አጠቃላይ ጉባኤ
የመዳናችን ደስታ
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


12:9

የመዳናችን ደስታ

የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እና ሀይል እያንዳንዳችንን ከስህተት፣ ከደካማነት፣ እና ኃጢአቶች ሊያድነን እና ከዚያ በላይ ተጨማሪ እንድንሆን ይረዳናል።

የዛሬ 10 አመት ገደማ የአዳኙን ምስል ለመሳል ተነሳስቼ ነበር። ምንም እንኳን ሰአሊ ብሆንም፣ ትንሽ የፍረሃት ስሜት ተሰማኝ። መንፈሱን ለማሳየት የሚችል የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል እንዴት እኔ ልስል እችላለሁ? ከየት ልጀምር? ጊዜስ አገኛለሁ?

ጥያቄዎች ቢኖሩኝም ጌታ እንደሚረዳኝ በማመን ለመጀመር ወሰንኩ። ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለእርሱ ትቼ መቀጠል ነበረብኝ። ጸለይኩ፣ አሰላሰልሁ፣ ጥናት ካደረኩ እንዲሁም ንድፍ አወጣሁ፣ እናም እርዳታን እና ግብዓቶችን በማግኘት ተባረኩ። ነጭ ሸራ የነበረው ነገር ከዚያ የላቀ ነገር መሆን ጀመረ።

የአዳኝ ሥዕል በመሳል በሂደት ላይ።

ሂደቱ ቀላል አልነበረም። አንዳንድ ጊዜ እኔ እንዳሰብኩት አይሆንልኝም ነበር። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በመንፈሥ የተነሣሡ ጭረቶችን እና ሀሳቦችን የማገኝባቸው ጊዜያት ነበሩ። እንዲሁም ብዙ ጊዜ፣ ደግሜ ደጋግሜ መሞከር ነበረብኝ።

በመጨረሻ በዘይት ቀለም የተሠራው ሥዕል እንደተጠናቀቀ እና እንደደረቀ ባሰብኩኝ ጊዜ፣ ከቆሻሻና ከአቧራ ለመከላከል የሚያስችለውን የሚያሳይ ቫርኒሽ መቀባት ጀመርኩ። ይህን እንዳደረግሁ በሥዕሉ ላይ ያለው ፀጉር መለወጥ፣ መጥፋት እና መሟሟት መጀመሩን አስተዋልኩ። ወዲያውኑ፣ ያ የስዕሉ ክፍል አሁንም እርጥብ እንደነበረና አለጊዜው ቫርኒሹን እንደቀባሁ ተገነዘብኩ!

የሥዕሌን የተወሰነ ክፍል በቫርኒሹ ጠርጌው ነበር። እንዴት እንዳዘንኩኝ። እግዚአብሄር እንድሰራ የረዳኝን ነገር እንዳጠፋሁ ሆኖ ተሰማኝ። አለቀስኩ፣ ውስጤም ታመመ። ተስፋ በመቁረጥ እንደዚህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ማንም ሰው የሚያደርገውን ነገር አደረግሁ፡ ለእናቴ ደወልኩላት። እሷም በጥበብ እና በእርጋታ፣ “የነበረውን መልሰሽ ማግኘት አትችይም፣ ነገር ግን ባለሽ ነገር የተቻለሽን ሁሉ አድርጊ” አለችኝ።

የተጠናቀቀ የአዳኝ ሥዕል።

እና እኔ ተካፍያለሁ፣ በክርስቲን ኤም. ዪ

ስለዚህ ጸለይኩ፣ እርዳታ ለማግኘትም ተማጸንኩ፣ ነገሮችን ለማስተካከልም ሌሊቱን ሙሉ ሳልኩ። ስዕሉን በማለዳ ስመለከት ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻለ ይመስል እንደነበረ አስታውሳለሁ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ሳይስተካከል ስህተት መስሎኝ የነበረው የእርሱ የህምረት እጅ የሚታይበት እድል ነበር። እሱ በሥዕሉ ላይ አልተጠናቀቀም፣ እና ከእኔ ጋር አልተጠናቀቀም። ታላቅ ደስታ እና እፎይታ ልቤን ሞላው። ሥዕሉን በተአምር ስላዳነው ብቻ ሳይሆን እያንዳንዳችንን ከስህተታችን፣ ከድክመታችን እና ከኃጢአታችን ለማዳን እና የተሻልን እንድንሆን ስለሚረዳን ስለ ፍቅሩ እና ስለኃይሉ የበለጠ ስላስተማረኝ ጌታን ስለ ምህረቱ አመሰገንኩት።

“መስተካከል የማይችል” ሥዕልን እንዳስተካክል በምሕረቱ ስለረዳኝ ለአዳኙ ያለኝ ምስጋና ጥልቀት እንደጨመረ ሁሉ፣ በድካሜ ላይ ለመስራት ስሻ እና ለስህተቶቼ ምህረትን ሳገኝ ለእርሱ ያለኝ ፍቅር እና ምስጋና እየጠነከረ ሄዷል። መለወጥ እና መንጻት ስለምችል አዳኜን ለዘላለም አመሰግናለሁ። ልቤ የየርሱ ነው፣ እንዲሁም እርሱ እንዳደርግ እና እንድሆን ለማድረግ ተስፋ አለኝ።

በሌላ መንገድ ልናውቀው በማንችለው መንገድ፣ ንስሐ መግባት የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማን እና እርሱን እንድናውቀውና እንድንወደው ያስችለናል። የአዳኙን እግር በእንባዋ ያጠበችውን ሴት በተመለከተ፣ እርሱ እንዲህ ብሏል፥ “እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል” በማለት ተናግሯል። ኢየሱስ በብዙ ይቅር ስላላት እጅግ አድርጋ ወደደችው።

እንደገና መሞከር እንደምንችል በማወቅ ውስጥ እንዲህ ያለ እፎይታ እና ተስፋ አለ—ሽማግሌ ቤድናር እንዳስተማሩት፣ በእውነት እና በቅንነት ንስሃ ስንገባ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ቀጣይነት ያለው የኃጢአታችንን ስርየት ማግኘት እንችላለን።

የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ኃይል ከቃል ኪዳኖቻችን ታላቅ በተስፋ የተሰጡ በረከቶች ውስጥ አንዱ ነው። በቅዱስ ስርዓቶች ውስጥ ስትሳተፉ ስለዚህ በረከት አስቡ። ያለሱ ቤታችን፣ ወደ ሰማይ አባታችን መመለስ እና ወደምንወዳቸው አንችልም።

ጌታችንና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለማዳን ኃያል እንደሆነ አውቃለሁ። የአለምን ሀጢያት ዋጋ የከፈለ እና ህይወቱን አሳልፎ የሰጠ እንዲሁም ዳግም ያነሳው የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆኑ መጠን የማዳንን እና የትንሳኤ ሀይልን ይዟል። እርሱን ለመረጡት ሁሉ ዘላለማዊነት እና የዘላለም ሕይወት እንዲቻል አድርጓል። በእርሱ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት አማካኝነት ንስሀ መግባት እንደምንችል እንዲሁም በእውነት መንጻት እና መዳን እንደምንችል አውቃለሁ። በዚህ መልኩ እኔን እና እናንተን መውደዱ ተአምር ነው።

እርሱ፣ “እፈውሳችሁ ዘንድ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን?” ይላል። የነፍሳችሁን “ባድማ” ማለትም ደረቅ፣ ከባድ እና በኃጢአትና በኀዘን ባዶ የተደረጉትን ቦታዎች መፈወስ እና “ምድረ በዳ[ችሁን] እንደ ኤደን” ያደርገዋል።

በጌቴሴማኒ እና በመስቀል ላይ የነበረውን የክርስቶስን ስቃይ እና መከራ ጥልቀት መረዳት እንደማንችል ሁሉ፣ “የእግዚአብሄርን ምሕረት እና ፍቅር እንዲሁም የይቅርታ ወሰን መለካትም ሆነ ጥልቀቱን መረዳት አንችልም”።

አንዳንድ ጊዜ መዳን የማይቻላችሁ ሆኖ፣ ምናልባትም ፈተናችሁ ወይም ባደረጋችሁት ነገር የተነሳ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የአዳኙ የስርየት ሀይል ለእናንተ እንዳልሆነ ሆኖ ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን እናንተ መምህሩ ከሚደርስበት በታች እንዳልሆናችሁ እመሰክራለሁ። አዳኙ “ከሁሉም ነገሮች በታች” ወርዷል እንዲሁም እናንተን ለማንሳት እና ከጨለማው ገደል ወስዷችሁ “ወደሚደነቅ ብርሃኑ” ሊያመጣችሁ በመለኮታዊ ቦታ ላይ ነው። በእርሱ መከራ አማካኝነት፣ እያንዳንዳችን የግል ድክመቶቻችንን እና ኃጢአታችንን የምናሸንፍበትን መንገድ አዘጋጅቶልናል። “በስሙ የሚያምኑትን እና ለንስሐ የሚሆን ፍሬን የሚያስገኙትን ማንኛውንም ሰው ለማዳን [ሙሉ] ስልጣን [አለው]።”

ሥዕሉን ለማስተካከል ሥራ እንዲሁም የሰማያት እርዳታን መማጸን እንዳስፈለገ ሁሉ፣ ለንስሐ የሚሆን ፍሬ” ማፍራት ሥራ፣ ቅንነት እና ትሕትናን ይጠይቃል። እነዚህ ፍሬዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በሃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ ማመን እና እምነትን መለማመድን፣ የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስን ለእግዚአብሔር ማቅረብን፣ ኃጢአትን መናዘዝን እና መተውን፣ የተበላሸውን፣ አቅማችን በፈቀደው መጠን ወደነበረበት መመለስን፣ እንዲሁም በጽድቅ ለመኖር መጣርን ያካትታሉ።

በእውነት ንስሀ ለመግባት እና ለመቀየር፣ መጀመሪያ “ኃጢያታችንን … [እንደፈጸምን]” ማመን አለብን። አንድ ሰው መታመሙን እስካልተረዳ ድረስ መድሃኒት መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን አይመለከትም። ወደ ውስጣችን ለመመልከት እና ፈውስ እና መፍትሄ የሚያስፈልገውን ለማየት ፈቃደኛ የማንሆንባቸው ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ።

በሲ ኤስ ሉዊስ ፅሁፎች ውስጥ፣ አስላን እነዚህን ቃላቶች በራሱ ውስብስብ ሃሳብ ውስጥ ላለ ሰው እንዲህ ሲል አቅርቧል፡ “ኦ፣ [የሰው ልጅ]፣ እንዴት በብልጠት ራስህን ከሚጠቅም ነገር ሁሉ ተከላከልክ።”

እኔ እና እናንተ ራሳችንን ከሚጠቅሙን ነገሮች የምንከላከለው እንዴት ነው?

እግዚአብሔር ሊባርከን ከሚፈልገው መልካም ነገር ራሳችንን አንከላከል። እንዲሰማን ከሚፈልገው ፍቅር እና ምህረት። ሊሰጠን ከሚፈልገው ብርሃንና እውቀት። በጣም እንደሚያስፈልገን ከሚያውቀው ፈውስ። ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቹ ሁሉ ካሰበው ከጥልቅ የቃል ኪዳን ግንኙነት።

በማወቅም ይሁን ሳናውቅ፣ ራሳችንን ከእግዚአብሔር ፍቅር በረከቶች ለመከላከል የወሰድነውን ማንኛውንም “የጦር መሳሪያ” እንጥል ዘንድ እጸልያለሁ። ራስ ወዳድነት፣ ፍርሃት፣ ጥላቻ፣ ቅያሜ፣ ግድየለሽነት፣ ፍትሃዊ ያልሆነ ፍርድ፣ ቅናት—እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን ከመውደድ እና ከእርሱ ጋር የገባነውን ቃል ኪዳኖች ሁሉ ከመጠበቅ የሚያግዱንን የትዕቢት መሳሪያዎች ናቸው።

የገባነውን ቃል ኪዳኖች ስንኖር፣ የመንፈሳዊነት ጥገኛ ተህዋስ የሆነውን የትዕቢት ድክመታችንን እንድናውቅ እና እንድናሸንፍ ጌታ የምንፈልገውን እርዳታ እና ሀይል ሊሰጠን ይችላል። ነቢያችን እንዲህ ብለዋል፦

“ንስሃ የንጽህና መንገድ ነው፣ ንጽህናም ሃይልን ያስገኛል፡፡”

“እና አቤቱ፣ የእርሱ ኃይል በመጪዎቹ ቀናት በጣም ያስፈልገናል” በማለት ተናግረውናል።

ልክ እንደ ሥዕሌ፣ ጌታ ስህተት ስንሰራ እኛን አይተወንም፣ ስንደናቀፍም አይሸሸንም። የእኛ ፈውስን እና እርዳታን መፈለግ ለእርሱ ሸክም ሳይሆን የመጣበት ምክንያት ነው። አዳኙ እራሱ እንዲህ ብሏል፦

“እነሆ ዓለምን ከኃጢያት ለማዳን ለዓለም ቤዛነትን ለማምጣት ወደ ዓለም መጥቻለሁ።”

“እነሆ የምህረት ክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ፣ እናም ወደ እኔ የሚመጡ የተባረኩ ናቸው” በማለት ተናግሯል።

ስለዚህ ኑ—እናንተ የደከማችሁ፣ የታከታችሁ እና ያዘናችሁ ኑ፣ ኑና ድካማችሁን ትታችሁ ዕረፍትን አግኙ።39 ቀንበሩን በላያችሁ ተሸከሙ፣ እርሱ የዋህ በልቡም ትሑት ነውና።

የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን ያዩአችኋል። ልባችሁን ያውቃሉ። እናንተ ስለምትወዷቸው ጨምሮ ስለሚያሳስባችሁ ነገር ያስባሉ።

አዳኙ የጠፋውን፣ ያለንን የተበላሸ እና የተሰበረ ግንኙነት ሊያድን ይችላል። የሞተ እና ተስፋ የሌለው ለሚመስለው ህይወትን እንዲተነፍስ—የወደቀ ሁሉ የሚድንበትን መንገድ አዘጋጅቷል።

አሁን ላይ ማሸነፍ ነበረብን ብላችሁ በምታስቡት ሁኔታ እየተቸገራችሁ ከሆነ ተስፋ አትቁረጡ። በራሳችሁ ትዕግስት ይኑራችሁ፣ ቃል ኪዳኖቻችሁን ጠብቁ፣ አዘውትራችሁ ንስሐ ግቡ፣ አስፈላጊ ሲሆን የመሪዎቻችሁን እርዳታ ፈልጉ፣ እንዲሁም በተቻላችሁ መጠን ወደ ጌታ ቤት ሂዱ። የሚልክላችሁን ተነሳሽነቶች ስሙ እንዲሁም አድምጡ። እርሱ ከእናንተ ጋር ያለውን የቃል ኪዳን ግንኙነት አይተውም።

በሕይወቴ ውስጥ የታገልኩባቸው እና ከልቤ ለማሻሻል የፈለግኳቸው አስቸጋሪ እና ውስብስብ ግንኙነቶች ነበሩ። አንዳንድ ጊዜ፣ በአብዛኛው እየተሳካልኝ እንዳልሆነ ይሰማኝ ነበር። ነገሮችን ለመጨረሻ ጊዜ አላስተካከልኩም ነበር? በማለት እጠይቅ ነበር። በእውነት ድክመቶቼን አላሸነፍኩም ነበር? በጊዜ ሂደት የግድ የእኔ ጉድለት እንዳልሆነ ይልቁንስ ብዙ የሚሠራበት እንዳለ እና ብዙ ፈውስ እንደሚያስፈልግ ተማርኩ።

ሽማግሌ ዲ ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “በእርግጥ ጌታ ወደ ፍርድ ብቁ ሆኖ ለመምጣት በሚፈልግ፣ ድካምን በጥንካሬ ለመተካት ቀን ተቀን በቆራጥነት በሚደክም ይደሰታል። እውነተኛ ንስሐ፣ እውነተኛ ለውጥ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሊጠይቅ ይችላል፣ ነገር ግን በእንደዚህ ዓይነት ጥረት ውስጥ የሚያጠራ እና ቅዱስ የሆነ ነገር አለ። መለኮታዊ ይቅርታ እና ፈውስ ወደ እንደዚህ አይነት ነፍስ በቀላሉ ይፈስሳል።”

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት እያንዳንዱ ቀን በተስፋ እና በሚቻሉ ነገሮች የተሞላ አዲስ ቀን ነው። እኔ እና እናንተ እናታችን ሔዋን እንዳወጀችው “የመዳንን ደስታ”፣ ሙሉ የመሆንን ደስታ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን ማብቂያ የሌለው የፍቅር ስሜት ደስታ በየእለቱ ልናውቅ እንችላለን።

የሰማይ አባታችን እና አዳኛችን እንደሚወዷችሁ አውቃለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ዘር አዳኝ እና ቤዛ ነው። እርሱ ህያው ነው። በኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ፣ ከምንወዳቸው ጋር ፈውስን፣ ቤዛነትን እና የዘላለምን ህይወትን ለመምረጥ ነፃ እንድንሆን የኃጢአት እና የሞት እስሮች ለዘለዓለም ተሰበሩ። ስለእነዚህ ነገሮች የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ማቴዎስ19፥26ን ይመልከቱ።

  2. ከእግዚያብሄር ጋር አንዴ ቃል ኪዳን ከገባን ገለልተኛ ሃሳቦችን ለዘላለም እንተዋለን። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዲህ ያለውን ግንኙነት የፈጠሩትን አይተውም። በርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገቡ ልዩ የሆነ ፍቅር እና ምህረትን ማግኘት ይችላሉ። በእብራይስጥ ቋንቋ ያ የቃልኪዳን ፍቅር ሃሴድ (חֶסֶד) ይባላል” (ራስል ኤም ኔልሰን “The Everlasting Covenant [ዘለአለማዊው ቃል ኪዳን]፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) 5።

  3. እናንተ እና እኔ ወደዚያ መንገድ ስንገባ አዲስ የአኗኗር መንገድ ይኖረናል። በዚህም እንዲባርከን እና እንዲለውጠን የሚያስችለውን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር እንፈጥራለን። የቃል ኪዳኑ መንገድ ወደእርሱ እንድንመለስ ይመራናል። እግዚአብሄር በህይወታችን እንዲያሸንፍ ብንፈቅድ ያ ቃልኪዳን የበለጠ ወደእርሱ ወደመቅረብ ይመራናል። ቃልኪዳኖች ሁሉ አስገዳጅ እንዲሆኑ የታለሙ ናቸው። ዘላለማዊ ጥምረት ያለው ግንኙነት ይፈጥራሉ”(Russell M. Nelson, “The Everlasting Covenant,” 5)።

  4. አልማ 26፥35–36ን ይመልከቱ።

  5. አልማ 22፥18፦ “አንተን ለማወቅ ኃጢያቴን በሙሉ እተዋለሁ፣” ይመልከቱ።

  6. ሉቃስ 7፥47፤ በተጨማሪ ቁጥር 37–50ን ይመልከቱ።

  7. ስለቅዱስ ቁርባን በመናገር፣ ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዲህ አሉ፦

    ነገር ግን በተሰበረ ልብ እናመ በተዋረደ መንፈስ በቅዱስ ቁርባን ስርዓት ላይ በጥንቃቄ ስንዘጋጅና ስንካፈል፣ ከዚያ ቃልኪዳኑ የጌታ መንፈስ ሁሌም ከእኛ ጋር እንደሚኖር ነው። እናም የእኛ ቋሚ ጓደኛ በሆነው በሚያነፃው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኩል፣ የሀጢያቶቻችንን ስርየት ሁሌም ማቆየት እንችላለን” (“Always Retain a Remission of Your Sins,” Liahona, May 2016, 61–62)።

    “… ወደ አዳኙ በመምጣት እና በመንፈስ ዳግም መወለድ ሂደት ውስጥ፣ የመንፈስ ቅዱስን የመቀደስ ሃይል በህይወታችን መቀበል ነፍሳችንን ከኃጢአት የማንጻት ቀጣይነት ያለው እድል ይፈጥራል። ይህ አስደሳች በረከት በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ‘ምንም እርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ሊኖር አይቻለውምና’ [1 ኔፊ 10፥21]” [“Always Retain a Remission of Your Sins,” 61]።

    ሽማግሌ ቤድናር በ2023 የተልዕኮ አመራር ሴሚናር ላይ አስተምረዋል “እናም የእኛ ቋሚ ጓደኛ በሆነው በሚያነፃው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኩል፣ የሀጢያቶቻችንን፣ስርየት ሁሌም ማቆየት እንችላለን። ስለዚህ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የኃጢአታችን ስርየትን ለማቆየት ሁለተኛ፣ ሶስተኛ፣ አራተኛ፣ እንዲሁም ማለቂያ የሌላቸው እድሎችን ይሰጣል” [in “Teach to Build Faith in Jesus Christ, Elder Bednar Instructs,” Church News፣ ሰኔ 23፣ 2023 (እ.አ.አ)]።

  8. “ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ የክህነት ሥነ-ሥርዓቶችን አስፈላጊ ሚና አጠር አድርጎ ገልጿል፦ ‘ዳግመኛ መወለድ በእግዚአብሔር መንፈስ በሥርዓቶች በኩል ይመጣል።’ [Teachings of Presidents of the Church፥ Joseph Smith (2007), 95] ይህ ዘልቆ የሚገባ ገለጻ በመንፈስ ዳግም የመወለድ ሂደት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን እና የቅዱስ ስርዓቶችን ሚና ያጎላል። …

    “ቅዱሳን ሥርዓቶች በአዳኙ ወንጌል እና ወደ እርሱ በመምጣት እና በመንፈስ ዳግም መወለድን በመፈለግ ሂደት ውስጥ ማዕከላዊ ናቸው። …

    “ዳግም በተመለሰችው የጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉ የመዳን እና ከፍ ከፍ የመደረግ ስርዓቶች ከአምልኮ ሥርዓቶች ወይም የምልክት ተግባሮች የበለጡ ናቸው። ይልቁንም፣ የሰማይ በረከቶች እና ሀይሎች ወደ ግል ህይወታችን የሚፈሱባቸው የተፈቀደላቸው መስመሮችን ይመሰርታሉ። …

    “እግዚአብሔርን የመምሰል ኃይል እና በአዳኙ የሀጢያት ክፍያ በኩል የሚገኙትን በረከቶች ሁሉ ለማግኘት በቅንነት የተቀበልናቸው እና ያከበርናቸው ስርዓቶች አስፈላጊ ናቸው” (ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “Always Retain a Remission of Your Sins,” 59–60)።

  9. ዮሐንስ 10፥17–18; 3 ኔፊ 9፥22.ተመልከት።

  10. የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዮሐንስ 1፥16ያዕቆብ 6፥9ሙሴ 1፥39ን ይመልከቱ።

  11. አልማ 12፥33–34ን ይመልከቱ።

  12. ዮሐንስ 3፥16ን ይመልከቱ።

  13. 3 ኔፊ 9፥13

  14. “እርሱ እናንተን ይፈውሳችሁ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትመጡ እለምናችኋለሁ። ከሀዘን እና ፍርሃት ይፈውሳችኋል። ከዚህ አለም ቁስል ይፈውሳችኋል” (ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Answer Is Always Jesus Christ [መልሱ ሁል ጊዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው]፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2023 (እ.አ.አ)።

  15. ኢሳይያስ 51፥3፣ እንዲሁም ኢሳይያስ 58፥10–12ህዝቄል 36፥33–36ን ይመልከቱ።

  16. James E. Talmage, Jesus the Christ (1916), 265.

  17. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” 5–7፤ እንዲሁም በዚህ መልእክት ውስጥ የመጨረሻ ማስታወሻዎች 2 እና 3ን ይመልከቱ።

  18. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6፤ ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7–9ን ይመልከቱ።

  19. 1 ጴጥሮስ 2፥9፣ እንዲሁም አልማ 26፥16-17ን ይመልከቱ።

  20. አልማ 12፥15፤ አጽንኦት ተጨምሮበታል።

  21. አልማ 34፥17ን ይመልከቱ።

  22. 2 ቆሮንቶስ 7፥103 ኔፊ 9፥19–20፣ 15–22ን ይመልከቱ።

  23. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥4364፥7ን ይመልከቱ።

  24. ሞዛያ 27፥32–37አልማ 26፥30ን ይመልከቱ።

  25. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥32ን ይመልከቱ።

  26. አልማ 24፥8–10ን ይመልከቱ።

  27. ሮበርትኤል. ሚለት፣ Becoming New፥ A Doctrinal Commentary on the Writings of Paul [2022 (እ.አ.አ)]።

  28. ሲኤስ. ሊውስ፣ The Magician’s Nephew [1955 (እ.አ.አ)]።

  29. አብርሐም 4፥6-9ን ይመልከቱ።

  30. አልማ 12፥9–1026፥223 ኔፊ 26፥9ን ይመልከቱ።

  31. “የቃል ኪዳኑ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት ነው” (Russell M. Nelson, “The Everlasting Covenant,” 11፤ እንዲሁም በዚህ መልእክት ውስጥ የመጨረሻ ማስታወሻዎች 2 እና 3ን ይመልከቱ)።

  32. አልማ 24፥17–19ን ይመልከቱ።

  33. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥10ን ይመልከቱ።

  34. ያዕቆብ 4፥13ን ይመልከቱ። ድክመታቸውን የማያዩ አያድጉም። ድክመታችሁን ማወቅ በረከት ነው፣ ምክንያቱም ትሁት እንድትሆኑ እና እናንተን ጠንካራ ለማድረግ ሀይል ወዳለው አዳኝ ለመዞር እንድትቀጥሉ ይረዳችኋልና። መንፈስ እናንተን ማፅናናት ብቻ ሳይሆን በፍጥረታችሁ ውስጥ የኃጢያት ክፍያ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራበት ነው። ደካማ ነገርች ጠንካራ ይሆናል” (Henry B. Eyring, “My Peace I Leave with You,” Liahona, May 2017, 16)።

  35. ራስል ኤም ኔልሰን፣ “የተሻለ ማድረግ እንችላለን እንዲሁም የተሻልን መሆን እንችላለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 68።

  36. በመመሪያ እና በመንፈስ አማካኝነት፣ በቤተመቅደስ ውስጥ የሚስተላለፈው ሁሉም ትምህርት ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖረንን መረዳት ይጨምራል። በቅዱስ የክህነት ቃል ኪዳኖች አማካኝነት አስፈላጊዎቹ የእርሱ ስርዓቶች ከእርሱ ጋር ያጣምሩናል። ከዚያም በኋላ፣ ቃል ኪዳኖቻችንን ስንጠብቅ፣ በእርሱ ፈዋሽ፣ የሚያበረታ ኃይል ይባርከናል። በሚቀጥሉት ቀናት የእርሱን ኃይል እንፈልጋለን” [ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ቤተመቅደስ እና መንፈሳዊ መሰረታችሁ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2021 (እ.አ.አ)፣ 93-94]።

  37. 3 ኔፊ 9፥21

  38. 3 ኔፊ 9፥14

  39. ኤሪክ ደዋር፣ “Come Find His Rest” (መዝሙር፤ 2024) ማቴዎስ 11፥28–30ን ይመልከቱ።

  40. ዘዳግም 30፥20ዮሃንስ 11፥25ኢተር 3፥14ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥6፣ 13ን ተመልከቱ።

  41. “ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የሚከተለውን ቃል እገባላችኋለሁ። ሁኔታችሁ በሚፈቅድላችሁ መጠን በቤተመቅደሥ አዘወትራችሁ የማምለክን ያህል በበለጠ ሁኔታ የብረቱን በትር አጥብቃችሁ ለመያዝ የሚረዳችሁ ምንም ነገር የለም። የዓለም የጨለማ ጭጋግ ሲያጋጥማችሁ የበለጠ የሚጠብቃችሁ ምንም ነገር የለም። የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን እና የእርሱን የኃጢያት ክፍያ ምሥክርነት የበለጠ የሚያጠናክርላችሁ ወይም የእግዚአብሔርን ድንቅ ዕቅድ የበለጠ እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁ ምንም ነገር የለም። በህመም ጊዜ የበለጠ መንፈሣዊ ማፅናኛን የሚሠጥ ምንም ነገር የለም። ሠማያትን ይበልጥ የሚከፍት ምንም ነገር የለም። ምንም!” [ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “Rejoice in the Gift of Priesthood Keys፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024 (እ.አ.አ)]፣ 122።

  42. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣” 5።

  43. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “The Answer Is Always Jesus Christ,” 127፤ እንዲሁም የመጨረሻ ማስታወሻ 14ን በዚህ መልእክት ውስጥ ይመልከቱ።

  44. ዲ. ታድ ክርስቶፈርሰን፣ “The Divine Gift of Repentance፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2011 (እ.አ.አ)፣ 39 ይመልከቱ።

  45. ሙሴ 5፥11

  46. 2 ኔፊ 2፥26–28ን ይመልከቱ።