የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፳፩


ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፳፩፥፳፬–፳፮።ሉቃስ ፳፩፥፳፭–፳፮ ጋር አነጻፅሩ

ኢየሱስ ስለመምጫው አንዳንድ ምልክቶች ተናገረ።

፳፬ አሁን ስለ ኢየሩሳሌም መጥፋትን በሚመለከት እነዚህን ነገሮች ተናገራቸው። ከእዚያም ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ መምህር፣ ስለመመለስህ ንገረን?

፳፭ እርሱም መልሶ አላቸው፣ የአሕዛብም ዘመን በሚፈጸምበት የትውልድ ዘመን በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ። ምድር እና የታላቅ ባህር ውሀዎች ደግመውም ይጨነቃሉ።

፳፮ የሰዎች ልቦችም ስለፈሩ እና ወደ ምድር የሚመጡትን ነገሮች ስለሚመለከቱ ወደቁባቸው። የሰማይ ሀይላትም ይንቀጠቀጣሉ።

ጆ.ስ.ት.፣ ሉቃስ ፳፩፥፴፪።ሉቃስ ፳፩፥፴፪ ጋር አነጻፅሩ

የአህዛብ ዘመን ሲሟላ ሁሉም ነገሮች ይሟላሉ።

፴፪ እውነት እላችኋለሁ፣ የአህዛብ ዘመን የሚሟላበት ጊዜ ትውልድ፣ ሁሉም እስኪሟላ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።