ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪፥፱–፲፪። ከሉቃስ ፲፪፥፱–፲ ጋር አነጻፅሩ፤ ደግሞም ጆ.ስ.ት.፣ ማቴዎስ ፲፪፥፴፯–፴፰ እና ት. እና ቃ. ፻፴፪፥፳፮–፳፯ ተመልከቱ
ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን መስደብ እንደማይሰረይ ገለጸ።
፱ ነገር ግን እኔን በሰው ፊት የሚክደኝ፣ በእግዚአብሔር መላእክቶች ፊት ይካዳል።
፲ አሁን ደቀ መዛሙርቱ ይህን ያለው ስለእርሱ በሰዎች ፊት ክፉን ተናግረው ስለነበር እንደሆነ አወቁ፤ በሰዎች በፊት ስለእርሱ ለመመስከር ፈርተው ነበርና።
፲፩ እና እንዲህ በማለትም እርስ በራሳቸው እየተወያዩ አሉ፣ ልባችንን ያውቃል፣ እና ለኩነኔአችን ይናገራል፣ እና አይሰረይልንም። ነገር ግን እርሱ መለሳቸው፣ እና እንዲህም አላቸው፣
፲፪ በሰው ልጅም ላይ ቃል የሚናገር፣ እና ንስሀ የሚገባ፣ ሁሉ ይሰረይለታል፤ መንፈስ ቅዱስን የሚሰድብ ግን አይሰረይለትም።
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፪፥፵፩–፶፯። ከሉቃስ ፲፪፥፴፯–፵፰ ጋር አነጻፅሩ
ኢየሱስ አገልጋዮቹ ለእርሱ መምጣት ሁልጊዜም መዘጋጀት እንዳለባቸው ገለጸ።
፵፩ እነሆ በለሊቱ በመጀመሪያ ክፍል ይመጣልና፣ እና በሁተኛው ክፍልም ደግሞ ይመጣል፣ እና እንደገናም በሶስተኛው ክፍልም ይመጣል።
፵፪ እና እውነት እላችኋለሁ፣ ስለእርሱ እንደተጻፈውም አስቀድሞም መጥቷል፤ እንደገናም ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፣ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤
፵፫ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ይታጠቃል፣ እና ምግብ ለመመገብም ይቀመጣሉ፣ እና መጥቶም ያገለግላቸዋል።
፵፬ አሁንም፣ የጌታ መምጣት እንደሌባ በማታ እንደሚመጣ እነዚህን ነገሮች እንድታውቁ ዘንድ፣ እውነት እላችኋለሁ።
፵፭ እና ይህም እቃዎቹን ካልጠበቀ በማያውቅበት ሰአት ሌባ እንደመጣበት እና እቃዎቹን እንደወሰደበት እና ከጓደኞቹ ጋር እንደተከፋፈለበት ባለቤት ሰው አይነት ነው።
፵፮ እና እርስ በራሳቸውም ተባባሉ፣ ጥሩው ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ በነቃ፣ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም፣ እና እቃዎቹን ባላጣ ነበር።
፵፯ እና እንዲህ አላቸው፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።
፵፰ ጴጥሮስም ጌታ ሆይ፣ ይህን ምሳሌ ለእኛ ወይስ ደግሞ ለሁሉ ትናገራለህን? አለው።
፵፱ ጌታም አለ፣ የተናገርኩት እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ለልጆቹ ለሚሰጧቸው ጌታ በቤተ ሰዎቹ ላይ ለሚሾሙት ነው።
፶ እነርሱም ታማኝና መጋቢ አገልጋይ ማን ነው? አሉ።
፶፩ ጌታም አላቸው፣ ይህም የምግቡን ክፍል በጊዜው ለመስጠት የሚጠብቀው አገልጋይ ነው።
፶፪ ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው።
፶፫ እውነት እላችኋለሁ፣ ባለው ሁሉ ላይ መሪ ያደርገዋል።
፶፬ ያ ክፉ ባሪያ ግን ሲጠብቅ የማይገኘው ነው። እና ያ ባሪያ ሳይጠብቅ ከተገኘ፣ በልቡም ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ ያስባል፤ እና ሎሌዎችን ባሪያዎችና ገረዶችንም መምታት፣ መብበምላትም፣ መጠጣትም፣ መስከርም ይጀምራል።
፶፭ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፣ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል እድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርጋል።
፶፮ የጌታውንም ፈቃድ አውቆ፣ ለጌታው መምጣት ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል።
፶፯ የጌታውን ፈቃድ ያላወቀ፣ መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ግን ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ጌታ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ ሰዎች አብዝተው ይሹበታል።