አጠቃላይ ጉባኤ
አባታችንን ማመን
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:20

አባታችንን ማመን

እግዚአብሔር አያሌ አስፈላጊ ውሳኔዎችን እናደርግ ዘንድ ያምነናል እንዲሁም በሁሉም ጉዳዮች እርሱን እንድናምነው ይጠይቀናል።3

በሰኔ 1፣ 1843 (እ.አ.አ) አዲሰን ፕራት ባለቤቱን ሉዊዛ ባርነት ፕራትን ወጣት ቤተሰባቸውን እንድትንከባከብ ትቷት በሀዋዪ ደሴቶች ወንጌልን ለመስበክ ናቩ ኢለኖይን ለቆ ሄደ።

በናቩ ስደቱ እየጠነከረ በሄደ ጊዜ ቅዱሳኑም ለቀው እንዲሄዱ በመገደዳቸው እና በአመቱም አጋማሽ ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ ለመፍለስ በተዘጋጁ ጊዜ ሉዊዛ ጉዞውን የማድረግ ውሳኔ ተጋረጠባት። ለብቻዋ ከመኋዝ ይልቅ እዚያው መቆየት እና አዲሰን እስኪመለስ መጠበቁ ይቀል ነበር።

በሁለቱም ሁኔታ እንድትሄድ ካበረታታት ከነቢዩ ብሪግሃም ዘንድ ምሪትን ፈለገች። ታላቅ ውጣውረድ እና የግል የሆነ ማመንታት ቢኖርባትም በየጊዜው ጉዞውን በስኬት አከናውናለች።

በመጀመሪያ ሉዊዛ በጉዞው ጥቂት ደስታ ነበር ያገኘችው። ይሁን እንጂ ወዲያውኑ አረንጓዴ የለመለመ ሳር፣ በህብረ ቀለማት የተዋቡ የበረሃ አበቦችን እና በወንዝ ዳርቻዎች አጠገብ ያለ የተጠጋገነ መሬት በማየቷ እየተደሰተች መጣች። “በአእምሮዬ የነበረው ጭጋግ ቀስ በቀስ እየደበዘዘ ሄደ፤” በማለት አስታወሰች፣ “እናም በጓዱ ውስጥ ከሷ ይበልጥ ሳቂታ የነበረች አንድም ሌላ ሴት አልነበረችም።”

የሉዊዛ ታሪክ በጥልቀት አነቃቅቶኛል። የግል ፍላጎቶቿን ወደጎን ለመተው፣ እግዚአብሔርንም ለማመን የነበራትን ችሎታ እና ሁኔታውን በተለየ መልኩ እንድታይ ያገዛትን እምነት ለመለማመድ የነበራትን ፈቃደኝነት አደንቃለሁ።

የትም ብንሆን ስለኛ የሚያስብ እና ከማንም ወይም ከምንም በላይ ልንተማመንበት የምንችል አፍቃሪ አባት በሰማይ እንዳለን አስታውሳኛለች።

የእውነት ምንጭ

እግዚአብሔር አያሌ አስፈላጊ ውሳኔዎችን እናደርግ ዘንድ ያምነናል እንዲሁም በሁሉም ጉዳዮች እርሱን እንድናምነው ይጠይቀናል። ይህ በተለይ አስቸጋሪ የሚሆነው ውሳኔያችን ወይም የአደባባይ አስተሳሰባችን፣ እርሱ ለልጆቹ ካልው ፈቃድ የተለየ በሚሆንበት ጊዜ ነው።

አንዳንዶች እንደሚያስቡት ትክክል በሆነው እና ስህተት በሆነው መካከል መስመር እንድናበጅ ይሻሉ ምክንያቱም እውነት አንጻራዊ ነው፣ እውነት እንደራስ እይታ ይገለጻል፣ ወይም እግዚአብሔር ለጋስ ከመሆኑ የተነሳ ለምናከናውናቸው ማናቸውም ጉዳዮች የሚጨነቅ አይደለም ብለው ስለሚያምኑ ነው።

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመረዳት እና ለመቀበል ስንፈልግ፣ ትክክል በሆነው እና ስህተት በሆነው መካከል ድንበር መኖሩን መግለጽ የእኛ ተግባር እንዳልሆነ ማስታወስ ይገባል። ለእኛው ጥቅም እና በረከት ተመስርቶ ባለ ዘለአለማዊ እውነት፣ እግዚአብሔር ራሱ እነዚህን ድንበሮች መስርቷል።

የእግዚአብሔርን ዘለአለማዊ እውነት የመቀየር ፍላጎት ረጅም ታሪክ ያለው ነው። ይህ የጀመረው ሰይጣን በእግዚአብሔር እቅድ ላይ ባመጸበት ጊዜ አለም ከመፈጠሩ በፊት ነው። ይህን በመከተል፣ እንደ ሼረም፣ ናሆር እና ቆሪሆር ያሉ ሰዎች እምነት ሞኝነት ነው፣ ራእይ አያስፈልግም፣ እንዲሁም ማድረግ የምንፈልገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው በማለት ተከራክረው ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በአብዛኛው ይህ ከእግዚአብሔር እውነት ማፈንገጥ ወደ ታላቅ ሀዘን ያመራል።

አንዳንድ ነገሮች እንደአገባባቸው የሚወሰኑ ቢሆኑም ሁሉም ነገር ግን አይደለም። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም ኔልሰን በተደጋጋሚ እንዳስተማሩት የእግዚአብሔር እውነቶች፣ ፍጹም፣ ራሳቸውን የቻሉ፣ እና በእግዚአብሔር በራሱ የሚገለጹ ናቸው።

ምርጫችን

ማንን እንደምናምን መምረጣችን ለህይወት አስፈላጊ ከሆኑት ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ ነው። ንጉስ ቢንያም ህዝቡን እንዳስተማረው፣ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ እርሱ እንዳለ፣ … እመኑ፤… ሁሉ ጥበብ … እንዳለው እመኑ …፤ ጌታ ሊረዳቸው የሚችለውን ነገሮች ሁሉ ሰው እንደማይረዳቸው እመኑ።”

እንደመታደል ሆኖ እኛ የእግዚአብሔርን እውነት እንረዳ ዘንድ የቅዱሳን መጻህፍት እና የህያው ነቢያት ምሪት አለን። ምናልባትም ካለን ነገር በላይ ገለጻ ቢያስፈልግ እንኳ እግዚአብሔር በነቢያቱ አማካይነት ያዘጋጅልናል። እስካሁን በሙላት ያላወቅናቸውን እውነቶች ለመረዳት በፈለግን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከልብ ለሆኑ ጸሎቶቻችን እርሱ መልስን ይሰጠናል።

ሽማግሌ ኒል ኤል አንደርሰን በአንድ ወቅት እንዳስተማሩት፣ “የግል አመለከቶቻችን አንዳንድ ጊዜ ከጌታ ትምህርቶች ጋር የማይጣጣሙ እንኳን ቢሆኑ አትደነቁ። እነዚህ የትምህርት፣ የትህትና፣ በጉልበታችን የምንሆንባቸው የጸሎት ጌዜያት ናቸው። እግዚአብሔርን በማመን ወደፊት በእምነት እንራመዳለን፣ ከጊዜ ወደጊዜ ከሰማዩ አባታችን የበለጠ መንፈሳዊ ማብራሪያን እንቀበላለን።”

ትኩረት በሰጠን ጊዜ እና ለቃሉም ለመገዛት ጥረት ባደረግን በሁሉም ጊዜያት እግዚአብሔር ቃሉን እንደሚሰጠን አልማ ያስተማረ መሆኑን ማሰብ ይረዳል። ለእግዜአብሔር ቃል ትኩረት ስንሰጥ የበለጠ እየተቀበልን፣ ምክሩን ችላ ባልን ጊዜ ደግሞ ምንም እስከማይቀረን ድረስ እየተወሰደብን እንሄዳለን። ይህ የእውቀት እጦት እውነትን ስህተት ሆኗል የሚያስብል አይደለም፣ ይልቁኑም ይህ የሚያሳየው ለመረዳት ችሎታውን እያጣን መሆኑን ነው።

ወደ አዳኙ ተመልከቱ

በቅፍርናሆም አዳኛችን ስለማንነቱ እና ስለተልእኮው አስተምሯል። ብዙዎች ጀርባቸውን እስኪሰጡ እና ከእርሱም ጋር ዳግም “[እንዳይራመዱ]” ቃሉን ለመስማት ከብዷቸው ነበር።

ለምን ትተውት ሄዱ?

ምክንያቱም እርሱ የተናገረውን አልወደዱም ነበር። በመሆኑም የራሳቸውን ውሳኔ በማመን፣ ቀርተው ቢሆን ኖሮ ሊያገኟቸው ይችሉ የነበሩትን በረከቶች በማጣት ትተውት ሄደዋል።

ተዕቢታችን በእኛ እና በዘለአለማዊው እውነት መካከል መምጣቱ ቀላል ነው። የማንረዳው ከሆነ፣ ፋታ ልንሰጠው፣ ስሜቶቻችንም እንዲረግቡ በማድረግ እና እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለብን መምረጥ እንችላለን። አዳኛችን ሲመክረን፣ “ባሰ[ብነው] ነገር ሁሉ ወደ [እርሱ] [እንድንመለከት]፣ [እንዳንጠራጠር]፣ [እንዳንፈራ]” አስተምሮናል። በአዳኙ ላይ ትኩረት ስናደርግ እምነታችን ስጋታችንን መቋቋም መጀመር ይችላል።

ፕሬዚዳንት ዲይተር ኤፍ. ኡክዶርፍ እንዲህ እንድናደርግ አበረታትተውናል፦ “እባካችሁ እምነታችሁን ከመጠራጠራችሁ በፊት ጥርጣሬአችሁን ተጠራጠሩ። ጥርጣሬ እስረኛ እንዲያደርገን እና ከመለኮታዊው ፍቅር፣ ሰላም፣ እና በጌታ ኢየሱስ እምነት ከሚመጣ ስጦታ እንዲያስቀረን በጭራሽ ልንፈቅድለት አይገባም።”

በረከቶች የሚመጡት አርፈው ላሉት ነው

በዚያ ቀን ደቀመዛሙርት ጌታን ትተው በሄዱ ጊዜ፣ አስራ ሁለቱን “እናንተስ ትሄዳላችሁን?” በማለት ጠየቃቸው።

ጴጥሮስም እንዲህ መለሰ፦

“ጌታ ሆይ፣ ወደ ማንስ እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ።

“እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምነናል፣ አውቀናልም።”

አሁን፣ ሐዋርያቱ የኖሩት በአንድ አይነት አለም ውስጥ ነበር፣ እንዲሁም ትተውት እንደሄዱት ደቀመዛሙርት ተመሳሳይ ማህበራዊ ችግሮችን ይጋፈጡ ነበር። ይሁን እንጂ፣ በዚህ ጊዜ፣ እምነታቸውን መርጠዋል እንዲሁም እግዚአብሔርን ታምነዋል፣ በዚህም ለቀሩት እግዚአብሔር የሚሰጠውንም በረከት ለራሳቸው አስቀርተዋል።

ምናልባት እናንተም፣ እንደ እኔ፣ አንዳንድ ጊዜ ለውሳኔ ልባችሁ ተከፍሎ ታገኙ ይሆናል። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመረዳት ወይም በደስታ ለመቀበል ችግር በሚያጋጥመን ጊዜ የትም እንሁን የት ባለንበት የሚወደን መሆኑን ማስታወስ ያጽናናል። እንዲሁም እርሱ ለእኛ የተሻለ ነገር አለው። ወደ እርሱ ብንጠጋ እርሱ ይረዳናል።

ወደ እርሱ ለመጠጋት አስችጋሪ መስሎ እንኳን ቢታየን፣ ልክ ለልጁ ፈውስን የለመነው አባት በአዳኙ እንደተነገረው፣ “ለሚያምን ሁሉ ይቻላል።” በጭንቀታችን ጊዜ እኛም እንዲሁ “አለማመኔን እርዳው” በማለት መጮህ እንችላለን።

ፈቃዳችንን ለእርሱ ማስገዛት

ሽማግሌ ኒል ኤ.ማክስዌል በአንድ ወቅት እንዲህ አስተማሩ፦ “ፈቃድን አሳልፎ መስጠት በእግዚአብሔር መሰዊያ ላይ የምናስቀምጠው ብቸኛው የተለየ ግላዊ ነገር ነው።” ንጉስ ቢንያምን ይበልጥ ያጓጓው ህዝቡ “የዋህ፣ ትሁትና ትዕግስተኛ፣ በፍቅር የተሞላ፣ ልጅ አባቱ የሰጠዉን እንደሚቀበለዉ ሁሉንም ነገሮች ጌታ የሚሰጠውን ለመቀበል ፈቃደኛ” መሆን እንዳለባቸው ማስተማሩ የሚገርም አይሆንም።

እንደወትሮው ሁሉ አዳኛችን ለእኛ ፍጹም የሆነ ምሳሌነትን አስተምሯል። ልቡ እየከበደበት ሊያደርገው የነበረውን የህመም ስራ በማወቅ የመሲህነት ተልዕኮውን በመፈጸም እና ለእናንተ እና ለእኔ የዘለአለማዊነትን የተስፋ ቃል ተደራሽ በማድረግ ለአባቱ ፈቃድ ራሱን አስገዝቷል።

ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳችንን የማስገዛት ምርጫ ደቀመዝሙርነትን ማእከል ያደረገ የእምነት ድርጊት ነው። ያንንም ምርጫ በማድረግ የምርጫ ነጻነታችን የተመናመነ እንዳልሆነ እንገልጣለን፣ ይልቁንም አላማን፣ ሀሴትን ሰላምን፣ እና በሌላ ስፍራ ልናገኘው የማንችለውን ተስፋ በሚያስገኝልን በመንፈስ ቅዱስ መገኘት የሚጎላ እና የምንካስበት ይሆናል።

ከአያሌ ወራት በፊት የካስማ ፕሬዘዳንት እና እኔ በእርሱ ካስማ ውስጥ ያለችን አንዲት እህት እና ወጣት ጎልማሳ ልጇን ጎበኘን። ከቤተክርስቲያን ከራቀች ከረጅም ጊዜ እንዲሁም አስቸጋሪውን እና መልካም ያልሆነውን ጉዞ ከተጓዘች በኋላ ልትመለስ ችላለች። በጉብኝታችን ወቅት ለምን ተመልሳ እንደመጣች ጠየቅናት።

“ህይወቴን አመሳቅዬዋለሁ፣” አለች “እናም የት መሆን እንዳለብኝ አወቅሁኝ፣”

ከዚያም እኔ በጉዞዋ ምን እንደተማረች ጠየኋት።

በጥቂቱ ስሜታዊ በመሆን ቤተክርስቲያን ያለመምጣትን ልማድ ለመስበር ረዘም ላለ ጊዜ መካፈል እንዳለባት እና መቆየት የምትፈልግበት ስፍራ መሆኑን እስከምታረጋግጥ ድረስ ይህንኑ መቀጠል እንዳለባት የተማረች መሆኗን አካፈለችን። መመለሷ ቀላል አልነበረም፣ ነገር ግን በሰማይ አባት እቅድ እምነትን ስትለማመድ የመንፈስም መመለስ ተሰምቷታል።

ከዚያም “እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ እናም የእርሱ መንገድ ከእኔ የትሻለ እንደሆነም ለራሴ ተምሬያለሁ” በማለት አከለች

ዘለአለማዊ አባት ስለሆነው ስለሚወደን እግዚአብሔር፣ ስለአዳነንም ስለልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ። እነርሱ ህመሞቻችንን እና ፈተናዎቻችንን ያውቃሉ። በፍጹም አይተዉንም፣ እንዴት እንዲያበረቱንም በፍጹምነት ያውቃሉ። ከማንም ወይም ከምንም ነገር በላይ ስናምናቸው ደስተኞች ልንሆን እንችላለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።