የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯፥፳፩።ሉቃስ ፲፯፥፳–፳፩ ጋር አነጻፅሩ

የእግዚአብሔር መንግስት አስቀድማ መጥታለች።

፳፩ ደግሞም እንኋት በዚህ ወይም እንኋት በዚያ አይሉአትም፣ እነሆ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።

ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፯፥፴፮–፵።ሉቃስ ፲፯፥፴፯ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ስለኋለኛው ቀናት መሰብሰብ ለመግለጽ የንስርን ምሳሌ ተናገረ።

፴፮ መልሰውም ጌታ ሆይ፣ ወዴት ይወሰዱ? አሉት።

፴፯ እርሱም ሥጋ ወዳለበት፣ ወይም በሌላ ቃላቶች፣ የትም ቅዱሳን በተሰበሰቡበት፣ በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ፣ ወይም በዚያ የሚቀሩትም አብረው ይሰበሰባሉ አላቸው።

፴፰ ይህን የተናገረው የቅዱሳንን መሰብሰብ በሚመለከት ነው፤ እና መላእክቶች ወርደው የሚቀሩትን ስለመሰብሰባቸው ነው፤ አንዱን ከመኝታ፣ ሌላን ከወፍጮ፣ እና ሌላን ከሜዳ፣ የትም ከሚፈልግበት።

፴፱ በእውነትም ጻድቅ የሚኖርበት አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር ይኖራሉ።

እና ምንም እርኩስ ነገር አይገኝበትም፤ ምድርም አሮጌ፣ እንዲሁም እንደ ልብስ፣ ሆና ብከላም ተጨምሮባታልና፣ ይህም ቢሆን ይህም ይጠፋል፣ እና የእግር መርገጫም፣ ከኀጥያት ጸድታ፣ በቅድስና ትቀራለች።