አጠቃላይ ጉባኤ
እጁ እኛን ለመርዳት ዝግጁ ነው
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


10:13

እጁ እኛን ለመርዳት ዝግጁ ነው

በእምነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶች ስንቀርብ፣ እርሱም ሁልጊዜ ይገኛል።

በልጅነቴ፣ እንደ ቤተሰብ፣ በትውልድ አገሬ ቺሊ የባሕር ጠረፍ ላይ ወደሚገኝ የባሕር ዳርቻ ለመዝናናት ሄድን። በበጋው ወቅት ከቤተሰቤ ጋር በመደሰት ጥቂት ቀናትን ለማሳለፍ ጓጓሁ። በጣም ተደስቼ ነበር፣ ምክንያቱም በመጨረሻ ላይ ሁለቱ ታላላቅ ወንድሞቼ በውሃ ላይ ብዙውን ጊዜ ለመዝናናት ያደረጉትን ተቀላቅዬ ለማድረግ እንደምችል ስላሰብኩ ነው።

አንድ ቀን ወንድሞቼ ማዕበሉ ወደሚበተንበት ቦታ ለመጫወት ሄዱ፣ እናም እነሱን ለመከተል እኔ ትልቅ እና የበሰልኩኝ እንደሆንኩኝ ተሰማኝ። ወደዚያ አካባቢ ስሄድ፣ ማዕበሎቹ ከባህር ዳር ከታዩት የበለጠ ትልቅ መሆናቸውን ተረዳሁ። በድንገት፣ አንድ ማዕበል ሳላስበው በፍጥነት ወደ እኔ ቀረበ። የተፈጥሮ ሃይል እንደያዘኝ ተሰማኝ፣ እናም ወደ ጥልቅ ባህር ተጎተትኩ። ወደዛ ወደዚህ ስገላበጥ ምንም አይነት የመለያ ቦታ ማየት ወይም ሊሰማኝ አልቻለም። በምድር ላይ ያለኝ ቆይታ ወደ መገባደዱ እንደመጣ ሳስብ፣ አንድ እጅ ወደ ላይ እየጎተተኝ እንደሆነ ተሰማኝ። በመጨረሻም፣ ፀሀይን ማየትና ትንፋሼን መውሰድ ቻልኩኝ።

ወንድሜ ክላውዲዮ እንደ ትልቅ ሰው ለመሆን ያደረኩትን ሙከራ አይቶ እኔን ለማዳን መጣ። ከባህር ዳርቻው ብዙም አልራኩም። ምንም እንኳን ውሃው ጥልቀት የሌለው ቢሆንም፣ ግራ ተጋባሁ እንዲሁም ራሴን መርዳት እንደምችል አላወቅኩም ነበር። ክላውዲዮ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብኝ እና ከፈለግኩ ሊያስተምረኝ እንደሚችል ነገረኝ። የዋጥኩት ውሃ በሊትር የሚቆጠር ቢሆንም፣ ኩራቴ እና ትልቅ ልጅ የመሆን ምኞቴ ጠነከረ እና “በእርግጥ” አልኩት።

ክላውዲዮ ማዕበሎቹን ማጥቃት እንዳለብኝ ነገረኝ። እንደ ትልቅ የውሃ ግድግዳ ከሚመስለው ጋር ብፋለም በእርግጠኝነት እንደምሸነፍ ለራሴ ነገርኩ።

አዲስ ትልቅ ማዕበል ሲቃረብ ክላውዲዮ በፍጥነት “ተመልከተኝ፤ እንደዚህ ነው የምታደርገው” አለኝ። ክላውዲዮ ወደ መጪው ማዕበል ሮጦ ከመበተኑ በፊት ዘሎ ጠለቀ። በአጠላለቁ በጣም በመደመሜ የሚቀጥለውን መጪ ማዕበል መመልከት ረሳሁ። ስለዚህ እንደገና ወደ ባሕሩ ጥልቀት ተወሰድኩኝ እና በተፈጥሮ ኃይሎች ተወረወርኩ። ከጥቂት ሴኮንዶች በኋላ፣ አንድ እጅ የእኔን እጅ ያዘ፣ እና እንደገና ወደ ላይ እና አየር ወዳለበት ተሳብኩኝ። የኩራቴ ነበልባል እየጠፋ ነበር።

በዚህ ጊዜ ወንድሜ አብሬው እንድጠልቅ ጋበዘኝ። በግብዣው መሰረት፣ ተከተልኩት፣ እና አብረን ጠለቅን። በጣም የተወሳሰበን ትግል ድል ያደረኩኝ ያህል ተሰማኝ። በእርግጠኝነት፣ በጣም ቀላል አልነበረም፣ ነገር ግን ወንድሜ ላሳየው እርዳታ እና ምሳሌ ምክንያትእኔ ይህን ለማድረግ ችያለሁ። የእሱ እጅ ሁለት ጊዜ አዳነኝ፣ የእሱ ምሳሌ ትግሌን እንዴት መቋቋም እንደምችል እና በዚያ ቀን ድል እንዳደርግ አሳይቶኛል።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለሰለስቲያል እንድናስብ ጋብዘውናል፣ እናም ምክራቸውን በመከተል በበጋ ታሪኬ ላይ ተግባራዊ ማድረግ እፈልጋለሁ።

አዳኙ በጠላት ላይ ያለው ኃይል

ስለ ሰለስቲያል ካሰብን፣ ለማሸነፍ ካለን አቅም በላይ የሚመስሉ ፈተናዎች በህይወታችን ውስጥ እንደሚገጥሙን እንረዳለን። በሟች ጊዜያችን ለጠላት ጥቃት እንጋለጣለን። በዚያ የበጋ ቀን በእኔ ላይ ኃይል እንደነበራቸው ማዕበሎች ሁሉ፣ አቅም እንደሌለን ሊሰማን እና ለጠንካራ እጣ ፈንታ መሸነፍ እንፈልጋለን። እነዚያ “ተንኮለኛ ሞገዶች” ከጎን ወደ ጎን ሊያናውጡን ይችላሉ። ነገር ግን በእነዚያ ማዕበሎች እና በእውነቱ በሁሉም ነገሮች ላይ ስልጣን ያለው ማን እንደሆነ አትርሱ። ያም አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከማንኛውም የመከራ ሁኔታ ወይም አስከፊ ሁኔታ እኛን ለመርዳት ኃይል አለው። ወደ እርሱ መቅረባችን ቢሰማንም ባይሰማንም፣ ባለንበት ቦታ እና ሁኔታ ሊደርስልን ይችላል።

በእምነት ወደ እርሱ ስንቀርብ፣ እርሱ ሁል ጊዜ እዚያ አለ፣ እና በእርሱ ጊዜ፣ እጆቻችንን ለመያዝ እና ወደ ደህና ቦታ ለመጎተት እሱ ዝግጁ እና ፍቃደኛ ይሆናል።

አዳኙ እና የአገልግሎት ምሳሌው

ስለሰለስቲያል የምናስብ ከሆነ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን የአገልግሎት እንከን የለሽ ምሳሌ መሆኑን እንገነዘባለን። እሱ ወይም ደቀ መዛሙርቱ እርዳታ፣ መዳን ወይም መባረክ ለሚያስፈልገው ሰው እጃቸውን ሲዘረጉ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ለእኛ ምሳሌ አለ። በታሪኬ ውስጥ እንደነበረው፣ ወንድሜ እዚያ እንዳለ አውቅ ነበር፣ ግን በዚያ መኖሩ የሚበቃ አልነበረም። ክላውዲዮ በችግር ላይ እንደሆንኩኝ አወቀ፣ እንዲሁም ከውሀው ሊያወጣኝ ለመርዳት ፈለገ።

አልፎ አልፎ፣ ለተቸገረ ሰው ብቻ እዛ መሆን እንዳለብን እናስባለን፣ እና ብዙውን ጊዜ፣ ማድረግ የምንችለው ብዙ ነገር አለ። ዘለአለማዊ እይታ ማግኘታችን ለተቸገሩ ሌሎች ወቅታዊ እርዳታ ለመስጠት ራዕይን እንድንቀበል ይረዳናል። በመንፈስ ቅዱስ መመሪያ እና መነሳሳት ምን አይነት እርዳታ እንደሚያስፈልግ ለማወቅ እንችላለን፤፣ እርዳታዎችም ጊዜያዊ ድጋፍ እንደ ስሜታዊ ማጽናናትን፣ ምግብን፣ ወይም በእለት ተእለት ተግባራት ላይ እርዳታን፣ ወይም ሌሎች በሚያደርጉት የመንፈሳዊ ጉዞ ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ያከብሩ ዘንድ የሚዘጋጁበትን፣ ኪዳን የሚገቡበትን፣ እና እንዲያከብሩ መርዳትን ለማካተት ይችላሉ።

አዳኙ እኛን ለማዳን ዝግጁ ነው

ሊቀ ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ “ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ። … ፈራ። ሊሰጥምም ጀመረ፣” ከዚያም “ጌታ ሆይ አድነኝ ብሎ ጮኸ።” ኢየሱስ ጴጥሮስ በውሃ ላይ ወደ እርሱ ለመምጣት ያሳየውን እምነት ያውቃል። የጴጥሮስን ፍርሃትም ያውቅ ነበር። ታረኩ እንደሚናገረው፣ ኢየሱስ “ወዲያውም … እጁን ዘርግቶ ያዘውና” የሚከተሉትን ቃላት ተናገረው፦ “አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ?” የእርሱ ቃላት ጴጥሮስን ለመገሰጽ ሳይሆን እርሱ መሲሑ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መሆኑን ለማስታወስ ነው።

ስለሰለስቲያል የምናስብ ከሆነ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት አዳኛችን፣ ከአብ ጋር ጠበቃችን እና መዳኒታችን መሆኑን በልባችን ማረጋገጫ እናገኛለን። በእርሱ ላይ እምነትን ስንለማመድ፣ ከወደቅንበት ሁኔታ፣ ከችግሮቻችን ባሻገር፣ ከድካማችን እና ከዚህ የጊዚያዊ ህይወት ፍላጎታችን ያድነናል እናም ከስጦታዎች ሁሉ የላቀውን የዘለአለም ህይወት ስጦታ ይሰጠናል።

አዳኙ በእኛ ላይ ተስፋ አይቆርጥም

ወንድሜ በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተስፋ አልቆረጠም፣ ነገር ግን ለራሴ እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ መማር እንድችል ቀጠለ። እኔን ሁለት ጊዜ ማዳን ቢያስፈልገውም፣ ቀጠለ በመጀመሪያ ላይ መማር ባልችልም ቀጠለ። ያንን ፈተና አሸንፌ እንዲሳካልኝ ቀጥሏል። ስለሰለስቲያል የምናስብ ከሆንን፣ ለመማር፣ ለመለወጥ፣ ለማሸነፍ፣ ለመቋቋም ወይም ለማሳካት ከፈለግን አዳኛችን አስፈላጊውን ምንም ያህል ጊዜ እዛ እንደሚገኝ እንገነዘባለን።

የአዳኙ እጆች

ቅዱሳት መጻህፍት የአዳኝን እጆች ምልክት እና አስፈላጊነት ለዘለአለም እንዲታወስ ያደርጋሉ። በኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ፣ በመስቀል ላይ ለመስቀል እጆቹን በምስማር ቸነከሩ። ከትንሣኤው በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ በፍፁም አካል ተገለጠ፣ ነገር ግን በእጆቹ ያሉት ህትመቶች ማለቂያ ለሌለው መስዋዕቱን ለማስታወስ ይቀራሉ። መጀመሪያ ላይ ሊታየን ወይም ሊሰማን ባይችልም እንኳ፣ እጁ ሁል ጊዜ ለእኛ እዛ ይኖራል፣ ምክንያቱም እሱ በሰማይ አባታችን የተመረጠ፣ አዳኛችን፣ የሰው ዘር ሁሉ ቤዛ ነውና።

የተዘረጉት የአዳኙ እጆች

በእጆቻችን ውስጥ፣ በጄይ ብርያንድ ዋርድ

የሚያድኑት የአዳኙ እጆች

እግዚአብሔር እጅ፣ በዮንግሱንግ ኪም.

ስለሰለስቲያል የማስብ ከሆነ፣ በዚህ ህይወት ብቻችንን እንዳልተተውን አውቃለሁ። ችግሮችን እና ፈተናዎችን መጋፈጥ ቢገባንም፣ የሰማይ አባታችን ችሎታችንን ያውቃል እናም ችግሮቻችንን መሸከም ወይም ማሸነፍ እንደምንችል ያውቃል። የበኩላችንን መወጣት እና በእምነት ወደ እርሱ መዞር አለብን። የተወደደው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን ነው እና ሁልጊዜም በዚያ ይኖራል። በእርሱ ስም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ስለ ሰለስቲያል አስቡ!፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2023 (እ.አ.አ)፣ 118–20።

    “ምርጫዎችን በምታደርጉበት ጊዜ ረዘም ያለ— ዘላለማዊ እይታ እንዲኖራችሁ እጋብዛችኋለሁ። የዘለአለም ህይወታችሁ በእሱ ላይ ባላችሁ እምነት እና በኃጢያት ክፍያው ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስን አስቀድሙት። …

    “አጣብቂኝ ውስጥ ስትገቡ ስለ ሰለስቲያል አስቡ! በፈተና ስትፈተኑ፣ ስለ ሰለስቲያል አስቡ!” ህይወት ወይም የምትወዳቸው ሰዎች ሲያሳዝኗችሁ ስለ ሰለስቲያል አስቡ! አንድ ሰው ያለጊዜው ሲሞት ስለ ሰለስቲያል አስቡ። አንድ ሰው በአሰቃቂ ህመም ሲቆይ ስለ ሰለስቲያል አስቡ። የህይወት ጫናዎች ሲደራረቡባችሁ፣ ስለ ሰለስቲያል አስቡ! ልክ እንደኔ ከአደጋ ወይም ከጉዳት በማገገም ላይ ስትሆኑ፣ ስለሰለስቲያል አስቡ!”

  2. ማርቆስ 4፥35–41 ተመልከቱ።

  3. የሰማይ አባታችን እና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስፈልገን ጊዜ ሊረዱን እንደሚችሉ ብናምንም የእነርሱ እርዳታ ሁልጊዜ በምንጠብቀው መንገድ ላይመጣ ይችላል። እኛ እራሳችንን ከምናውቀው በላይ እንደሚያውቁን እና ለእኛ የሚበጀንን ድጋፍ እና እርዳታ በትክክለኛው ጊዜ እንደሚሰጡን ማመን አስፈላጊ ነው። “ልጄ ሆይ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥7)።

    የሚያጋጥሙን ፈተናዎች እና ችግሮች ፈተናን ለመቋቋም እና የተፈጥሮ ሰውን ለማሸነፍ ጥንካሬን እና ባህሪን እንድናዳብር ይረዱናል።

  4. ማቴዎስ 14፥31ማርቆስ 1፥315፥419፥27የሐዋርያት ስራ 3፥73 Nephi 18፥36 ተመልከቱ።

  5. ፕሬዚዳደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በአዲስ እና በተቀደሰ መንገድ እንድናገለግል ሲጋብዙን (“አገልግሎት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 100 ተመልከቱ)፣ ይህ አዲስ የአግልግሎት መንገድ ስለ እኔ እና እኔ ማቅረብ ስለምፈልገው ነገር ሳይሆን ሌሎች ስለሚያስፈልጋቸው ነገሮች መሆኑን እንድንረዳ ጠይቀውናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ባልንጀራችንን (ሉቃስ 10፥27ን ተመልከቱ) ከፍ ባለ እና ቅዱስ በሆነ መንገድ እንድንወድ እድል እየሰጠን ነው።

  6. ማቴዎስ 14፥29–30

  7. ማቴዎስ 14፥31

  8. ደስታን በእውነት ለመረዳት በህይወታችን ውስጥ የበረከቶችን ሚና መረዳት አለብን። የ“በረከቶች” ፍቺ ይህንን ጽንሰ-ሀሳብ ለማብራራት ይረዳል፡- “በረከት ለአንድ ሰው መለኮታዊ ውለታን መስጠት ነው። ለእውነተኛ ደስታ፣ ለደህንነት፣ ወይም ለብልጽግና የሚያበረክት ማንኛውም ነገር በረከት ነው” (የቅዱሳን ጽሑፎች መመሪያ፣ “መባረክ፣ ተባረከ፣ በረከት፣” የወንጌል ቤተ መጻሕፍት)። ዓለም ብዙውን ጊዜ እውነተኛ ደስታን ከጊዚያዊ ደስታ ጋር ግራ ያጋባል፣ ይህም ለአጭር ጊዜ የሚቅይ “ደስታን” ይመሳሰላል።

  9. ኢሳይያስ 49፥16 ይመልከቱ።