የእግዚአብሔር ሀሳብ እናንተን ወደ ቤቱ ማምጣት ነው።
አብ ለውድ ልጆቹ ያለው እቅድ ሁሉ የተነደፈው ሁሉንም ወደ ቤት ለመመለስ ነው።
በፕሬዚዳንት ኔልሰን በኩል እንደጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ በመሆን እንዳገለግል በተጠራሁበት የመለማመድን ሂደት ስጀምር፣ ለጸሎቶቻችሁ ምስጋናዬን ልገልጽ እወዳለሁ። ይህም እንዴት ትሁት እንደሚያደርግ ልትገምቱ ትችላላችሁ፣ እንዲሁም እጅግ የተለየ የግራ መጋባት እና በእርጋታ ራስን የመመርመሪያ ጊዜ ነበር። በእርግጥም በየትኛውም የአገልግሎት ደረጃ አዳኛችንን ማገልገል እና የእርሱን የተስፋ ወንጌል ለማካፈል ከእናንተ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ ክብር ነው።
ከዚያም በላይ፣ እንደሚባለው ከእያንዳንዱ አዲስ ሐዋርያ ጀርባ የተገረመችች አማት አለች። በእርግጥ እንደዚያ ተብሎ እንደሆነ አላውቅም፣ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ በእርግጠኝነት ተገርማለች። አማቴ አሁን ከእኛ ጋር ያለመሆንዋ እውነታ አግራሞቷን ሊቀንሰው እንደማይችል አልጠራጠርም።
ከአያሌ ወራት በፊት እኔና ባለቤቴ ለተለያዩ የቤተክርስቲያን የስራ ምደባዎች ሌላ አገር እየጎበኘን በነበርንበት ወቅት አንድ ቀን ማልጄ ተነሳሁ፣ እናም በሆቴላችን መስኮት በድንግዝግዝ ተመለከትኩ። ቁልቁል በተጨናነቀው መንገድ ላይ፣ መኪኖች ወደ ምልክቱ ሲደርሱ አዙረው እንዲመለሡ ለማድረግ አጠገቡ ፖሊስ የቆመበት መሠናክል እንደተቀመጠ ተመለከትኩ። በመጀመሪያ በመንገዱ ላይ ይታዩ የነበሩት ጥቂት መኪኖች ብቻ ነበሩ እነርሱም እንዲመለሱ ተደርገዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን የመኪኖች እንቅስቃሴ በጨመረ ቁጥር ሰልፉ እየጨመረ ሄደ።
ከመስኮቱ በላይ በኩል፣ የትራፊክ ፖሊሱ የትራፊክ እንቅስቃሴውን የማገድ እና ሰዎቹንም ከዚያ የመመለስሥልጣን የነበረው በመሆኑ እርካታ የተሰማው እንደሚመስል ተመለከትኩኝ። በእርግጥም፣ እያንዳንዱ መኪና የዝግ መንገድ ምልክት ወዳለበት ሲቀርብ መጠነኛ ዳንስ እየጀመረ ያለ ይመስል በእርምጃዎቹ ነጠር ነጠር ማለት ያዘ። በመሰናክሉ ምክንያት አንድ ሾፌር ቢበሳጭ፣ ፖሊሱ የሚረዳም ሆነ የሚራራ አይመስልም ነበር። በተደጋጋሚ ጭንቅላቱን ይነቀንቅ እና ወደ ዞረው እንዲመለሡ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ያመለክት ነበር።
ውድ ጓደኞቼ፣ በሟች ህይወት መንገድ ላይ ያላችሁ የደቀመዝሙርነት ጓዶቸ፣ የአባታችን ወብታማ እቅድ፣ እንዲሁም የእርሱ “አስገራሚ” እቅድ፣ እናንተን ወደ ቤት ለመለለስ የተነደፈ ነው እንጂ ከእዚያ ውታችሁ እንድትቀሩ የሚያደርግ አይደለም። ማንም ሊመልሳችሁም ሆነ ሊያባርራችሁ የገነባ እና በዚያ የቆመ ሠው የለም። በእርግጥም የዚያ ተቃራኒ ነው። እግዚአብሔር ያለማቋረጥ ከእናንተ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይፈልጋል። እርሱ ሁሉም ልጆቹ ወደ እርሱ መመለስን እንዲመርጡ ይፈልጋል፣ ስለዚህም ወደ እርሱ እንድትመለሡ ለመርዳት የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል።
የሚወደን አባታችን እርሱን እንድንመርጥ መለኮታዊ ስጦታ የሆነውን የመምረጥ ነጻነት እድላችንን ለመጠቀም፣ ለመማር፣ ለማደግ፣ ስህተትን ለመስራት፣ ንሰሃ ለመግባት፣ እግዚአብሔርን እና ባልንጀሮቻችንን እንድንወድ፣ እና አንድ ቀን ወደቤታችን ወደ እርሱ እንድንመለስ ከምቾት ክልላችን የምንወጣበትን እና የተሻልን ሠዎች የምንሆንሆንበትን ምድራዊ ልምምዶችን የምናደርግበት እንዲኖረን፣ ለእኔ እና ለእናንተ ለዚህ ልዩ አላማ ሲል የዚችን ምድር መፈጠር ተቆጣጥሯል።
የሰውን ዘር የህይወት ልምምዶች በህይወቱ እንዲካፈል፣ ልጆቹም ሁሉ የእርሱን ምሳሌ እንዲከተሉ፣ እና ለኃጥያታቸው ዋጋ እንዲከፍል እና ቤዣቸው እንዲሆን፣ ወድ አንድያ ልጁን ወደዚህች ወደወደቀች ዓለም ላከው። የክርስቶስ ታላቅ የኃጥያት ክፍያ ስጦታ ከዘለዓለማዊው ቤታችን ሊለየን የሚችለውን ማንኛውንም የስጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሞት መሰናክል ያስወግዳል።
አብ ለውድ ልጆቹ ያለው እቅድ ሁሉ የተነደፈው ሁሉንም ወደ ቤት ለመመለስ ነው።
የእግዚአብሔር መልእክተኞች የሆኑት ነቢያቱ፣ በዳግም መመለስ ቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ይህንን እቅድ ምን ብለው ይጠሩታል? የቤዛነት እቅድ፣ የምህረት እቅድ፣ ታላቁ የደስታ እቅድ፣ እና “በአንድያ ልጄ ደም አማካይነት” ለሁሉ የተዘጋጀ የደህንነት እቅድ ብለው ይጠሩታል።
የአባታችን ታላቁ የደስታ እቅድ አላማ እዚህ እያለን፣ አሁን፣ እና በዘለዓለማዊነት ውስጥ ደስተኞች እንሆን ዘንድ ነው። ደስታ እንዳታገኙ ለማድረግ እና የጭንቀት እንዲሁም የፍርሀት ምክንያት እንዲሆንባችሁ አይደለም።
በእርግጥም የአባታችን የቤዛነት እቅድ አላማው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ እና ሞት አማካይነት መዳን፣ እንዲሁም ከኃጥያት እና ከሞት ባርነት ነፃ መሆን ነው። እንዲሁ እንዳላችሁ ሊተዋችሁ አይደለም።
የአባታችን የምህረት እቅድ አላማ ወደ እርሱ በምትመለሱበት ጊዜ እና ለእርሱ ያለችሁን የታማኝነት ቃል ኪዳን በምታከብሩበት ጊዜ ምህረትን መስጠት ነው። ምህረትን ሊነፍገን እና ህመምን እና ስቃይን ሊያስከትልብን አይደለም።
የአባታችን የደህንነት እቅድ አላማ፣ በእርግጥም በሰለስቲያል ክብር መንግስት ውስጥ ደህንነት የምታገኙት የኢየሱስን ምስክርነት ስትቀበሉ እና ሙሉ ነፍሳችሁን ለእርሱ ስትሰጡ ነው። በውጪ ሊያስቀራችሁ አይደለም።
ይህ ማለት ህይወታችንን በምንኖርበት መንገድ ሁሉም ነገር ተቀባይ ነው ማለት ነውን? የመምረጥ ነፃነታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ልዩነት አያመጣም ማለት ነውን? የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መቀበልም ሆነ መተው እንችላለን ማለት ነውን? አይደለም፣ በእርግጥም አይደለም። በወንጌላት ውስጥ እንደተዘገበው፣ በእርግጠኝነት በምድር አገልግሎቱ የኢየሱስ ያልተቋረጠ ግብዣ እና ተማፅኖ፣ እንድንለወጥ እና ንስሀ እንድንገባ እንዲሁም ወደ እርሱ እንመጣ ዘንድ ነበር። በትምህርቶቹ ሁሉ በመሠረታዊነት በተዘዋዋሪ መንገድ ከፍ ያለ ግብረገባዊ ባህርይ እንድንኖር የሚያስተምረን፣ የግል እድገት እንድናሣይ፣ በክርስቶስ ለውጥን የሚያመጣ እምነት እንዲኖረን እና ታላቅ የልብ ለውጥ እንድናደርግ ጥሪ ለማስተላለፍ ነው።
እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው ከራስ ወዳድ እና ትዕቢተኛ ግፊት ለመላቀቅ የለውጥ እንቅስቃሴን እንድናደርግ፣ ፈጥሮአዊውን ሰው አስወግደን “ሂድ፣ ደግመህ ኃጥያት አትስራ” ባለው መሠረት እንድንኖር ነው።
የአባታችን ሁሉን አቀፍ እቅድ ሊያድነን፣ ሊቤዠን፣ ምህረትን ሊሰጠን እና በዚህም ደስታን ሊያመጣልን እንደሆነ የምናምን ከሆነ፣ ይህ ታላቅ እቅድ በእርሱ አማካኝነት እንዲመጣ ያደረገው የልጁ አላማስ ምንድን ነው?
ወልድ እራሱ እዲህ ነግሮናል፦ “ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።”
የኢየሱስ ፈቃድም ደግ የሆነው የአብ ፈቃድ ነው። ሁሉም የአባቱ ልጆች የእቅዱ የመጨረሻ ግብ የሆነውን ከእርሱ ጋር ለዘለዓለም የመኖር ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ይፈልጋል። ከዚህ መለኮታዊ ችሎታ ማንም የተገለለ አይደለም።
መቼም አንለካም ወይም የክርስቶስ ወሰን የሌለው የኃጥያት ክፍያ ፍቅራዊ ተደራሽነት ሌላውን ሁሉ ይሸፍናል እንጂ እኔን የሚሸፍን አይደለም ብላችሁ ለጭንቀት ከተጋለጣችሁ፣ እናንተ አልተረዳችሁም ማለት ነው። ወሰን የሌለው ማለት ወሰን የሌለው ማለት ነው። ወሰን የሌለው እናንተን እና የምታፈቅሯቸውንም በሙሉ ይሸፍናል።
ኔፊ ይህንን ውብ እውነት እንዲህ አብራርቷል፦ “እርሱም ለዓለም ጥቅም ካልሆነ በስተቀር ማንኛውንም አያደርግም፤ ምክንያቱም ሰዎችን ሁሉ ወደ እርሱ ይስብ ዘንድም ሕይወቱን አሳልፎ እስከመስጠት ዓለምን ይወዳል። ስለዚህ፣ ማንንም ደህንነቱን እንዳይካፈሉ አያዝም።”
አዳኙ፣ መልካሙ እረኛ፣ እስከሚያገኛቸው ድረስ የጠፉትን በጎቹን ፍለጋ ይሄዳል። ከእነርሱ አንዳቸውም ይጠፉ ዘንድ አይፈቅድም።
“እነሆ የምህረት ክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ።”
“ከእናንተ መካከል በሽተኞች አሉን? ወደዚህ ስፍራ አምጧቸው። ከእናንተ መካከል ድውይ፣ ወይም አይነ ስውር፣ ወይም ሽባ፣ ወይም ለምፃም፣ ወይም ሰውነታቸው የሰለለ፣ ወይም ደንቆሮ፣ ወይ በተመሳሳይ የሚሠቃዩ አሉን? ወደዚህ ሥፍራ አምጧቸው፣ እናም ለእናንተ ከአንጀቴ ርህራሄ ስላለኝ እፈውሳቸዋለሁ።”
የደም መፍሰስ ችግር ያለባትን ሴት አላገለላትም፣ ከለምፃሙም ሰው ሊርቅ አልወደደም፣ ስታመነዝር የተያዘችውንም ሴት አላወገዛትም፣ ህመምተኞችን አልተቃወመም፣ ምንም ኃጥያተኞች ቢሆኑም ንስሀ የገቡትን አላስወገደም። የተሰበረ ልባችሁን እና የተዋረደ መንፈሳችሁን ይዛችሁ በመጣችሁ ጊዜ እናንተንም ሆነ የምትወዷቸውን አያገልልም። ያ የእርሱ ግብ ወይም ንድፍ ወይም የእርሱ እቅድ፣ ዓላማ፣ ምኞት ወይም ተስፋ አይደለም።
አይደለም፣ እርሱ መሰናክልን እና ማገጃን አያኖርም፣ ያስወግዳቸዋል እንጂ። እርሱ ወደ ውጭ አያስወጣችሁም፣ ትገቡ ዘንድ መልካም አቀባበል ያደርግላችኋል እንጂ። መላ አገልግሎቱ የዚህ ዓላማ እውነተኛ መግለጫ ነው።
ከዚያም በእርግጥ፣ ለመረዳት አዳጋች የሆነው እንረዳውም ዘንድ ከስጋዊ አቅማችን በላይ የሆነው የእርሱ የኃጥያት ክፍያ መስዋዕትነትም አለ። ነገር ግን፣ ይህ አስፈላጊ “ነገር ግን፣” ነው፣ ይህን ለኃጥያት የተከፈለ መስዋዕትነት ቅዱስ የደህንነት ዓላማ እንረዳዋለን፣ ልንረዳውም እንችላለን።
ኢየሱስ በመስቀል በሞተ ጊዜ፣ የቤተመቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ፣ ይህም ወደ እርሱ ለሚመለሱት፣ ለሚያምኑት፣ ሸክማቸውንም በእርሱ ላይ ለሚጥሉ፣ በቃል ኪዳኑ ግንኙነት አማካይነት ቀንበሩን በላያቸው ለሚሸከሙት ሁሉ ወደ አብ የሚወስደው መንገድ በሰፊው የመከፈቱ ተምሣሌት ነው።
በሌላ አባባል የአብ እቅድ ስለ መሰናክል አይደለም። ሆኖም አያውቅም ወደፊትም አይሆንም። ልናደርጋቸው የሚገቡን ነገሮች፣ ልንጠብቃቸው የሚገቡን ትዕዛዛት፣ ከማንነታችን ሊቀየሩ የሚገቡ ነገሮች አሉን? አዎን። ነገር ግን በፀጋው ምክንያት ከእኛ የራቁ ሳይሆን ልንደርስባቸው የምንችላቸው ነገሮች ናቸው።
መልካም ዜናው ይህ ነው! ስለእነዚህ ቀላል እውነቶች ሊነገር በማይችል ሁኔታ አመስጋኝ ነኝ። የአብ ንድፍ፣ የእርሱ እቅድ፣ የእርሱ አላማ፣ የእርሱ ሀሳብ፣ የእርሱ ምኞት እና የእርሱ ተስፋ ትፈወሱ ዘንድ ነው፣ ሠላምን ይሰጣችሁ ዘንድ ነው፣ እንዲሁም ወደ ቤት ይመልሳችሁ ዘንድ ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።