ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፫፥፬–፲፩። ከሉቃስ ፫፥፬–፮ ጋር አነጻፅሩ
ክርስቶስ እንደተተነበየው ደህንነትን ለእስራኤል እና ለአህዛብ ለማምጣት ይመጣል። በዘመን ፍጻሜ፣ በአለም ላይ ለመፍረድ እንደገና ይመጣል።
፬ በነቢዩ በኢሳይያስ ቃል መጽሐፍ ውስጥ እንደተጻፈው፤ እና ቃላቶቹም እነዚህ ናቸው፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረበዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ አለ።
፭ እነሆ፣ እና አስተውሉ፣ በነቢያት መፅሀፍ ውስጥ እንደተጻፈውም የአለምን ኀጥያቶች ለማስወገድና ወደ አህዛብ ህዝቦችም ደህናነትን ለማምጣት፣ የጠፉትንም፣ የእስራኤል በግ መንጋዎች የሆኑትን፣ ለመሰብሰብ ይመጣል።
፮ አዎን፣ እንድሁም የተበተኑትን እና የሚሰቃዩትን፤ ደግሞም መንገድን ለማዘጋጀት፣ እና ለአህዛባት ወንጌልን ለመስበክ የሚቻልም ለማድረግ፤
፯ በጭለማ ጥላ ተቀምጠው ላሉትም፣ እስከ ምድር ዳርም ድረስ፣ ብርሀን ለመሆን፤ የሙታንን ትንሳኤ ለማምጣት፣ እና በአብ ቀኝ እጅ በኩል ለመኖር ወደላይም ለማረግ፣
፰ እስከ ዘመን ፍጻሜ፣ እና ህግ እና ምስክር እስከሚታተም፣ እና የመንግስት ቁልፍም ወደ አብ እስከሚመለሱ ድረስ፤
፱ ለሁሉም ፍርድ ለመስጠት፤ በሁሉም ላይ ለፍርድ ለመውረድ፣ እና እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች ስለሰሩት እግዚአብሔርን የማያመልኩ ስራቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ፤ እና ይህም ሁሉ በሚመጣበት ቀን።
፲ ይህም የሀይል ቀን ነውና፣ አዎን፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሞላል፣ እና እያንዳንዱ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሆናል፣ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሆናልና፤
፲፩ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያል።
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፫፥፲፱–፳። ከሉቃስ ፫፥፲–፲፫ ጋር አነጻፅሩ
ደሆች ከግምጃ ቤት ትርፍራፊ እንክብካቤ ያገኛሉ። ቀራጮችም በህግ ከተመደበላቸው በላይ ምንም አይወስዱም።
፲፱ ቴዎፍሎስ፣ ይህም በአንተ በደንብ ይታወቃል፣ በአይሁዳ ልምድ መሰረት፣ እና ገንዘብን ወደ ግምጃ ቤት በሚቀበሉበት በህጋቸው ባህል መሰረት፣ ከተቀበሉት ግምጃ ቤት ትርፍ ውስጥ ለድሆች ተመድቧል፣ ለእያንዳንዱ ሰው ክፍሉም፤
፳ እና ከዚህም መንገድ ቀራጮችም አደረጉ፣ ስለዚህ ዮሐንስ ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው።