አጠቃላይ ጉባኤ
በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ማተኮር
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:50

በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ማተኮር

የዓለምን ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች ችላ ብለን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ስናተኩር፣ ስኬታችን የተረጋገጠ ይሆናል።

በ1996 (እ.አ.አ)፣ በአትላንታ ጆርጂያ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በተካሂደው ኦሎምፒክ የናይጄሪያ የእግር ኳስ ቡድን የወርቅ ሽልማትን አገኙ። ፍጻሜው ሲጠናቀቅ፣ በያንዳንዱ የናይጄሪያ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በደስታ የተሞላ ህዝብ ፈሰሰ። ይህች 200 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሀገር ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ በቅጽበት ወደ ታላቅ ክብረ በዓል ተለወጠ! ስዎች ምግብ ሲበሉ፣ ሲዘፍኑ፣ እና ሲደንሱ በአየሩ ውስጥ የሚጋባ ደስታ እና ሃሴት ነበር። በዚያ ወቅት፣ ናይጄሪያ አንድ ሆና ነበር እናም ሁሉም ናይጄሪያዊ ናይጄሪያዊ በመሆኑ ተደስቶ ነበር።

ከኦሎምፒኩ በፊት፣ ይህ ቡድን ብዙ ችግሮች አጋጥሞት ነበር። ውድድሩ ሲጀምር ያገኙት የነበረው የገንዝብ ድጋፍ ተቋረጠ። ቡድኑ ተገቢ መሳሪያዎች፣ የስልጠና ቦታ፣ በቂ ምግብ እና የልብስ ማጠብ አገግሎቶች ሳይኖረው በውድድሩ ተካፈለ።

የናይጄሪያ የእግር ኳስ ቡድን ከወርቅ ሜዳልይ ጋር

ጀሮም ፕሬቮስት/ከጌቲ ምስሎች

በአንድ ወቅት፣ ከውድድሩ ለመሰናበት በጣም ተቃርበው ነበር፣ ነገር ግን የናይጄሪያ ቡድን አሸነፈ። ይህች ወሳኝ ቅፅበት እራሳቸውን የሚያዩበትን መንገድ ለወጠ። በዚህ አዲስ በተገኘው ልበ ሙሉነት እንዲሁም በግል እና በቡድን ጠንካራ ስራ፣ አንድነት እና ቆራጥነት፣ ብዙ የሚረብሹ ነገሮችን ችላ በማለት በማሸነፍ ላይ አተኮሩ። ይህ ትኩረት የወርቅ ሽልማትን አስገኘላቸው፤ ናይጄሪያውያንም “የህልም ቡድን” ብለው ሰየሟቸው። በ1996 (እ.አ.አ) ኦሎምፒክ የተሣተፈው የህልም ቡድን በናይጄሪያ ስፖርት ውስጥ መጠቀሱን ቀጥሏል።

የናይጄሪያ የህልም ቡድን

ዴቪድ ካነን/ኦል ስፖርት/ከጌቲ ምስሎች

የእግር ኳስ ቡድን ያጋጠማቸውን ቡዙ የሚረብሹ ነገሮች ችላ ማለትን እና በግባቸው ላይ ማተኮርን ሲማሩ፣ ካሰቡት በላይ ውጤታማ ሆኑ—እና ታላቅ ደስታን አገኙ። (እኛም በናይጄሪ ውስጥ የነበርነው እንዳገኘነው ደስታ!)

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አለማዊ የሚረብሹ ነገሮችን ችላ ስንል እና በክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ ስናተኩር፣ በሙሉ ከምናስበው የበለጠ ውጤትን—እንዲሁም ታላቅ የደስታ ስሜትን ለማግኘት እንደምንችል ማረጋገጫ ይኖረናል። ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “የህይወታችን ትኩረት … በኢየሱስ ክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ሲሆን፣ በህይወታችን ከተከሰተውም ወይም ካልተከሰተውም ሁኔታ ባሻገር ደስታ ሊሰማን ይችላል።

ለደቀመዝሙርነታችን በህይወታችን ወስጥ እየተከሰተ ካለው ወይም ሳይከሰት ከቀረው ሁኔታ ባሻገር በክርስቶስ ደስታን እንደንለማመድ በኢየሱስ ክርስቶስና በወንጌሉ ላይ የማተኮርን የፕሬዚዳንት ኔልሰንን ግብዣ ለማዳመጥ መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዳችንን እንዲረዳን እጸልያለው።

በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኙ በርካታ ዘገባዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ በማተኮር ህይወታቸውን ስለለወጡ ግለሠቦች ይገልፃሉ።

ወጣቱ አልማን አስቡበት። አመጸ እንዲሁም ከቤተክርስቲያኗ ጋር ተጋጨ። አባቱ አልማ ጾመ እና ጸለየ። መልአክ ተገለጠና ትንሹ አልማ ንስሃ እንዲገባ ነገረው። በዚያ ጊዜ አልማ “በተኮነነች ነፍስ ህመምም እንክዋ ተሰቃየ።” በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ጊዜ፣ ክርስቶስ ለአለም ኃጢአቶች ለመክፈል እንደሚመጣ አባቱ ያስተማረውን ትምህርት አስታወሰ። አዕምሮው ይህን ሀሳብ ሲይዝ፣ የእግዚአብሔርን ምህረት ለመነ። ውጤቱም ደስታ ነበር፣ ደስታውንም ሀያል ብሎ ገልጾታል! ምህረት እና ደስታ ወደ አልማ የመጡት እርሱ እና አባቱ በአዳኝ ላይ ስላተኮሩ ነው።

ከክርስቶስ እና ከወንጌሉ የራቁ ልጆች ላሏችሁ ወላጆች፣ በርቱ! ልጃችሁ ንስሃ እንዲገባ ለምን መልአክ እንደማይመጣ ከመጠየቅ ይልቅ፣ በልጃችሁ መንገድ ላይ ስጋ ለባሽ መልአክን ጌታ እንዳስቀመጠ እወቁ፦ ማለትም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሌላ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ወይም አገልጋይ ወንድም ወይም እህት። በጾም እና በጸሎት ከቀጠላችሁ፣ ለእግዚአብሔር የጊዜ ሰሌዳ ወይም የጊዜ ገደብ ካላስቀመጣችሁ፣ እና እርሱ ለመርዳት እጁን እንደዘረጋ ካመናችሁ፣ ይዋል ይደር እንጂ፣ ልጃችሁ ለማዳመጥ ሲመርጥ፣ እግዚአብሔር የልጃችሁን ልብ ሲነካው ታያላችሁ። ይህም የሚሆነ ክርስቶስ ደስታ ስለሆነ ነው፣ ክርስቶስ ተስፋ ስለሆነ ነው፤ እርሱ ወደፊት የሚመጡ መልካም ነገሮች ቃል ኪዳን ነው። ስለሆነም፣ ክርስቶስን ስለልጃችሁ እመኑት፣ ምክንያቱም እርሱ የእያንዳንዱ ወላጅ የእያንዳንዱ ልጅ ጥንካሬ ነው።

አንዴ የክርስቶስን ደስታ ከተለማመደ በኋላ፣ ትንሹ አልማ ከዛ ደስታ ጋር ኖረ። ነገር ግን ይህንን ደስታ በችግር እና በፈተና ውስጥ ጠብቆ የያዘው እንዴት ነበር? እንዲህ አለ፦

“እናም ከዚያን ጊዜ እስከአሁን ድረስ እንኳን፣ ነፍሳትን ወደ ንስሃ አመጣ ዘንድ፣ እኔ ወደ ቀመስኩት ታላቅ ደስታ እነርሱንም እንዲቀምሱ አመጣቸው ዘንድ፣

“… እናም … ጌታ በስራዬ ፍሬም እጅግ ታላቅ የሆነ ደስታን ይሰጠኛል። …

“እናም በሁሉም ዓይነት ፈተናና በሁሉም ዓይነት ስቃይ ተደግፌአለሁ።”

አልማ በክርስቶስ ደስታ ማግኘት የጀመረው በእርሱ እምነትን ሲለማመድ እና ምህረት ለማግኘት ሲያለቅስ ነበር። ከዚያም በኋላ፣ ሌሎች ይህንኑ ደስታ እንዲቀምሱ ለመርዳት በመስራት አልማ በክርስቶስ እምነትን ተለማመደ። እነዚህ ቀጣይነት ያላቸው ስራዎች የተለያየ አይነት ፈተናዎች እና ችግሮች ውስጥ ሆኖም እንኳን ለአልማ ታላቅ ደስታን አመጡለት። ምን መሰላችሁ፣ “ጌታ ጥረትን ይወዳል” እና በእርሱ ላይ ያተኮረ ጥረት በረከቶችን ያመጣል። ሆኖም፣ ሁሉም “በክርስቶስ ደስታ [ተውጦ]” ነበር።”

በመጽሐፈ ሞርሞን ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እና ወንጌሉን የህይወታቸው ትኩረት ያደረጉ እና ደስታን ያገኙ ሌላ ሰዎች የሔላምን ከተማ ያገኙት ሰዎች ናቸው—እሱም ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት እና የሐይማኖታቸውን ነጻነት የሚያጣጥሙበት ቦታ ነበር። ይህ ጻድቃን በመልካም ኑሮ የሚኖሩ ሰዎች በዘራፊ ቡድን ባርነት ተገዝተው ሃይማኖትን የመከተል መሠረታዊ ሰብዓዊ መብት ተነፍገዋል። አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ነገሮች በጥሩ ሰዎች ላይ ይከሰታሉ፦

“ጌታ ህዝቡን መግሰፅ ተገቢ መሆኑን አየ፣ አዎን፣ ትዕግስታቸውንና እምነታቸውን ፈተነ።

“ይሁን እንጂ—እምነቱን በእርሱ ያደረገ በመጨረሻው ቀን ከፍ ይላል። አዎን እናም ለዚህ ህዝብም እንደዚህ ነበር።”

እነዚህ ህዝቦች ፈተናቸውን እና ስቃያቸውን የተቋቋሙት እንዴት ነበር? በክርስቶስ እና በወንጌሉ ላይ በማተኮር ነበር። ችግራቸው ማንነታቸውን አልገለጸውም ነበር፤ ከዚያ ይልቅ እያንዳንዳቸው ወደ እግዚአብሔር ተመለከቱ ምክንያቱም እራሳቸውን እንደ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የቃል ኪዳን ልጅ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ስለገለጹ ነበር። ማንነታቸውን ሲያስታውሱ እና እግዚአብሔርን ሲጠሩ፣ በክርስቶ ሰላምን፣ ጥንካሬን እና በመጨረሻም ደስታን አገኙ።

“እናም አልማ እና ህዝቦቹ … ልባቸውን ወደ እርሱ አፈሰሱ፤ እናም እርሱ የልባቸውን ሐሳብ ያውቅ ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ የጌታ ድምፅ በስቃያቸው እንዲህ በማለት መጣ፥ ራሳችሁን አቅኑም መልካም መፅናኛ ይኑራችሁም፤ ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን አውቀዋለሁና፤ ከህዝቤም ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ እናም ከባርነት አስለቅቃቸዋለሁ።”

በምላሽም፣ ጌታ “በትከሻቸው … ሸክማቸውን አቀለለላቸው። … “እናም አሁን እንዲህ ሆነ በአልማና በወንድሞቹ ላይ የሆነው ሸክም ቀለለላቸው፣ አዎን፣ ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ እናም በደስታና በትዕግስት ለጌታ ፈቃድ ተቀባይ እንዲሆኑ ጌታ ብርታትን ሰጥቷቸዋል”። እነዚህ ቅዱሳን ችግራቸውን፣ ስቃያቸውን እና ፈተናቸውን በክርቶስ ደስታ እንዲዋጥ እንደፈቀዱ አስተውሉ! ከዚያም፣ በትክክለኛው ሰዓት፣ የሚያመልጡበትን መንገድ ለአልማ አሳየው፣ እናም አልማ—የእግዚአብሔር ነቢይ—ወደ ደህንነት መራቸው።

በክርስቶስ ላይ ስናተኩር እና የእርሱን ነቢይ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰንን ስንከተል፣ እኛም ወደ ክርስቶስ እና ከወንጌሉ ወደሚገኘው ደስታ እንመራለን። ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዲህ እንዳስተምረዋል፦ “ደስታ ሃያል ነው፣ እናም በደስታ ላይ ማተኮር የእግዚአብሄርን ሃይል ወደ ህይወታችን ያመጣል። በሁሉም ነገሮች እንደሚሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቁ አርያችን ነው፣ እርሱም ‘በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታገሰ’” [ዕብራውያን 12፥2]

የሽማግሌ ኤግቦ እናት
ሽማግሌ ኤግቦ ከእናቱ ጋር

እናቴ በቅርቡ አረፈች፣ ያም ለእኔ አስደንጋጭ ነበር። እናቴን እውዳታለሁ እናም እሷን በወጣትነቷ አጣታለው ብዬ አላቀድኩም። ነገር ግን በእሷ ማረፍ የተነሳ፣ ቤተሰቤ እና እኔ ሀዘንም ደስታም ተሰምቶናል። በእርሱ አማካኝነት እሷ እንዳልሞተች አውቃለሁ—አለች። እናም በክርስቶስ እና በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት እና ዳግም በተመለሱት የክህነት ቁልፎች ምክንያት አንድ ቀን አብሬያት እሆናለሁ። እናቴ የማጣቴ ሃዘን በክርስቶስ ደስታ ተውጧል! “ስለ ሰለስቲያልን ማሰብ” እና “እግዚአብሔር እንዲያሸንፍ መፍቀድ” በክርስቶስ ውስጥ በሚገኘው ደስታ ላይ ማተኮርን እንደሚያካትት እየተማርኩኝ ነው።

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” በማለት ቃል ገብቷል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።