የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፬


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፬፥፴፭–፴፯።ሉቃስ ፲፬፥፴፬ ጋር አነጻፅሩ

ሙሴን እና ነቢያትን የሚያውቁ በኢየሱስ ያምናሉ።

፴፭ ከእነርሱ አንዳንዶቹ ወደ እርሱ መጡ፣ መምህር፣ ሙሴ እና ነቢያት አሉን፣ እናም በእነርሱ የሚኖር ሁሉ፣ ህይወት አይኖረውምን? አሉ።

፴፮ እና ኢየሱስ መልሶ አለ፣ ሙሴን ወይም ነቢያትን አታውቁም፤ የምያውቋቸው ቢሆን ኖሮ፣ በእኔ ታምኑ ነበርና፤ ለዚህ ምክንያት ነበር የተጻፉትና። እኔ የተላኩት እናንተ ህይወት ይኖራችሁ ዘንድ ነው። ስለዚህ መልካም ከሆነው ጨው ጋር አመሳስለዋለሁ፤

፴፯ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፈጣል?