አጠቃላይ ጉባኤ
የእግዚአብሔር ተወዳጅ
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:31

የእግዚአብሔር ተወዳጅ

በእግዚአብሔር ፍቅር መሞላት ከሕይወት ማዕበሎች ይጠብቀናል፣ ነገር ግን አስደሳች ጊዜዎችን የበለጠ አስደሳች ያደርጋቸዋል።

ከመጀመሬ በፊት ሁለት ልጆቼ ከአትሮንሱ ሲናገሩ ሩሃቸውን ስተው ወድቀዋል፤ እኔም ሩሄን ስቼ እንደማልወድቅ ተስፋ አደርጋለሁ። ከወጥመዱ በር ባሻገር በአእምሮዬ ላይ ብዙ ነገሮች አሉ።

በቤተሰባችን ውስጥ ስድስት ልጆች ያሉ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ በጣም ተወዳጅ የሆንኩት ልጅ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ እየተባባሉ አንዳቸው በሌላው ላይ ያሾፋሉ። እያንዳንዱ ልጅ ለምን ከሌላው የተሻለ ተመራጭ እንደሆነ የሚገልፁ የተለያዩ ምክንያቶችን አለው። ለሁሉም ልጆቻችን ያለን ፍቅር ንጹህ፣ የሚያረካ እና የተሟላ ነው። አንዳቸውንም ከሌላው የበለጠ መውደድ አንችልንም—ምክንያቱም ከእያንዳንዱ ልጅ መወለድ ጋር በጣም ደሥ የሚለው ፍቅራችን ጨምሯል። የሰማይ አባቴ ለእኔ ያለውን ፍቅር በጣም የምገነዘበው እኔ ለልጆቼ ባለኝ ፍቅር አማካኝነት ነው።

እያንዳንዳቸው ከሁሉም በላይ ተወዳጅ የሆነ ልጅ እንደሆኑ ለማስረዳት የሚናገሯቸውን ነገሮች ሲለማመዱ፣ በቤተሰባችን ውስጥ ያልተስተካከለ መኝታ ቤት በፍፁም ኖሮ አያውቅም ብላችሁ አስባችሁ ይሆናል። በወላጅ እና በልጅ መካከል ያለው ፍፅምና የጎደለው ግንኙነት በፍቅር ላይ በማተኮር ይቀንሳል።

የሆነ ጊዜ፣ ምናልባት ወደማይቀረው የቤተሰብ ጭቅጭቅ እያመራን እንደሆነ ስገነዘብ፣ እንዲ አይነት ነገር እናገራለሁ፦ “እሺ፣ አደከማችሁኝ፣ ግን ማን እንደሆነ አልገልፅም፣ ከእናንተ ውስጥ የትኛው የእኔ ተወዳጅ ልጅ እንደሆነ ታውቃላችሁ።” ዓላማዬ ስድስቱም፣ እያንዳንዳቸው የአሸናፊነት ስሜት እንዲሰማቸው እና ቢያንስ እስከሚቀጥለው ጊዜ ሁሉን ካማከለው ግብግብ እንዲታቀቡ ነው!…

ለእርሱ ያለው ፍቅር በሆነ መንገድ ልዩ የሆነ ይመስል፣ ዮሐንስ በወንጌሉ ውስጥ ራሱን “ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር” ሲል ገልጿል። ይህ የሆነው፣ ዮሐንስ በኢየሱስ ሙሉ ለሙሉ ይወደደ እንደነበረ ስለተሰማው ነው ብዬ ማሰብ እወዳለሁ። ኔፊ፣ “በ እኔ ኢየሱስ እደሠታለሁ” ብሎ በጻፈ ጊዜ ተመሳሳይ ስሜት ተሠምቶኛል። አዳኙ ከዮሐንስ የበለጠ የኔፊ አዳኝ እንዳልሆነ እርግጥ ነው፣ ሆኖም ኔፊ “ከየእርሱ” ኢየሱስ ጋር ያለው ግንኙነት ግላዊ ባህሪ ያንን የፍቅር ቃል ወደመናገር መርቶታል።

ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም በግለሠብ ደረጃ እንደታየን እና እንደተወደድን ሊሰማን የምንችልባቸው ጊዜያት መኖራቸው አይገርምም? ኔፊ “የእኔ” ኢየሱስ ብሎ ሊጠራው ይችላል፣ እኛም እንዲሁ ማለት እንችላለን። የአዳኛችን ፍቅር “ከሁሉም በላይ፣ ልዑላዊ እናጠንካራ የሆነ የፍቅር ዓይነት” ነው፣ ስለዚህም “እስክንሞላ” ድረስ ይሰጠናል። መለኮታዊ ፍቅር በጭራሽ አያልቅም፣ እናም እያንዳንዳችን ውድ የሆንን ይበልጥ የተወደድን ነን። የእግዚአብሔር ፍቅር በቬን ዲያግራም ላይ እንዳሉ የጋራ ነገር ያላቸው ክበቦች አንድ ላይ የምንሆንበት ነው። ከእኛ የትኛውም ክፍላችን የተለየ ቢመስለን ፍቅሩ አንድነትን የምናገኝበት ነው።

ታላላቆቹ ትዕዛዛት እግዚአብሔርን እና በዙሪያችን ያሉትን መውደድ መሆኑ ያስደንቃል? ሰዎች አንዳቸው ለሌላቸው የክርስቶስን ዓይነት ፍቅር ሲያሳዩ ስመለከት፣ ያ ፍቅር ከእነርሱ ፍቅር የሚበልጥ ነገርን የሚይዝ የሆነ ያህል ይሰማኛል። በመለኮታዊ ፍቅር የተሞላ ነው። በዚህ መንገድ የምንችለውን ያህል፣ እርስ በርሣችን ሙሉ በሙሉ ስንዋደድ ሠማያትም ተፅዕኗቸውን ያሣርፉበታል።

ስለዚህ የምናስብለት ሰው ከየእግዚአብሔር ፍቅር የራቀ መስሎ ከተሠማን፣ ይህን መንገድ ልንከተል እንችላለን—እኛ ራሳችን ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ የሚያደርገንን ነገር በማድረግና ከዚያም ወደ እነርሱ እንድንቀርብ የሚያደርገንን ነገር በማድረግ፣ ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ሊነገር የማይችል ምልክት ነው።

ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሠማችሁ የሚያደርጓችሁ ሁኔታዎች ምን እንደሆኑ ብጠይቃችሁ እወዳለሁ። በየትኞቹ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚገኙ ጥቅሶች፣ የትኞቹ ልዩ የአገልግሎት ተግባራት? የት ቦታ ላይ ትገኛላችሁ? የትኞቹን ሙዚቃዎች እያዳመጣችሁ? ከማን ጋር ጊዜ ስታሣልፉ? አጠቃላይ ጉባኤ ከእግዚአብሄር ፍቅር ጋር ስለመገናኘት ለመማር ብዙ አጋጣሚዎችን የሚፈጥር ቦታ ነው።

ነገር ግን ምናልባት ከእግዚአብሔር ፍቅር በጣም ሩቅ እንደሆናችሁ ይሰማችሁ ይሆናል? ምናልባት በሀሳቦቻችሁ ላይ የሚመዝኑ የተስፋ መቁረጥ እና የጨለማ የተቀናበሩ ድምጾች፣ በጣም እንደቆሰላችሁ እና ግራ እንደተጋባችሁ፣ በጣም ደካማ እና ችላ እንደተባላችሁ የሚነግራችሁ፣ ሰማያዊ ፍቅርን በምንም እውነተኛ መንገድ ለማግኘት በጣም የተለያችሁ ወይም ግራ የተጋባችሁ እንደሆናችሁ የሚናገሩ መልእክቶች ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚያን ሃሳቦች ከሰማችሁ እባካችሁ ይህንን አድምጡ፦ እነዚያ ድምፆች የተሳሳቱ ናቸው። የምንወደው እና እንከን የለሽ አዳኛችን በፈቃዱ “የተቀጠቀጠ፣ የተሰበረ፣ [እና] የተሸረከተ” መሆኑን የሚያስታውሰንን መዝሙር በምንዘምርበት እና የተቆረሰውን ዳቦ በምንወስድበት ጊዜ፤ በምንም መንገድ ከሰማያዊው ፍቅር የሚያባርረንን ስብራትን ችላ ማለት እንችላለን። በእርግጥ ኢየሱስ በመሠበር የመጣን ሀፍረት ሁሉ ያስወግዳል። በመሠበሩ ምክንያት ፍፁም ሆነ፣ ስለዚህም ብንሠበርም ፍፁም ሊያደርገን ይችላል። የተሰበረ፣ ብቸኛ፣ የተሸረከተ እና የቆሰለ ነበር—እኛም እንደዚያው እንደሆንን ሊሰማን ይችላል—ከእግዚአብሔር ፍቅር ከተለየን ግን አይሠማንም። መዝሙሩ እንደሚለው “Broken people; perfect love,” [የተሰበሩ ሕዝቦች ፍፁም ፍቅር] የሚለው ግጥም ማለት ነው።

የምትወደዱ እንዳልሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጋችሁ ስለራሣችሁ አንድ ሚስጥር ልታውቁ ትችላላችሁ። ስለራሣችሁ ስለምታውቁት ነገር ምንም ያህል ትክክል ልትሆኑ ብትችሉም፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ለእናንተ የማይገኝ አድርጋችሁ በማሰባችሁ ተሳስታችኋል። በማንም ሌላ ሠው ላይ እንሆንበታለን ብለን ልናስብ በማንችልባቸው መንገዶች አንዳንድ ጊዜ በራሳችን ላይ ጨካኞች እንሆናለን እንዲሁም ራሳችንን አንታገስም። በዚህ ህይወት ውስጥ ብዙ የምንሰራው ነገር አለ፤ ነገር ግን ራስን መውቀስ እና በሐፍረት ራስን ማውገዝ ከዛ ዝርዝር ውስጥ አይገኙም። ምንም ያህል የተሳሳተ አካሄድ እንደተከተልን ቢሠማንም እጆቹ አላጠሩም። በፍፁም። ሁልጊዜም “ወደ እኛ ለመድረስ” እና እያንዳንዳችንን ለማቀፍ በበቂ ሁኔታ ረዥም ናቸው።

የመለኮታዊ ፍቅር ሙቀት ባልተሰማን ጊዜ፣ ትቶን ሄዷል ማለት አይደለም። እግዚአብሔር አንደበት ይህን ተናግራል፦ “ተራሮች ይፈልሳሉ፣ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቱ ግን [ከእኛ] አይፈልሥም።” ስለዚህ፤ ግልጽ ለማድረግ፣ ተራሮች እስኪፈልሡ እና ኮረብታዎች እስኪወገዱ ድረስ እርሱ ላይ ስለማንደርስ እግዚአብሔር መውደዱን አቁሟል የሚለው ሐሳብ በሕይወታችን ውስጥ ሊኖሩ ከሚችሉት የማብራሪያዎች ዝርዝር ውስጥ በጣም ወደ መጨረሻው ላይ መቀመጥ አለበት።!

የእግዚአብሔር ፍቅር እርግጠኛነት ማስረጃ የሆነውን ይህን የተራሮች ምሳሌነት በጣም ወድጄዋለሁ። ይህ ሃይለኛ ምሳሌነት፣ ራዕይን ለመቀበል ወደ ተራራ በሄዱ ሰዎች ዘገባ ውስጥ እና ኢሳይያስ “የእግዚአብሔር ቤት ተራራ” “በተራሮች ራስ ላይ ፀንቶ [ስለመቆሙ]” በሰጠው በመላው ማብራሪያ ላይ ይገኛል። የጌታ ቤት እጅግ ውድ የሆኑት ቃል ኪዳኖቻችን መቀመጫ እና ሁላችንም ከነገሮች የምናፈገፍግበት እንዲሁም አባታችን ለእኛ ያለውን ፍቅር ማሥረጃ የምንፈትሽበት እና በእርሱ የምንከበብበት ቦታ ነው። የጥምቀት ቃል ኪዳኔን በከፍተኛ ደረጃ መጠበቄ እና በሞት በተለዩዋቸው ሠዎች ወይም በገጠማቸው ተሥፋ መቁረጥ ምክንያት የሚያዝኑ ሰዎች ሳገኝ እና ስሜታቸውን እንዲቆጣጠሩ እና እንዲሰሩበት ለመርዳት ስሞክር ወደ ነፍሴ በሚመጣው መጽናኛም ተደስቻለሁ። እነዚህ ውድ በሆነው የቃል ኪዳን ፍቅር፣ በማያቋርጥ፣ ይበልጥ የምንሣተፍባቸው መንገዶች ናቸውን?

የእግዚአብሔር ፍቅር የማይርቀን ከሆነ፣ ፍቅሩ ሁልጊዜ የማይሰማን ለምንድነው? ምን አልባት መልስ እየጠበቃችሁ ከሆነ፣ ፦ ሙሉ ለሙሉ የሚያረካ መልስ የለኝም። ነገር ግን የተወደዱ መሆን የመውደድ ስሜት ከመሠማት ጋር በእርግጠኝነት አንድ አይደለም፤ ስለዚህም ለጥያቄያችሁ መልስ ለማግኘት ፍለጋ በምታደርጉበት ጊዜ ሊረዷችሁ የሚችሉ ጥቂት ሀሳቦች አሉኝ።

ምናልባት ከሀዘን፣ ከድብርት፣ ከመከዳት፣ ከብቸኝነት፣ ከተሥፋ መቁረጥ ወይም እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው ፍቅር እንዲሰማችሁ ባላችሁ ችሎታ ውስጥ ጣልቃ ከገቡ ከሌሎች ኃይለኛ ሁኔታዎች ጋር እየታገላችሁ ይሆናል። እንደዚያ ከሆነ፣ እነዚህ ነገሮች፣ የመሠማት ችሎታችንን ሊያደበዝዙ ወይም ሊሰሙን ይችሉ የነበሩትን ነገሮች እንዳይሠማን ሊያደርጉ ይችላሉ። ቢያንስ ለአንድ ወቅት፣ ምናልባት ፍቅሩ ላይሰማችሁ ይችላል እናም እውቀት ብቻውን የግድ በቂ ሊሆን የሚችልበት ወቅት ይሆናል። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፍቅር መግለጽን እና መቀበልን በተለያዩ መንገዶች በትዕግስት መሞከር ትችሉ ይሆን ብዬ አስባለሁ። ከፊታችሁ ካለው ከማንኛውም ነገር ራቅ ምናልባትም እንደገና ራቅ አሁንም ራቅ፣ ሰፋ ያለ መልክዓ ምድር እስክታዩ ድረስ፣ አሁንም ሰፋ ሰፋ እያደረጋችሁ፣ አስፈላጊ ከሆነ ቃል በቃል “ስለሰለስቲያል እስክታስቡ” ድረስ ራቅ ልትሉ ትችላላችሁ ምክንያቱም ከዋክብትን እያያችሁ እንዲሁም ለመቁጠር የማይቻል ዓለማትን እና በእነርሱም አማካኝነት ፈጣሪያቸውን እያስታወሣችሁ ስለሆነ ነው?

የወፎች ዝማሬ፣ በቆዳዬ ላይ ፀሀይ ሲያርፍ ወይም ንፋስ ሲነካኝ ወይም ዝናብ ሲወርድ ሲሰማኝ እና ተፈጥሮ በእግዚአብሔር ወደምደነቅበት ስሜት ሲከተኝ—እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ጋር ያለኝ ግንኙነት እንዲሠማኝ በማድረግ ረገድ ሚና ነበረው። ምናልባት የታማኝ ጓደኞች ማጽናኛ ይረዳ ይሆናል። ምናልባት መዝሙር? ወይም ማገልገል? ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁ ግንኙነት ለእናንተ ግልጽ የነበረበትን ጊዜ መዝግባችሁ ወይም በማስታወሻ ደብተር ላይ አስፍራችኋል? ምናልባት እፎይታን እና ግንዛቤን ለማግኘት ስትፈልጉ የምታምኗቸው ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት የሚያደርጉባቸን ምንጮች እንዲያካፍሏችሁ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ።

ኢየሱስ እናንተ እና እርሱ የምትገናኙበትን፣ በእርሱ ላይ ብቻ ትኩረት ልታታደርጉ የምትችሉበትን የግል ቦታ ቢመርጥ፣ ሌላ ማንም ሰው ሊሄድ የማይችልበትን ልዩ የሆነ በግላችሁ መከራ የምትቀበሉበትን፣ እርዳታ በጣም የምትፈልጉትን ቦታ ይመርጥ ይሆን ? ብዬ አስባለሁ። በጣም ብቸኝነት ስለተሰማችሁ በእውነት ብቻችሁን መሆን ባለባችሁ ሆኖም ብቻችሁን ያልሆናችሁበት የሆነ ቦታ፣ ምናልባትም እርሱ ብቻ የሄደበት ነገር ግን እዚያ ስትደርሱ እናንተን ለማግኘት ተዘጋጅቶ የሚጠብቅበት የሆነበት ቦታ። እርሱ እንዲመጣ እየጠበቃችሁት ከሆነ፣ አሁኑኑ እዚያ በአቅራቢያችሁ ሊሆን ይችል ይሆን?

ይህ የህይወታችሁ ወቅት በፍቅር የተሞላ እንደሆነ ከተሰማችሁ፣ እባካችሁ ያንን ፍቅር ራሣችን ጋር አናስቀረው፣ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለሁሉም ለማካፈል እንሞክር እንጂ። ፍቅሩን በየሄዳችሁበት አጋሩት። ከመለኮታዊ ኢኮኖሚ ተዓምራት አንዱ፣ የኢየሱስን ፍቅር ለማካፈል ስንሞክር፣ “ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል” በሚለው መርህ ዓይነት ራሣችንን በእሱ እየተሞላን እናገኘዋለን።

በእግዚአብሔር ፍቅር መሞላት በሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙ ማዕበሎች ይጋርደናል፣ነገር ግን በተጨማሪም አስደሳች ጊዜያቶችን የበለጠ አስደሳች ያደርግልናል—በሰማይ ላይ ፀሀይ ስትኖር የሚኖሩን አስደሳች ቀናት፣ ከነፍሳችን በምትወጣ ፀሀይ የበለጠ ብሩህ ይሆናሉ።

በእኛ ኢየሱስ እና በእርሱ ፍቅር “ሥር እና መሠረት” እንሁን። የእርሱ ፍቅር እና ሃይል በህይወታችን ውስጥ እንዲሠማን የሚያስችሉንን ተሞክሮዎች እንፈልግ እንዲሁም እንደ ውድ ሀብት እንያዛቸው። የወንጌል ደሥታ ለሁሉም ነው፦ደሥተኛ ለሆኑትም ለተዋረዱትም ብቻ አይደለም። ደሥታ ሁኔታዎቻችን የሚያቀርቡልን ሥጦታ ሣይሆን ዓላማችን ነው “እንድንደሰትና በእግዚአብሔርና በሁሉም ሰዎች ፍቅር እንድንሞላ” በቂ ምክንያት አለን። እንሞላ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ዮሐንስ 21፥20፤ በተጨማሪም ዮሐንስ 13፥2319፥2620፥221፥7ን ይመልከቱ።

  2. 2 ኔፊ 33፥6፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል።.

  3. ልግስና” የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት።

  4. በተቀደሰው ምድር፤ ማቲዎስ 14፥15–20። እና በአሜሪካ፤ 3 ኔፊ 27፥16

  5. ማቴዎስ 22፥35–40ን ተመልከቱ።

  6. 1 ዮሃንስ ወንጌል 4፥12ተመልከቱ።

  7. ለወጣቶች ጥንካሬ፦ ምርጫዎችን ለማድረግ መመሪያ “[ሌሎች] የሰማይ አባትን ፍቅር [በእኛ] በኩል እንዲሰማቸው” እንድንረዳ ይጠይቃል ([2022]፣ 12)።

  8. “Jesus of Nazareth, Savior and King,” Hymns, no. 181; see also Iኢሳያስ 53፥5ማቴዎስ 26፥26

  9. President Russell M. Nelson explained: “Just prior to [the Savior’s] crucifixion, He said that on ‘the third day I shall be perfected’ [Luke 13:32; ማብራሪያ ተጨምሮበታል።] ያንን አስቡት! The sinless, errorless Lord—already perfect by our mortal standards—proclaimed his own state of perfection yet to be in the future። His eternal perfection would follow his resurrection and receipt of ‘all power … in heaven and in earth’ [ማቲዎስ 28፥18፤ እንዲሁም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 93፥2–23]” (“Perfection Pending,” Ensign፣ ህዳር 1995(እ.አ.አ)፣ 87) ተመልከቱ። ነቢዩ ሞሮኒ ሁሉንም እንዲህ ሲል ጋብዟል፣ “እናም ለራሳችሁ ኃጢአተኝነትን በሙሉ ከካዳችሁ፣ በሙሉ ኃይላችሁ እና አእምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ እግዚአብሔርን ከወደዳችሁ፣ ፀጋው ለእናንተ ይበቃችኋል፣ በፀጋው በክርስቶስ ፍፁም ትሆናላችሁ።”(ሞሮኒ 10:32).

  10. “Savior of My Soul,” 2024 Youth Album, ChurchofJesusChrist.org.

  11. ኢሳይያስ 59፥1ን ይመልከቱ።

  12. “ሰላምን ለማግኘት ወዴት መዞር እችላለሁ?፣” መዝሙር፣ ቁጥር 129

  13. ኢሳይያስ 54፥10

  14. ለምሳሊእ ኔፊ፣ ( 1 ኔፊ 17፥7ን ተመልከቱ)፣ ሙሴ ( ዘጸአት 19:3ን ተመልከቱ)፣ አስራ አንዱ ሃዋሪያት ( ማቴዎስ 28፥16ን ተመልከቱ)፣ እና አዳኙ ( ማቴዎስ 14፥23ን ተመልከቱ)፤ እንዲሁም መዝምሙር 24፥3ን ተመልከቱ።

  15. ኢሳያስ 2፥2፤ እንዲሁም ቁጥር 3ን ይመልከቱ። ይህ ተምሳሌታዊነት በዓለም ዙሪያ ላሉ ልጆቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተመቅደሶችን በማቅረብ የጌታን አላማዎች እንዳስብ አድርጎኛል።

  16. My experience bears out the truth of President Nelson’s promise that the safest place to be living is inside our temple covenants (see “The Temple and Your Spiritual Foundation,” Liahona, Nov. 2021, 96).

  17. ፕሬዘደንት ኔልሰን አረጋግጠውልናል፡-

    በቤተመቅደሥ ውስጥ የምታሣልፉት ጊዜ ስለሰለሥቲያል እንድታስቡ እንዲሁም ስለእውነተኛ ማንነታችሁ፣ ወደፊት ማን መሆን እንደምትችሉ እና ለዘለዓለም ልትኖሩት ስለምትችሉት ህይወት እይታ እንድታገኙ ይረዳችኋል። የዘወትር የቤተመቅደሥ አምልኮ ራሳችሁን የምታዩበትን እንዲሁም ከእግዚአብሔር አስደናቂ እቅድ ጋር ተስማምታችሁ መኖር የምትችሉበትን መንገድ ያጎለብታል። ያንን ቃል እገባላችኋለሁ።

    “…በህመም ጊዜ የበለጠ መንፈሣዊ ማፅናኛን የሚሠጥ ምንም ነገር የለም። ሠማያትን ይበልጥ የሚከፍት ምንም ነገር የለም። ምንም!” (“Rejoice in the Gift of Priesthood Keys፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2024(እ.አ.አ)፣ 121፣ 122)።

  18. ሞዛያ 18፥8–10፣ 13ን ተመልከቱ። “The baptismal covenant is a public witness to Heavenly Father of three specific commitments: to serve God, to keep His commandments, and to be willing to take on the name of Jesus Christ. The other facets that are frequently associated with the baptismal covenant—that we ‘bear one another’s burdens,’ ‘mourn with those that mourn,’ and ‘comfort those that [are] in need of comfort’ [ሞዛያ 18፥8–9]—are fruits of making the covenant rather than part of the actual covenant. These facets are important because they are what a converted soul would naturally do” (Dale G. Renlund, “Stronger and Closer Connection to God through Multiple Covenants” [Brigham Young University devotional, Mar. 5, 2024], speeches.byu.edu).

  19. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ዘለአለማዊው ቃል ኪዳን፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)፣4–11።

  20. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 117-118።

  21. ማቴዎስ 16፣25

  22. ኤፌሶን 3፥17

  23. 2 ኔፊ 2፥25፤ ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ደስታ እና መንፈሳዊ መትረፍ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016(እ.አ.አ) ተመልከቱ።

  24. ሞዛያ 2፥4

  25. ሞሮኒ 7፥48ን ተመልከቱ።