ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፲፮፥፲፮–፳፫። ከሉቃስ ፲፮፥፲፮–፲፰ ጋር አነጻፅሩ
ህግ እና ነቢያት ስለኢየሱስ ይመሰክራሉ። ፈሪሳውያን መንግስትን ለመደምሰስ ይፈልጋሉ። ኢየሱስ የሀብታሙን ሰው እና የአልዓዛርን ምሳሌ አስተዋወቀ።
፲፮ እንዲህም አሉት፣ ህግና ነቢያት አለን፤ ነገር ግን ይህን ሰው አለቃችን እንዲሆን አንቀበለውም፤ እራሱን በእኛ ላይ ዳኛ ያደርጋልና።
፲፯ ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ ህግ እና ነቢያት ስለእኔ ይመሰክራሉ፤ አዎን፣ እና የጻፉት ነቢያት ሁሉ፣ እንዲሁም ዮሐንስ፣ ስለእነዚህ ቀናት ቀድመው ተናግረዋል።
፲፰ ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ እውነትን የሚፈልግ ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።
፲፱ እና ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ይቀላል።
፳ እና ለምን ህግን እያስተማራችሁ የተጻፈውን ትክዳላችሁ፤ እና እንድትድኑ ዘንድ ህግን ለማሟላት አብ የላከውን ታኮንናላችሁ?
፳፩ እናንተ ደንቆሮዎች! በልባችሁ እግዚአብሔር የለም ብላችኋለን። እና የቀናውን መንገድም አጣማችኋል፤ እና በእናንተም መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፤ እና ትሁቶችን አሳዳችኋል፤ እና በሁከታችሁም መንግስትን ለመደምሰስ ትፈልጋላችሁ፤ እና የመንግስት ልጆችንም በግድ ትወስዳላችሁ። ለእናንተ ዘማዊዎችም ወዮላችሁ!
፳፪ ዘማዊ ናቸው ስላለም በእርሱ ተናድደው እንደገናም ሰደቡት።
፳፫ ነገር ግን ቀጥሎም አለ፣ ሚስቱንም የሚፈታ ሁሉ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ ከባልዋም የተፈታችውን የሚያገባ ያመነዝራል። እውነትም እላችኋለሁ፣ እናንተን እንደ ሀብታሙ ሰው አመሳስላችኋለሁ።