሽና ውስጥ እናቴን እንዲሁም ወንድም እና እህቶቼን እቀላቀል ስለነበረው ጊዜ አስደሳች ትውስታ አለኝ። በትክክል ካሸግነው፣ ይሄ ጣፋጭ ፍሬ፣ ከሁለት እስከ አራት ቀናት ብቻ ሳይሆን እስከ በዙ አመታት ይቆያል። በትክክል ከተዘጋጀ እና እንዲሞቅ ከተደረገ፣ ማሸጊያው እስኪከፈት ድረስ ሳይበላሽ ይቆያል።

“[እንድንሄድ]ና ፍሬ [እንድናፈራ]፣… ፍሬአች[ን]ም [እንዲ]ኖር” ክርስቶስ መርቶናል። ነገር ግን ስለ ኮክ እያወራ አልነበረም። እየተናገረ የነበረው እግዚያብሔር ለልጆቹ ስላለው በረከቶች ነው። ቃል ኪዳኖችን ገብተን ከጠበቅን፣ ከቃልኪዳኖቻቸን ጋር የተያያዙት በረከቶች ከዚህ ህይወት አልፈው፣ ለዘለአለም የሚዘልቁ ፍሬዎች በመሆን በእኛ ላይ ለዘለአለም ይታተማሉ ወይም ይቆያሉ።

መንፈስ ቅዱስ፣ እንደ ቅዱስ የተስፋ መንፈስ ባለው መለኮታዊ ሚና፣ ለቃል ኪዳናቸው ታማኝ በሆኑት ከሟችነት በኋላ ትክክለኛ እንዲሆኑ እያንዳንዱን ስርዓት ያትማል። የተገቡት የቃልኪዳን በረከቶች ዘላቂ ፍሬ ሆነው ለዘላለም እንዲቆዩ፣ መንፈስ ቅዱስ የተቀደሱ ስርአቶችን ለኛ ማተሙ ወሳኝ ነው።

በተለይ ከፍ ከፍ መደረግ የምንፈልግ ከሆነ ይሄ አስፈላጊ ነው። ፕሬዘዳንት ራሰል ኤም ኔልሰን እንዳስተማሩት፤ “መጨረሻውን በአእምሮአችን ይዘን መጀመር አለብን። … በእርግጥ፣ ለእያንዳንዳችን፣ የምንፈልገው አይነት ‘መጨረሻ’ ከሰማይ አባታችን እግዚያብሔር እና ከልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር በዘላለማዊ ደህንነት መኖር ነው።” ፕሬዘዳንት ኔልሰን ጨምረው እንዳሉትም፤ “ሰለስቲያል ጋብቻ ለዘላለም የመኖር ቁልፉ ክፍል ነው። ትክክለኛውን ሰው፣ በትክክለኛው ቦታ፣ በትክክለኛው ስልጣን ማግባት እና ቅዱስ ቃልኪዳኖችን በእምነት መጠበቅን ይጠይቃል። ከዚያም፣ በእግዚአብሔር ሰለስቲያል መንግስት ውስጥ የዘላለማዊ ደህንነት ማረጋገጫ ይኖረናል።”

ከፍ ከፍ የመደረግ በረከቶች ምንድን ናቸው? እነዚያም የሚያካትቱት እንደ ባል እና ሚስት በእግዚይብሔር መገኘት ውስጥ መሆንን፣ “ዙፋኖችን፣ ነገስታትን፣ ስልጣናትን እና ሃይሎችን፣ … እናም የዘሮችን ለዘለአለም መቀጠልን“ መውረስ፣” እንዲሁም አብ እግዚያብሔር ያለውን ሁሉ መውረስን ነው።

በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ጌታ ይህን ገለጠ፤

“በሰለስቲያል ክብር ውስጥ ሶስት ሰማያት ወይም ደረጃዎች አሉ፤

“ከፍተኛውን ለማግኘት፣ ሰው ወደ እዚህ የክህነት ስርዓት መግባት አለበት [ይህም አዲስ እና ዘለአለማዊ የጋብቻ ቃል ኪዳን ማለት ነው]፤

“እና ይህን ባያደርግ፣ ሊያገኘው አይችልም።

“ወደሌሎቹ ለመግባት ይችላል፣ ነገር ግን ያን የሚያደርገው መጨረሻው መንግስቱ ነው፤ ተጨማሪም ሊያገኝ አይችልም።

አንድ ሰው ያላገባ ሆኖ በሰለስቲያል መንግስት ወይም እግዚያብሔር ባለበትመሆን እንደሚችል እንማራለን። ነገር ግን በታላቁ የሰለስቲያል መንግስት ውስጥ በዘላለማዊ ደህንነት ለመኖር፣ አንድ ሰው በትክክለኛው ስልጣን እና በጋብቻ መጣመር ይኖርበታል እናም በዚያ ትዳር ውስጥ ለተገቡት ቃልኪዳኖ እውነተኛ መሆን አለበት። ለእንዚህ ቃልኪዳኖች ታማኝ ስንሆን፣ የቃልኪዳኑ ቅዱሱ መንፈስ የጋብቻ ቃልኪዳናችንን ያትምልናል። እነዚህ የታተሙት በረከቶች “ዘላቂ ፍሬ” ይሆናሉ።

አዲሱን እና ዘለአለማዊውን የጋብቻ ቃልኪዳን በታማኝነት ለመጠበቅ የሚያስፈልገው ምንድን ነው?

ሁለት አይነት ጥምረቶች፣ በባል እና ሚስት መሃል ያለ ጎናዊ ጥምረት እና ከእግዚያብሔር ጋር ወደ ላይ ያለ ጥምረት፣ እንዳለ ፕሬዘዳንት ራሴል ኤም ኔልሰን አስተምረዋል። የዘለአለማዊ ደህንነት በረከቶች በእኛ ላይ እንዲታተሙ እና ከዚህ ህይወት በኋላ አብረውን እንዲቆዩ፣ ለጎናዊው እና ለላይኛው የቃልኪዳን ጥምረቶች እውነተኛ መሆን አለብን።

ጎናዊውን ጥምረት ከባለቤታችሁ ጋር እንድትጠብቁ፣ እግዚአብሔር “ሚስ[ታችሁን] [ወይም ባላችሁን] በሙሉ ል[ባችሁ] ውደዱ፣ እና … ከሌላ ከማንም ሳይሆን ከእርሷ [ወይም እርሱ] ጋር [ተጣበቁ]”በማለት መክሮናል። ላገቡት፣ ከሌላ ከማንም ጋር ሳይሆን ከእሷ ወይም ከእሱ ጋር መጣበቅ ማለት በፍቅር አብሮ መመካከር፣ መዋደድ እና አንዳችሁ ሌላኛውን መንከባከብ፣ ከሌላ ከውጪአዊ ፍላጎቶች ይልቅ ከባለቤታችሁ ጋር ያለውን ጊዜ ማስቀደም፣ እንዲሁም ድክመታችሁን ለማሸነፍ እግዚአብሔርን ትጠራላችሁ ማለት ነው። ይሄ ማለትም ከጋብቻችሁ ውጪ ሌላ ምንም ስሜታዊ ወይም ጾታዊ ግንኙነ አለማድረግ፣ መመኘትን የሚያስከትሉ ማሽኮርመም እና መጠናናትን፣ የእራቁት ስዕልን አለመመልከትን ያካትታል።

ጎናዊው ጥረትን ለመጠበቅ፣ እያንዳንዱ ተጣማሪ ጋብቻ ውስጥ ለመሆን መፈለግ አለበት። ፕሬዘዳንት ዳሊን ኤች ኦክስ በቅርብ እንዳስተማሩት፤ “እርሱ [እግዚአብሔር] ማንንም ያለ ፍላጎቱ ወደ መታተም ግንኙነት ውስጥ አስገድዶ እንደማያስገባም እናውቃለን። የመታተም ግንኙነት በረከቶች ቃልኪዳናቸውን ለሚጠብቁ ሁሉ የተረጋገጡ ናቸው ነገር ግን የመታተምን ግንኙነት ብቁ ባልሆኑ ወይም ፍላጎት በሌላቸው ላይ በመጫን አይደለም።”

ወደላይ ያለው ጥምረት ሲሉ ፕሬዘዳንት ኔልሰን ምን ማለታቸው ነው? የወደላዩ ጥምረት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባው ነው።

የወደላዩን ጥምረት ከእግዚያብሔር ጋር ለመጠበቅ፣ የመታዘዝን፣ የመስዋእትን፣ የወንጌልን፣ የንጽህናን፣ እና የመሰጠትን ህግጋቶች አስመልክቶ በቤተመቅደስ ለገባናቸውን ቃልኪዳኖች እውነተኛ መሆን አለበን። ዘላለማዊ አጋራችንን ለመቀበል እና የተቀደሰ ባለቤት እና ወላጅ ለመሆንም ከእግዚያብሔር ጋር ቃል እንገባለን። የወደላዩን ጥምረት ስንጠብቅ፣ በአብረሃማዊ ቃልኪዳን አማካኝነት የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል የመሆን በረከቶችን እንዲሁም ለዘር፣ ለወንጌል እና ለክህነት በረከቶችም ጭምር ብቁ እንሆናለን። እነዚህ በረከቶች ዘላቂ ፍሬዎችም ናቸው።

በአዲሱ እና በዘላለማዊው ቃልኪዳን ውስጥ የሚገቡ ሁሉ እውነተኛ ሆነው እንደሚቆዩ እና በረከቶቹ እስከዘላለም በእነርሱ ላይ እንደሚታተሙ ተስፋ ብናደርግም፣ ያ ስኬት አንዳንዴ ከእኛ የራቀ ይመስላል። በአገልግሎቴ ውስጥ፣ ቃልኪዳኖችን የሚገቡ እና የሚጠብቁ፣ ነገር ግን ባለቤታቸው እንደዚያ ያልሆኑ አባላት ያጋጥሙኛል። በምድራዊ ህይወት ውስጥ የማግባት እድል የማይኖራቸው፣ ያላገቡ ሰዎችም አሉ። ለጋብቻ ቃልኪዳኖቻቸው ታማኝ ያልሆኑም አሉ። በእነዚህ በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ምን ያጋጥማቸዋል?

  1. የቤትመቅደስ ቡራኬን ስትቀበሉ ለገባችሁት ቃልኪዳኖች ታማኝ ሆናችሁ ከቆያችሁ፣ ባለቤታችሁ የሱን ወይም የሷን ቃልኪዳኖች ቢሰብሩ ወይም ከጋብቻ ቢወጡም በቡራኬው ውስጥ የተገቡላችሁን የግል በረከቶች ትቀበላላችሁ። በጋብቻ ታትማችሁ ኋላ ላይ የተፋታችሁ ከሆነ፣ እንዲሁም መታተማችሁ ያልተሰረዘ ከሆነ፣ እናንተ ታማኝ ሆናችሁ እስከቆያችሁ ድረስ የዚያ መታተም የግል በረከቶች ለእናንተ ይቆያሉ።

    አንዳንድ ጊዜ፣ በመከዳት እና እውነተኛ የመጎዳት ስሜት ምክንያት፣ በምድር እና ለዘላለም ከነሱ ለመራቅ ታማኝ ባለትዳር ታማኝ ካልሆኑት አጋራቸው ጋር ያላቸውን መታተም ለመሰረዝ ይፈልጉ ይሆናል። ንስሃ ካልገባ የትዳር አጋር ጋር ተጣምሬ እቀራለሁ ብላችሁ የምትሰጉ ከሆነ፣ አስታውሱ፣ ያ አይሆንም! እግዚአብሔር ማንም ሰው ያለ ፍላጎቱ በመታተም ግንኙነት ውስጥ እንዲቆይ አይጠብቅም። የእኛ ፍላጎቶች እና ምርጫዎች የሚፈቅዱልንን እያንዳንዱን በረከቶች እንድንቀበል የሰማይ አባት ያደርጋል።

    ሆኖም፣ መታተምን መሰረዝ ከሆነ የተፈለገው፣ ምርጫው ይጠበቃል። አንዳንድ አሰራሮችን መከተል ይቻላል። ነገር ግን ይህ ቀለል ተደርጎ መደረግ የለበትም! የመጀመሪያ አመራር በምድር እና በሰማይ ለማተም የክህነት ቁልፎች አላቸው። አንዴ የመታተም ስረዛ በመጀመሪያ አማካሪ ከተደረገ በኋላ፣ ከዚያ መታተም ጋር ተያይዘው ያሉት በረከቶች አይተገበሩም፤ በጎናዊ እንዲሁም ወደላይም ተሰርዘዋል። የዘላለማዊ ደህንነትን በረከቶች ለመቀበል፣ በዚህ ወይም በሚቀጥለው ህይወት፣ ይህን አዲሱን እና ዘላለማዊውን ቃልኪዳን ለመግባት እና በታማኝነት ለመጠበቅ ፍላጎት ማሳየት አለብን።

  2. በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላችሁ ያላገባችሁ አባላት፣ እባካችሁ አስታውሱ “በጌታ በራሱ መንገድ እና ጊዜ፣ ምንም አይነት በረከት ከእርሱ ታማኝ ቅዱሳን አይከለከልም። ጌታ ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ልቡ ፍላጎት እና ተግባሩ ይፈርዳል እናም ይሸልማል።”

  3. ለቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች ታማኝ ሆናችሁ ካልቆያችሁ፣ ተስፋ አለ? አዎን! የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የተስፋ ወንጌል ነው። ያ ተስፋ በእውነተኛ ንሰሃ እና በታዛዥነት የክርስቶስን አስተምሮቶች በመከተል በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ይመጣል። ግለሰቦች ቅዱስ ቃልኪዳኖችን በመስበር፣ ከፍተኛ ስህተትን ሲሰሩ አይቻለሁ። እውነተኛ ንሰሃ የሚገቡ፣ ይቅር የተባሉ፣ እና ወደ ቃልኪዳኑ መንገድ የሚመለሱ ሰዎችን በተደጋጋሚም አያለሁ። የቤተመቅደስ ቃልኪዳናችሁን ሰብራችሁ ከሆነ፣ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትዞሩ፣ ከኤጲስ ቆጶሳችሁ ጋር እንድትማከሩ፣ ንሰሃ እንድትገቡ፣ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጥያት ክፍያ አማካኝነት ወደሚገኘው ወደ ሃያሉ የማዳን ሃይል ነፍሳችሁን እድትከፍቱ አነሳሳችኋለው።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ለእኛ ያለውን ሁሉ እናገኝ ዘንድ ቃል ኪዳኖችን አፍቃሪው የሰማይ አባታችን ሰጥቶናል። እነዚህ ከእግዚያብሔር የሚመጡ ቅዱስ በረከቶች ከየትኛውም ምድራዊ ፍሬ ይበልጥ ጣፋጭ ናቸው። ለቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖቻችንን ታማኝ ስንሆን፣ የሚዘልቅ ፍሬ በመሆን፣ ለእኛ ለዘላለም ሊቆዩ ይችላሉ።

በሰማይ የታተመ እንዲሆን በምድር የማተም ስልጣንን እግዚያብሔር እንደመለሰ እመሰክራለሁ። ያ ስልጣን የሚገኘው በየኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። ይህ ስልጣን ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት አላቸው እናም በፕሬዘዳንት ረስል ኤም ኔልሰን አመራር ስር ይተገበራል። ወደ አዲሱ እና ዘላለማዊ የጋብቻ ቃልኪዳን ውስጥ የሚገቡ እና ቃልኪዳኑን የሚጠብቁ ፍጹማን ይደረጋሉ እንዲሁም ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ሁኔታዎች ቢኖሩም እንኳ፣ የአብን የክብር ሙሉነት በሂደት ይቀበላሉ።

ቃል ኪዳኖቻችንን አስመልክቶ ያሉት እነዚህ የቃልኪዳን በረከቶች በቃልኪዳኑ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ ሊታተሙ እና ለዘላለም “ዘላቂ ፍሬ” መሆን ይችላሉ። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ዮሐንስ 15፥16

  2. ዴል ጂ. ረንለንድ፣ “በቃልኪዳኖች የእግዚያብሔር ሃይልን ማግኘት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)፣ 35-38፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥7ይመልከቱ።

  3. ቅዱስ ስርአት የሚታተመው ስልጣን ባለው በመከናወኑ እና በቅዱስ መንፈስ በመረጋገጡ ምክንያት በሰማይ እና በምድርም ትክክለኛ ሲደረግ ነው።

    “የማተም ስልጣን በቤተመቅደስ ቅዱስ ስርአቶች ብቻ እንደሚተገበር እናስባለን፣ ነገር ግን ያ ስልጣን ማንኛውንም ቅዱስ ስርአት ትክክል እና ከሞት በላይ የሚያትም ለማድረግ አስፈላጊ ነው። የማተም ሃይል በጥምቀታችሁ ላይ የማተምን ማረጋገጫ ይሰጣል፣ ለምሳሌ፣ እዚህ እና በሰማይ እንዲታወቅ ያደርጋል። በመጨረሻም፣ ሁሉም የክህነት ስነስርዓቶች የሚከናወኑት በቤተክርስቲያኑ ፕሬዘደንት ቁልፎች ስር ነው፣ እና ፕሬዘደንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ እንዳብራሩት፣ ‘እሱ (የቤተክርስቲያኑ ፕሬዘደንት) ስልጣን ሰጥተውናል፣ በእኛ ክህነት ውስጥ የማተም ሀይልን አድርጓል፣ ምክንያቱም እነዚያን ቁልፎች ይዟል” [ዲ ቶድ ክሪስቶፈርሶን፣”የማተም ሃይል፣” ሊያሆና፣ ህዳር፣ 2023 (እ.አ.አ)]።

    “በቃል ኪዳን መንፈስ ቅዱስ የታተመ ድርጊት በመንፈስ ቅዱስ የተረጋገጠ እንዲሁም በጌታ የተፈቀደ ነው። ማንም ለመንፈስ ቅዱስ ለመዋሸት እና ለማምለጥ አይችሉም። … እነዚህ መርሆዎች ደግሞም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አሉት ለእያንዳንዱ ስርዓቶች እና ድርጊቶች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ስለዚህ ሁለቱም ወገኖች [በትዳር ውስጥ] ‘ጻድቅ እና እውነተኛ’ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 17፥53] ከሆኑ፣ ብቁ ከሆኑ፣ በቤተ መቅደስ ጋብቻቸው ላይ የማጽደቅ መታተም ይደረጋል፤ ብቁ ካልሆኑ፣ በመንፈስ አይደገፉም እና የመንፈስ ቅዱስ ማጽደቅ ይገደባል። ቀጣይነት ያለው ብቁነት መታተምን ያጸናል እናም ጻድቅ አለመሆን የትኛውንም መታተም ይሰብራል” (ብሩስ አር. መካንኪ፣ “የቃልኪዳን ቅዱስ መንፈስ፣” in Preparing for an Eternal Marriage Student Manual [2003]፣ 136)።

    ቅዱስ የቃል ኪዳን መንፈስ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ እርሱም በሁሉም ስርዓቶች፤ በጥምቀት፣ በማረጋገጫ፣ በመሾም፣ በጋብቻ ላይ የማረጋገጫ መሃተምን የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው። ተስፋው በታማኝነት ምክንያት በረከቶች እንደሚመጡ ነው። አንድ ሰው በጥምቀት፣ በሹመት፣ በጋብቻ ወይም በሌላ ነገር ቃልኪዳኑን ቢያፈርስ፣ መንፈሱ የማረጋገጫ ማህተሙን ያነሳል፣ እናም በረከቶቹ አይቀበልም። በታማኝነት ላይ በተመሰረተ የሽልማት ቃልኪዳን እያንዳንዱ ስርአት ታትሟል። ቃል ኪዳኖች በሚፈርሱበት ቦታ መንፈስ ቅዱስ የማረጋገጫ ማህተም ይነሳል” (ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ፣ Doctrines of Salvation, comp. ብሩስ አር. መኮንኪ [1954 (እ.እ.እ)]፣ 1:45)።

  4. ራሴል ኢም. ኔልሰን፣ የልብ ጉዳዮች፤ 100 አመታት ህይወት ያስተማረኝ (2023)፣ 15። ሁሉም ቃልኪዳኖች በመንፈስ ቅዱስ ቃል መታተም አለባቸው፣ ከሙታን ትንሳኤ በኋላ ፍቱነት እንዲኖራቸው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥7 ይመልከቱ)።

  5. ራስል ኤ. ኔልሰን፣ “Celestial Marriage፣Liahona፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 94።

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥19።

  7. ትምህርት እና ቃል ኪዳን 84፥38 ይመልከቱ።

  8. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፥1-4

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥19–20 ይመልከቱ። “ያ ከፍተኛ መድረሻ—በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ከፍ ከፍ መደረግ—የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትኩረት ነው” [ዳለን ኤች ኦክስ፣ “የመንግስቶቹ ክብር፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)]።

  10. ትዳር እና ቤተሰብ ልዩ ፍቅርን የሚፈጥር የተለየ የጎንዮሽ ትስስር እንደሚጋሩ ሁሉ፣ እኛም በአዲስ እና በዘላለማዊ ቃልኪዳን ከአምላካችን ጋር ከታች ወደ ላይ ስንተሳሰር የሚፈጠረው አዲስ ግንኙነትም እንዲሁ ነው” (ራስል ኤም. ኔልሰን፣ የልብ ጉዳይ፣ 41-42።

  11. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥22አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ-በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል38.6፣16። ስለ ጋብቻ ስናገር፣ ጋብቻን በአምላክ ሕግ መሠረት በማመልከት ነው፣ እሱም ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ያለው ሕጋዊ ውህደት ነው (“ቤተሰብ፤ አዋጅ ለአለም፣” የወንጌል መዛግብት ይመልከቱ)።

  12. ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” የወንጌል ቤተመጻህፍትን ይመልከቱ።

  13. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥22-24፣ ይመልከቱ።

  14. Dallin H. Oaks, “Kingdoms of Glory,” 29; emphasis added.

  15. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 86፥8–11 113፥8አብርሐም 2፥9–11 ይመልከቱ።

  16. አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ38.4.1 ይመልከቱ።

    የሙሉ ጊዜ ሚስዮን በስዊዘርላንድ እያገለገልኩ ሳለሁ፣ እኔና ጓደኛዬ ለ60 አመት እድሜ ላላቸው የስዊዘርላንድ ባልና ሚስት ወንጌሉን አካፍለን ነበር። እነዚህን ባልና ሚስት ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ስናስተምር ሴትየዋ ለምናስተምረው ነገር ከፍተኛ ፍላጎትን አሳየች። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ትክክለኛ ስልጣን እንደገና እንደተመለሰች፣ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን በህያው ነቢያት እና ሐዋርያት እንደሚመራው ምስክርነት አገኘች። እነዚህን ባልና ሚስት ስለ የመመለስ በጣም የላቁ ትምህሮቶችን ማለትም ስለ ዘላለማዊ ጋብቻ እድልን ለማስተማር እንጓጓ ነበር። በሚገርም ሁኔታ፣ ለእነዚህ ጥንዶች ስለ ዘላለማዊ ጋብቻ ትምህርት ስናስተምር ስዊዘርላንዳዊቷ ሴት ከባለቤቷ ጋር ለዘላለም የመኖር ፍላጎት እንደሌላት ተናገረች። ለእሷ፣ ለ36 ዓመታት በትዳር ውስጥ ከኖረችው ባሏ ጋር አብሮ መሆን መንግሥተ ሰማያትን አያካትትም። ይህች እህት ተጠምቃ ነበር፣ ነገር ግን ባሏ አልተጠመቀም፡፡ በቤተመቅደስ ውስጥ ፍጽሞ አልታተሙም።

    ይሁን እንጂ፣ ለብዙዎች፣ ካገቡት ሰው ጋር አብረው የማይሆኑ ከሆነ ሰማይ መንግስተ ሰማይ አትሆንም። ከምትወዷቸው ባለቤታችሁ ጋር ለዘላለም አብሮ መሆን በእውነት መንግስተ ሰማይን ይመስላል። ሽማግሌ ጄፍሪ ሆላንድ ስለ ውዷ፣ ተወዳጅ ሚስቱ፣ ፓት እንዳካፈለ፣ ያለሷ ገነት ሰማይ አይሆንም (“Scott Taylor: For Elder Holland, Heaven without His Wife and Children ‘Wouldn’t Be Heaven for Me,’” Church News, July 22, 2023 እ.አ.አ ይመልከቱ)።

  17. See Dallin H. Oaks, “Kingdoms of Glory,” 26.

  18. Russell M. Nelson, “Celestial Marriage,” 94.

  19. ዮሀንስ 15፥16 ይመልከቱ።