የሟችነት ዓላማ ውጤታማ ነው!
ሁላችንም የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ቢኖሩም፣ አፍቃሪው የሰማይ አባታችን እጣ ፈንታችን ውድቀት ሆኖ እንዳይቀር የደስታ እቅድን ለእኛ አዘጋጅቶልናል።
ለበርካታ ዓመታት በአጥቢያዬ ለምትኖር አንዲት አረጋዊት እህት እንደ የቤት ለቤት አስተማሪ እንድሆን ተመድቤ ነበር። ህይወቷ ቀላል አልነበረም። በመጫወቻ ሜዳው ላይ በደረሰባት የልጅነት አደጋ ምክንያት የተለያዩ የጤና ዕክሎች ነበሩባት እንዲሁም የሕይወቷን ዕድሜ ሙሉ በሕመም አሳልፋለች። በ32 ዓመቷ ትዳሯ ፈርሶ አራት ልጆቿን ለማሳደግ እና ለማስተዳደር ሃላፊነት ነበራት፣ ከዚያም በሃምሳ ዓመቷ መልሳ ትዳር ያዘች። ሁለተኛ ባሏ የሞተው 66 ዓመት እያለች ሲሆን፣ ይህች እህት መበለት ሆና ለተጨማሪ 26 ዓመታት ኖራለች።
በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ፈተናዎች ቢገጥሟትም፣ እስከ መጨረሻው ለቃል ኪዳኗ ታማኝ ነበረች ። ይህች እህት ትጉህ የትውልድ ሐረግ አዋቂ፣ በቤተ መቅደስ የምትሣተፍ እንዲሁም የቤተሰብ ታሪኮችን ሰብሳቢና ጸሐፊ ነበረች። ምንም እንኳ ብዙ አስቸጋሪ ፈተናዎች ቢኖሩባትም፣ እንዲሁም አንዳንዴ ሐዘንና ብቸኝነት ይሠማት የነበረ ቢሆንም፣ ገፅታዋ በደስታ የተሞላ ነበር እናም ለዛ ያለውና የሚያምር ባሕርይ ነበራት።
ከህልፈቷ ዘጠኝ ወራት በኋላ፣ ከወንድ ልጆቿ መካከል አንዱ በቤተመቅደሱ ውስጥ አስደናቂ ተሞክሮ አግኝቷል። እናቱ ለእርሱ መልእክት እንዳላት በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተማረ። ከእርሱ ጋርም ተነጋገረች ነገር ግን በራእይ ወይም በድምፅ ንግግር ቃላት አልነበረም። የሚከተለው የማያጠራጥርመልእክት ከእናቱ ዘንድ ወደልጁ አእምሮ መጣ፦ “የሟችነት ዓላማ ውጤታማ እንዳሆነ እንድታውቅ እፈልጋለሁ፣ እና ሁሉም ነገር [በሕይወቴ ውስጥ] የሆነው ለምን እንደሆነ አሁን እንደተረዳሁ እንድታውቅ እፈልጋለሁ—እናም ሁሉ መልካም ነው።”
ከሁሉም ይበልጥ የዚህ መልዕክት የሚያስደንቅው ነገር ቢኖር፣ ያለችበትን ሁኔታ እና ይህች እህት ያጋጠማትን ችግሮች መወጣት እና መቋቋም በመመልከት ነው።
ወንድሞች እና እህቶች፣ የሟችነት ዓላማ ውጤታማ ነው! ዓላማ እንዲኖረውም ተደርጎ ነው የተሰራው! ሁላችንም የሚያጋጥሙን ፈተናዎች፣ የልብ ምሬቶች፣ እና ችግሮች ቢኖሩም፣ አፍቃሪ፣ ጥበበኛ፣ እና ፍጹም የሰማይ አባታችን እጣ ፈንታችን ውድቀት ሆኖ እንዳይቀር የደስታ እቅድን ለእኛ አዘጋጅቶልናል። የእርሱ እቅድ ከስጋዊ ድክመቶቻችን እንበልጥ ዘንድ መንገድ ይከፍትልናል። ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሯል፣ “እነሆ፣ የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት ስራዬ እና ክብሬ ይህ ነው።”
ይሁን እንጂ የጌታ “ሥራ እና … ክብር” እንዲሁም “የህያውነት እና የለአለማዊ ሕይወት” ተጠቃሚዎች መሆን የምንፈልግ ከሆነ፣ መማር እና ማወቅ፣ እንዲሁም፣ አንዳንዴ እስከምንችለው ያኽል ድረስ በሚሞክረን፣ በሚያጠራው እሳት መሃል ማለፍን ግድ ሊለን ይገባል። የዚህን ዓለም ችግሮች፣ ፈተናዎች እና የህይወት ክብደቶች ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ መሞከር፣ በጣም አስፈላጊ የሆነውን የሟችነትን የዓላማ ስራ ሂደት ማደናቀፍ ይሆናል ።
ስለዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሲያጋጥመን ሊገርመን አይገባም። እኛን የሚገዳደሩ ሁኔታዎች እና እውነተኛ ልግስና እና ትዕግስትን እንድንለማመድ የሚያስችሉን ሰዎች ያጋጥሙናል። ችግሮቻችንን ልንታገሳቸው እና ጌታ የተናገረውንም ልናስታውስ ይገባናል፣ ጌታ እንዳለው፦
“እና ለእኔ ጉዳይ፣ ለስሜ ህይወቱን የሚሰጥም ዳግም ያገኘዋል፣ እንዲሁም ዘለአለማዊ ህይወትን።
“ስለዚህ፣ ጠላቶቻችሁን [ወይም ችግሮቻችሁን፣ ፈተናዎቻችሁን፣ ወይም የህይወት ክብደቶቻችሁን] አትፍሩ፣ በቃል ኪዳኔ … ፣ እንደምትጸኑ፣ ብቁም ሆናችሁ እንድትገኙ፣ በሁሉም ነገሮች እፈትናችሁ ዘንድ በልቤ አውጄዋለሁና፣ ይላል ጌታ።”
ስለ ችግሮቻችን ስንበሣጭ ወይም ስንጨነቅ ወይም ከህይወት ችግር ባለን ፍትሀዊ ድርሻ በላይ እየተቀበልን እንደሆነ ሲሰማን፣ ጌታ ለእስራኤል ልጆች የተናገረውን ማስታወስ እንችላለን፦
“አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።”
ሌሂ ልጁን ያዕቆብን እንዳስተማረው፦
“… በመከራና በብዙ ኃዘን ተሰቃይተሀል…። ይሁን እንጂ፣ … [እግዚአብሔር] መከራህን ወደ ጥቅምህ ይለውጥልሃል።… ስለዚህ፣ በቤዛህ ፅድቅ ምክንያት አንተ እንደምትድን አውቃለሁ።”
ምክንያቱም ይህች ህይወት የፈተና ቦታ ስለሆነች እና “የችግር የጨለማ ደመና በላያችን ላይ ተንጠልጥሎ እና ሰላማችንን ለማጥፋት ሲያስፈራራን፣” ከሕይወት ችግሮች ጋር የተያያዘን በሞዛያ 23 ውስጥ የሚገኘውን ይህንን ምክር እና ተስፋ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፦ “ይሁን እንጂ—እምነቱን በእርሱ ያደረገ በመጨረሻው ቀን ከፍ ይላል።”
በወጣትነቴ፣ በሌላ ሰው ላይ በሚፈጽመው ጽድቅ ባልሆኑ ድርጊቶች ምክንያት ከፍተኛ የስሜት ስቃይና ውርደት ደርሶብኛል፣ ይህም ለራሴ ያለኝ ግምት እንዲሁም በጌታ ፊት ያለኝ ብቁነት ለብዙ ዓመታት እንዲነካ አድርጓል። ቢሆንም፣ በዚህ የእንባ ሸለቆ ውስጥ በምንቆይበት ጊዜ እንድንለማመድ የተጠራነውን ማንኛውንም ችግር ጌታ ሊያበረታን እና ሊደግፈን እንደሚችል የግል ምስክርነቴን እሰጣለሁ ።
ጳውሎስ ያጋጠመውን ሁኔታ እናውቃለን፦
“ስለዚህም [በተሰጠኝ] መገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።
ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
“እርሱም። ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።”
የጳውሎስ “የሥጋ መውጊያ” ምን እንደሆነ አናውቅም። አካላዊ ሕመም፣ የአእምሮ ወይም የስሜት ሕመም ወይም ፈተና መሆን አለመሆናቸውን ለመግለጽ አልሞከረም። ነገር ግን እርዳታ ለማግኘት እንደታገለ እና ከጌታ ጋር እንደተማጸነ እና በመጨረሻም የጌታ ብርታትና ሀይል በዚህ በኩል የረዳው መሆኑን በዝርዝር ማወቅ አያስፈልገንም ።
ልክ እንደ ጳውሎስ ሁሉ፣ እኔም ከጊዜ በኋላ በስሜትና በመንፈሳዊ የተጠናከርኩት በጌታ እርዳታ ነበር፣ እናም ከብዙ አመታት በኋላ፣ ሁልጊዜም የወንጌል በረከቶችን ለማግኘት ብቁ ሰው እንደሆንኩ ተገነዘብኩ። አዳኝ ብቁ ያለመሆን ስሜቴን እንዳሸንፍ እና ለጥፋተኛው ሰው ይቅርታን እንዳደርግ እረዳኝ። በመጨረሻም የአዳኝ የሀጢያት ክፍያ ለእኔ የግል ስጦታ እንደሆነ እና የሰማይ አባቴ እና ልጁ ፍፁም በሆነ መንገድ እንደሚወዱኝ ተረዳሁ። በአዳኙ የሀጢያት ክፍያ ምክንያት፣ የሟችነት ዓላማ ውጤታማ ነው።
የኋላ በኋላም አዳኝ እንዴት እንዳዳነኝ እና በእነዚህ አጋጣሚዎች ከጎኔ እንደቆመ ለማወቅ በመቻሌ ተባርኬ ሳለሁ፣ በአስራዎቹ እድሜ ውስጥ የነበረኝ አሳዛኝ ሁኔታ፣ የእኔ የግል ጉዞዬ እና ልምዴ እንደነበረ፣ የመጨረሻው ውጤትም በሌሎች የዓመፀኝነት ባሕርይ ምክንያት መከራ በደረሰባቸውንና እየተሠቃዩ ባሉትን ሰዎች እንዲጠቆም የሚደረግ እንዳልሆነ በግልፅ ተረድቻለሁ።
የሕይወት ተሞክሮዎች —መልካምና ክፉ —የሆኑት ጠቃሚ ትምህርት ሊሰጡን እንደሚችሉ እገነዘባለሁ። የሟችነት ዓላማ ውጤታማ እንደሆነ አሁን አውቄአለሁ እናም እመሰክራለሁ! በሕይወቴ ውስጥ ባጋጠሙኝ ነገሮች ምክንያት—ጥሩም ሆነ መጥፎ—በሌላው ድርጊት ለሚሰቃዩት ርህራሄ እናለተጨቆኑ ሰዎች ተመሳሳይ ስሜት እንደሚኖረኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
በህይወቴ አጋጣሚ ምክንያት—መልካምና ክፉ— ለሌሎች ደግ እንደሆንኩኝ፣ ሌሎችን እንደ አዳኝ እንደሚያደርገው፣ እና ለሃጢያተኛው የበለጠ መረዳት እንደሚኖረኝ እና ፍፁም ታማኝነት እንዳለኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በአዳኙ ፀጋ ላይ ስንመካ እና ቃል ኪዳኖቻችንን ስንጠብቅ፣ እንደ አዳኙን የሀጢያት ክፍያ ታላቅ ውጤት በምሳሌነት ማገልገል እንችላለን ።
ሟችነት ዓላማ ውጤታማ እንደሆነ የመጨረሻ ምሳሌዬን አካፍላለሁ።
እናቴ በሟችነት ህይወት ውስጥ ቀላል ጉዞ አልነበራትም። ከፍተኛ ክብርም ሆነ ዓለማዊ ክብር አላገኘችም፣ እንዲሁም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷ ያለፈ የትምህርት ዕድል አልነበራትም። በልጅነቷ ፖሊዮ የተባለ በሽታ ይዟት ስለነበር በግራ እግሯ ላይ ሕይወት ሙሉ የሚዘልቅ ሕመምና ሥቃይ ደርሶባት ነበር። አዋቂ ስትሆን ብዙ አስቸጋሪ እና ከባድ የሆነ የአካላዊ እና የገቢ መቃወስ ሁኔታ ውስጥ አሳልፋለች ነገር ግን ለቃል ኪዳኗ ታማኝ እናም ጌታን የምትወድ ነበረች።
እናቴ 55 ዓመት ሲሆናት፣ የስምንት ወር ሕፃን ልጅዋን፣ የእህቴን ልጅ ያላእናት ትታ፣ ቀጣይ ታላቅ እህቴ አረፈች። በተለያዩ ምክንያቶች፣ የተነሳ እናቴ ለቀጣዮቹ 17 ዓመታት፣ በአብዛኛው የእህቴን ልጅ አሣዳጊ ሆነች፤ ብዙውን ጊዜ ይህን ያደረገችው በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነበር። ሆኖም እነዚህ ልምዶች ቢኖሩም፣ ቤተሰቧን፣ ጎረቤቶቿን፣ እና የአጥቢያ አባላቶቿን በደስታ እና በፈቃደኝነት አገልግላለች እንዲሁም በቤተመቅደስ ውስጥ እንደ ስነ-ስርዓት ሰራተኛ ለብዙ አመታት አገልግላለች። እናቴ ባሳለፈቻቸው የመጨረሻዎቹ ዓመታት፣ በሕመም ምክንያት ብዙ ጊዜ ግራ ተጋብታ፣ በመጦሪያ ተቋም ውስጥ ትኖር ነበር። የሚያሳዝነው ግን በድንገት ስትሞት ብቻዋን ነበረች።
እሷ ካለፈች ከተወሰኑ ወራት በኋላ ፈጽሞ ያልተረሳኝ ሕልም አየሁ። በሕልሜ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ሕንፃ ቢሮዬ ውስጥ ተቀምጬ ነበር። እናቴ ቢሮው ውስጥ ገባች። ከመንፈሳዊው ዓለም እንደመጣች አውቃለሁ። የነበረኝንም ስሜት ሁልጊዜ አስታውሳለሁ። ምንም አልተናገረችም፣ ነገር ግን ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀውን እና ለመግለፅ በምቸገርበት አቅም መንፈሳዊ ውበቷን ፈነጠቀች።
የፊቷ ሞገስ እና ስብዕናዋ በጣም አስደናቂ ነበር! መንፈሳዊ ኃይሏንና ውበቷን በማመላከት“እናቴ፣ አንቺ በጣም ቆንጆ ነሽ!፣” ማለቴን አስታውሣለሁ ነው። ምንም ሳትናገር በድጋሚ—ምስጋናዋን ሰጠችኝ። ለእኔ ፍቅር እንዳላት ተሰማኝ፣ እንዲሁም ከዓለማዊ አሳቢነቷ፣ ከነበረችበት ፈታኝ ሁኔታ እንዲሁም “ክብራማ የሆነውን ትንሣኤ” በጉጉት እየተጠባበቀች በመሆን ደስተኛና የተፈወሰች እንደሆነች አውቅ ነበር። ለእናቴ፣ የሟችነት ዓላማ ውጤታማ እንደሆነ—እና ለእኛም ውጤታማ እንደሆነ አውቃለሁ።
የአምላክ ሥራና ክብር የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ሕይወት ማምጣት ነው። የሟችነት ልምዶች እንድናድግ እና እንድንለወጥ ወደ ህያውነት እና ወደ ዘለአለማዊ ህይወት እንድንሄድ የሚያስችለን የጉዞው አካል ናቸው። አምላክ ለእኛ ባለው እቅድ ውጤታማ እንድንሆን እንጂ እንድንወድቅ ወደዚህ አልተላክንም።
እንደ ንጉስ ቢንያም እንዲህ አስተምሯል፦ “እናም በተጨማሪ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁትን የተባረከና አስደሳቹን ሁኔታ እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ። እነሆም እነርሱ በሁሉም ነገሮች፣ ለጊዜያዊም ሆነ ለመንፈሳዊ፣ የተባረኩ ናቸውና፤ እናም እስከ መጨረሻው በታማኝነት ከዘለቁ፣ ለዘለአለም በማያልቀው ደስታ ከእግዚአብሔር ጋር ይኖሩ ዘንድ፣ መንግስተ ሰማይ ትቀበላቸዋለች።” በሌላ አነጋገር፣ የሟችነት ዓላማ ውጤታማ ነው!
የወንጌል ስርዓቶችን ስንቀበል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳኖች ስንገባ እና ከዚያም እነዚያን ቃል ኪዳኖች ስንጠብቅ፣ ንስሀ ስንገባ፣ ሌሎችን ስናገለግል፣ እና እስከመጨረሻ ስንጸና፣ እኛም የሟችነት አላማ ውጤታማ እንደሆነ በጌታ ላይ ሙሉ እምነት ሊኖረን እንደምንችል እመሰክራለሁ! ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ከሰማይ አባታችን ጋር ያለን ክብራማ የወደፊት እጣ ፈንታ በአዳኝ ጸጋ እና የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት እውን እንደሆነ እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።