በማደግ ላይ ያለውን ትውልድ መደገፍ
በምርጫዎቻቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ያለው፣ በወጣቶቹ ህይወት ውስጥ ያሉት ግንኙነቶች ናቸው።
ለእናንተ ንግግርን ለማቅረብ በምዘጋጅበት ወቅት፣ በሔለማን እና በአሞናውያን ሰዎች ብላቴና ወንድ ልጆች ታሪክ ተስቤ ነበር። ይህንን መዝገብ በማጥናት የመጽሐፈ ሞርሞን ነቢያት ወላጆችን፣ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ እና የአጥቢያ አባላትን የማስተማር ሃይል ሊሰማኝ ችሏል።
ሔለማን፣ ወጣት አሞናውያን ሊያምኑት የሚችሉት ሰው ነበር። በጽድቅ እንዲያድጉ እና አዋቂ እንዲሆኑ ረዳቸው። ያውቁትና ይወዱት ነበር እንዲሁም “[እሱ] መሪያቸው እንዲሆን ይፈልጉ ነበር።”
ሔለማን እነዚህን ወጣት ወንድ ልጆች እንደ ልጆቹ ይወዳቸውና አቅማቸውን ያውቅ ነበር። ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንለንድ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “ሌሎችን በውጤታማ ሁኔታ ለማገልገል በሰማይ አባት አይኖች ልንመለከታቸው ይገባል። በዚያ ጊዜ ብቻ ነው የነፍስን እውነተኛ ዋጋ መረዳት የምንጀምረው። የሰማይ አባት ለሁሉም ልጆቹ ያለው ፍቅር ሊሰማን የሚችለው በዚያ ጊዜ ብቻ ነው።” ዛሬ ኤጲስ ቆጶሳት በጥበቃቸቸው ስር ያሉትን ወጣቶች መለኮታዊ ማንነት ለመመልከት በሚያስችላቸው የማስተዋል ስጦታ ተባርከዋል።
ሔለማን በእርሱ ጥበቃ ስር የነበሩትን ወጣት ልጆች “ቆጠራቸው” ከእነርሱ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መገንባትን ቅድሚያ ይሰጥ ነበር።
የሕይወትና የሞት ጉዳይ በሆነበት ጊዜ ሔለማንና ወጣቶቹ ተዋጊዎች ያሳድዷቸው የነበሩትን ተዋጊዎች አመለጧቸው። ሔለማን ከወጣቶቹ ጋር ተመካከረ፦
“እነሆ፣ በወጥመዳቸው እስከሚይዙን ወደ እነርሱም እንድንመጣ ዘንድ ቆመው እንደሆነ አናውቅም። …
እነዚህ አማኝ ወጣት ወንዶች እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “አባታችን፣ እነሆ አምላካችን ከእኛ ጋር ነው፤ እናም እንድንወድቅ አይፈቅድም፤ ስለዚህ [እንሂድ] ።” ሔለማን እነዚህ ወጣት ወንድ ልጆች ያሣለፉትን ውሳኔ እንዲተገብሩ በረዳቸው ጊዜ ቀኑን አሸንፈው ነበር።
ወጣቶቹ አሞናውያን ታላቅ ምክንያት ነበራችው እናም “በሰዎቹ ድጋፍ ምክንያት” ጀግኖች ነበሩ። በሔለማን ይመራ የነበረው “ይህ ትንሹ ሃይል”፣ ተሞክሮ በነበራቸው የኔፋዊያን ሰራዊት ልብ ውስጥ “ታላቅ ተስፋን እና ብዙ ደስታን” አምጥቶ ነበር። ዛሬ ኤጲስ ቆጶሳት በተለየ መልኩ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች፣ አጥቢያውን እንዲባርኩ እና እስራኤልን እንዲሠበሥቡ መምራት ይችላሉ። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ይህ “[እነሱ] ወደ ምድር የተላኩበት ተልእኮ” እንደሆነ አስተምረዋል።
ሔለማን፣ “በሁሉም ጊዜ በተሰጣቸው በማንኛውም ነገር ታማኝ” እንደነበሩት ልክ እንደነዚህ አሞናውያን፣ በታማኝነት መሪዎቹን ተከተለ። ተግዳሮቱ ወይም ፈተናው ምንም ይሁን ምን ሔለማን አላማቸውን ለማሳካት ሁልጊዜ “ድፍረትን አገ[ኘ]”። “ከትንንሽ ልጆ[ቹ] ጋር እንዲዘምት” መመሪያ ሲሰጠው ታዟል።
ኤጲስ ቆጶሳት “ከአጥቢያው የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንቶች ጋር በመወያየት፣” የመሪዎቻችንን ምሪት በመከተላቸው የዛሬ ወጣቶች ተባርከዋል። የካስማ ፕሬዚዳንቶች ኤጲስ ቆጶሳትን እና የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንቶችን የወጣቶችን ሃላፊነት እንዲያሟሉ መመሪያ እንደሚሰጣቸው ያረጋግጣሉ።
ሔለማን ቃል ኪዳኖችን አከበረ። አሞን የብላቴና ወንድ ልጆችን ወላጆች ወንጌልን ሲያስተምራቸው፣ እነዚህ ወላጆች ይህን በተከፈተ ልብ ተቀበሉት። አዲስ ለሆነው የጽድቅ ደቀመዝሙርነት ህይወታቸው የተሰጡ ከመሆናቸው የተነሳ “የአመጽ መሳሪያቸውን ለመጣል ቃል ገቡ።” ይህንን ቃል ኪዳን ጥሶ የድሮ የጦርነት መንገዳቸው ወደሆነው መመለስን ታሳቢ እንዲያደርጉ ያደረጋቸው ብቸኛው ነገር ኔፋዊያንን በአደጋ ውስጥ ማየታቸው ነበር።
አሞናዊያን ደህንነቱ የተጠበቀ ቤትን ለሰጧቸው ለእነዚህ ሰዎች እርዳታ ማድረግን ፈልገው ነበር። ሔለማን፣ ከሌሎቹ ጋር በመሆን፣ መቼም ላለመዋጋት የገቡትን ቃል ኪዳን እንዲጠብቁ አሳመናቸው። እነዚህ አሞናውያን በሰይፋቸው እና በቀስቶቻቸው ሊሰጡ ይችሉ ከነበረው ጥንካሬ ይልቅ እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ይችል በነበረው ጥንካሬ ላይ ይበልጥ ተማምኖ ነበር።
ሔለማን እና ወጣት ተዋጊዎቹ አስፈሪ መከራዎች በገጠማቸው ጊዜ፣ ሔለማን ቆራጥ ነበር። “ነገር ግን እነሆ ይህ ምንም ማለት አይደለም— እግዚአብሔር እንደሚያድነን እናምናለን።” አንድ ጊዜ፣ እስከ ሞት በሚያደርስ ረሃብ በነበሩበት ጊዜ፣ መልሶቻቸው፣ “እግዚአብሔር እንዲያበረታቸው እና፣ እንዲያድ[ናቸው] በጸሎት ነፍሳቸውን ማፍሰስ ነበር፤ … [እናም] ጌታም እንደሚያድናቸው ማረጋገጫን በመስጠት ጎበ[ኛቸው]”፣ “ይህም የሆነው እንዲያምኑ በተማሩት ታላቅ እምነት የተነሣ ነው።”
እነዚህ ወጣት ወንዶች በወላጆቻቸው ተደግፈው እንደነበር ከሔለማን እንማራለን። እነዚህ ታማኝ ወላጆች ዋና ሃላፊነታቸው ልጆቻቸውን ማስተማር እንደነበረ ያውቁ ነበር። ልጆቻቸው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዲጠብቁና በፊቱም በቅንነት እንዲራመዱ አስተማሯቸው፡፡ እናቶቻቸው፣ የማይጠራጠሩ ከሆነ እግዚአብሔር እንደሚያድናቸው አስተምረዋቸው ነበር። አባቶቻቸው ቃል ኪዳን የመግባት ሃያል የሆነ ምሳሌን ትተውላቸው ነበር። እነዚህ የቀድሞ ተዋጊዎች የጦርነትን አሰቃቂ ሁኔታዎች ያውቁ ነበር። ተሞክሮ የሌላቸው ወንድ ልጆቻቸውን በሔለማን ጥበቃ ስር እንዲሆኑ እምነታቸውን ጣሉ እንዲሁም “ብዙ ስንቆችን” በመላክ ረዷቸው።
ሔለማን ወጣት ወንድ ልጆቹን ባገለገለበት ጊዜ ብቻውን አልነበረም። እርዳታ እና ምሪት የሚጠይቃቸው ሰዎች በዙሪያው ነበሩት። ካፒቴን ሞሮኒን እርዳታ እንዲያደርግለት ጠይቆት ነበር፣ እርዳታውንም መጣለት።
በጌታ መንግስት እያገለገለ ያለ ማንኛውም ሰው ብቻውን አያገለግልም። ጌታ በአጥቢያዎች እና በካስማዎች ባርኮናል። በእርሱ ዳግም በተመለሰ ድርጅት አማካኝነት፣ ማንኛውንም ተግዳሮት ለመጋፈጥ፣ ሃብቱ፣ ጥበቡ፣ እና ተነሳሽነቱ አለን።
ኤጲስ ቆጶስ በቡድኖች በኩል ለአጥቢያዎች መመሪያ ይሰጣል። በየሩብ ዓመቱ የአገልግሎት ቃለ መጠይቆች እንዲካሄዱ ይረዳል ከዚያም የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማሕበር ቤተሰቦችን የማገልገል ሃላፊነታቸውን እንዲያሟሉ ያበረታታል። እነዚህ አመራሮች ፍላጎቶችን በመገምገም እና በመንፈሥ የተነሣሡ መፍትሄዎችን በማግኘት ዙሪያ ግምባር ቀደም ይሆናሉ። የካስማ አመራሮች የሽማግሌዎች ቡድንን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን አመራሮች ስለእነዚህ ሃላፊነቶች በማስተማር ድጋፍ ይሠጣል።
ለመሪዎች እና ለወላጆች የሚያስፈልጓቸው መመሪያዎች በወንጌል ላይብረሪ እና በGospel Living apps መተግበሪያዎች ውስጥ ይገኛሉ። በእነዚህ በመንፈሥ የተነሣሡ ግብዓቶች ውስጥ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን፣ የአሁን ዘመን ነቢያት አስተምህሮዎችን እና የአጠቃላይ መመሪያ መጽሐፍን ልናገኝ እንችላለን። በወንጌል ላይብረሪ ውስጥ የሚገኘው የወጣቶች ማውጫ[youth tab] ለቡድን እና ለክፍል አመራሮች ብዙ ግብአቶች አሉት፣ እንዲሁም ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን የማድረግ መመሪያ ይገኝበታል። ሁሉም የአጥቢያው አባላት እነዚህን በመንፈሥ የተነሣሡ ግብአቶች፣ ሲያጠኑ እና ከመንፈስ ቅዱስ ምሪትን ሲፈልጉ፣ ወጣቶችን በማጠናከር ረገድ ሁሉም ከጌታ ምሪትን መቀበል ይችላሉ።
እንዲሁም አባላት እያደገ ባለው ትውልድ ላይ ባተኮሩ ጊዜ መላው አጥቢያ ይጠናክራል እንዲሁም ይባረካል። ጉድለቶቻችን እና ድክመቶቻቻን እንዳሉ ሆነው፣ የሰማይ አባታችን፣ በመንፈስ ቅዱስ አጋርነት በኩል ሌሎችን እንድንረዳ እያንዳንዳችንን ጋብዞናል። የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ስንከተል እንደምናድግ እና ንጹህ እንደምንሆን ያውቃል። ጥረቶቻችን ፍጹም አለመሆናቸው ችግር የለውም። ከጌታ ጋር ስንጣመር፣ ጥረቶቻችን እርሱ ለወጣቶች ሊያደርገው ከሚችለው ነገር ጋር እንደሚስማሙ ማመን እንችላለን።
ወጣቶቹን በመርዳት አኳያ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን መመሪያ በመከተል፣ በህይወታቸው ውስጥ የሰማይ አባት ፍቅር ምስክሮች እንሆናለን። ከጌታ የሚመጡ ምሪቶችን መተግበር የፍቅር እና የመተማመን ግንኙነቶችን ይገነባሉ። በምርጫዎቻቸው ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያላቸው፣ በወጣቶቹ ህይወት ውስጥ ያሉት ግንኙነቶች ናቸው።
ሌሎችን ስለማገልገል የሚሰጡ የመንፈሥ ምሪቶችን በመፈለግ እና በመተግበር ሂደት ላይ ከእኛ ጋር ሲሳተፉ ወጣቶች የራዕይን ቅደም ተከተል ይማራሉ። ወጣቶቹ ይህን በመንፈሥ የተነሣሣ ምሪት እንዲያገኙ ጌታን ሲጠይቁ፣ ከእርሱ ጋር ያላቸው ግንኙነት እና እምነት ጠንካራ ይሆናል።
ሙሉ ለሙሉ ሳንቆጣጠራቸው እርዳታን እና መመሪያን በመስጠት በወጣቶች ላይ ያለንን እምነት እንገልጻለን። ያለ እኛ ተሣትፎ ወጣቶቹ አንድ ላይ በመመካከር እንዲማሩ በምንፈቅድበት ጊዜ፣ ተነሳሽነት ያለውን ትምህርት በመምረጥ እና እቅዳቸውን ተግባራዊ በማድረግ እውነተኛ የደስታ እና የእድገት ተሞክሮ ይኖራቸዋል።
ፕሬዚዳንት ሔንሪይ ቢ. አይሪንግ እንዲህ በማለት አስተምረዋል፦ “በጣም ወሳኝ የሆነው፣ እነርሱ በእውነትም ማን እንደሆኑ እና ምን መሆን እንደሚችሉ [ከእናንተ] መማራቸው ነው። የእኔ ግምት፣ ይህንን በቃል ከሚሰጡ ትምህርቶች ያን ያህል እንደማይማሩት ነው። ከእናንተ የማንነት፣ እነሱ ማን ናቸው ብላችሁ ከምታስቡት እና ማን ሊሆኑ ይችላሉ ብላችሁ ከምታስቡት ስሜቶች ያገኙታል።
ወጣቶቻችን በድፍረታቸው፣ በእምነታቸው እና በአቅማቸው ያስደንቁናል። ሙሉ በሙሉ የሚሳተፉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ለመሆን ሲመርጡ፣ የእርሱ ወንጌል በልባቸው ውስጥ ይቀረፃል። እርሱን መከተል ለማድረግ ያህል ብቻ የሚያደርጉት ነገር ሳይሆን የማንነታቸው አካል ይሆናል።
ሔለማን፣ ወጣት አሞናውያን፣ ደፋር የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር እንዴት እንደሚኖር መመልከት እንዲችሉ ረድቷቸዋል። ዛሬ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንዴት እንደሚኖሩ በማሳየት ለወጣቶች ብርቱ ምሳሌዎች መሆን እንችላለን። አማኝ ወላጆች በልጆቻቸው ህይወት ውስጥ እነዚህ ምሳሌዎች እንዲኖሯቸው እየጸለዩ ነው። ምንም አይነት ፕሮግራም የአፍቃሪ፣ ቃል ኪዳን ጠባቂ ጎልማሶችን ተጽዕኖ ሊተካ አይችልም።
የካህናት ቡድን ፕሬዚዳንት እንደመሆኑ፣ ኤጲስ ቆጶሱ፣ እንዴት ታማኝ ባል እና አፍቃሪ አባት መሆን እንደሚችሉ ለወጣቶች ምሳሌ በመሆን ጥበቃ በማድረግ፣ አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ እና በጽድቅ መንገዶች በመምራት ረገድ ሊያስተምራቸው ይችላል። ኤጲስ ቆጶሳት፣ ወጣቶች ላይ ጠንካራ ትኩረት በማድረግ፣ ለብዙ ትውልዶች የሚቆይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል።
የዛሬ ወጣቶች በጣም ክቡር ከሆኑት የሰማይ አባት መንፈሶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። በቅድመ ምድራዊ ህይወት ውስጥ ታማኝ የእውነት እና የነጻ ምርጫ ጠባቂዎች ነበሩ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው ጠንካራ ምስክርነት አማካኝነት እስራኤልን ለመሰብሰብ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ተወልደዋል። እያንዳንዳቸውን እንዲሁም ታላቅ አቅማቸውን ያውቃል። ዕድገት እያደረጉ በሚሄዱበት ጊዜ ይታገሣል። ያድናቸዋል እንዲሁም ይጠብቃቸዋል። ይፈውሳቸዋል እንዲሁም ይመራቸዋል። ያነሳሳቸዋል። እኛ ወላጆቻቸው እና መሪዎቻቸው እነርሱን ለመደገፍ ዝግጁ ነን። ቀጣዩን ትውልድ በምናሳድግበት ወቅት የምትረዳን የአዳኙ ቤተክርስቲያን አለችን።
በጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተመለሰችው፣ አሁን ደግሞ በፕሬዚዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን የምትመራው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች በነዚዚህ የኋለኞቹ ቀናት ታላቅ የሆነውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ለመርዳት የተመሰረተች እንደሆነ ምስክርነቴን አካፍላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።