የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፮


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፮፥፳፱–፴።ሉቃስ ፮፥፳፱–፴ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ከጠላት ጋር ከመከራከር በመሰደድ መጽናት ይሻላል ብሎ አስተማረ።

፳፱ ጕንጭህን ለሚመታህ ደግሞ ሁለተኛውን ስጠው፥ ወይም፣ በሌላ ቃል፣ እንደገና ከመሳደብ ሌላውን መስጠት ይሻላል። ጐናጸፊያህንም ለሚወስድ እጀ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው።

ጠላትህ እነዚህ ነገሮች እንዲወስድ መፍቀድ፣ ከእርሱ ጋር ከመጣላት ይሻላልና። በእውነት እላችኋለሁ፣ በሚስጥር የሚያየው የሰማይ አባታችሁ ያን ክፉውን ወደ ፍርድ ያመጣልና።