ንፋሱ መንፈሱን አላቆመም
ሌሎች የእግዚአብሔርን በረከቶች ለማግኘት በሚያደርጉት ጉዞ እድገት እንዲያደርጉ ልንረዳቸው እንችላለን።
በ2015 (እ.አ.አ) በፔርናምቡኮ፣ ብራዚል ግዛት ውስጥ 62 የጄ.ሩብን ክላርክ የህግ ማህበር አባሎች በአራት የሞግዚት ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን የህግ ችግሮች በመመርመር ላይ ከግዛቱ የአቃቤ ህግ ቢሮ ጋር ተባበሩ። በአንድ ቅዳሜ ለአምስት ሰዓታት እነዚህ የህግ ጠበቃዎች በማህበረሰቡ በተግባር ተረስተው የነበሩ ከ200 በላይ የሆኑ ነዋሪዎችን አንድ በአንድ፣ ቃለ መጠይቅ አደረጉ።
በቃል መጠይቃቸው ወቅት እንደ ችላ ማለት፣ መበደል እና ፈንዶችን አላግባብ መጠቀም ያሉ በአዛውንት ነዋሪዎች ላይ የሚፈፀሙ ብዙ ወንጀሎችን አጋለጡ። የዚህ የህግ ማህበር ዋናው አካል ድሆችን እና የተቸገሩትን መንከባከብ ነው። ከሁሉት አመት በኋላ አቃቤ ህጉ የሚመለከታቸው አካላት ላይ በውጤታማነት ክስ መሰረተ።
የእነሱ እርዳታ ንጉስ ቢኒያም እንዲህ ላስተማረው ጥሩ ምሳሌ ነው፣ “እናንተ ሰዎችን በምታገለግሉበት ጊዜ እግዚአብሔርን ብቻ እያገለገላችሁ እንደሆነ እንድትማሩ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እናገራችኋለሁ።”
በነጻ አገልግሎት ፕሮጀክት ወቅት እኔ በግል ቃለ መጠይቅ ያደረኩላት ሉሲያ የምትባል አንድ የ93 አመት ልበቅን አዛውንት ነበረች። አገልግሎታችንን እያመሰገነች በመቀለድ “አግባኝ!” አለች።
በመገረም፣ እንዲህ ብዬ ምላሽ ሰጠሁኝ፦”ያቺን ቆንጅዬ ወጣት ሴት ተመልከቺ! ባለቤቴ እና የግዛቱ አቃቤ ህግ ነች።”
በፍጥነት እንዲህ አለች፣ “እና ምን ችግር አለው? ወጣት እና ቆንጆ ነች እናም በቀላሉ እንደገና ማግባት ትችላለች። ለእኔ ያለኸኝ አንተ ብቻ ነህ!”
አስደናቂ ነዋሪዎቹ ሁሉም ችግራቸው በዚያ ቀን አልተቀረፈም። ካለምንም ጥርጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መከራን መጋፈጣቸውን ቀጠሉ ልክ እንደ ያሬዳውያን በጀልባቸው ውስጥ ወደ ቃልኪዳኗ ምድር በአስቸጋሪው ጉዞ ላይ “በተራራማው ማዕበል እናም ደግሞ በኃያሉ ንፋስ ምክንያት በመጣው በታላቁና ኃይለኛው አውሎ ንፋስ … ባህሩ ውስጥ ተቀብረው ነበር።”
ነገር ግን በዚያ ቅዳሜ፣ የአረጋውያን መኖሪያ ማዕከሉ ነዋሪዎች ምንም እንኳን በምድር ባይታወቁም ለቀላል ጸሎት እንኳን ምላሽ በሚሰጠው በአፍቃሪው የሰማይ አባት በግል እንደሚታወቁ አወቁ።
የመምህሮች መምህር ያሬዳውያን ወደ ቃል ኪዳን በረከቶች እንዲገፉ “ኃይለኛ ንፋስ” አስነሳ። ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ፣ በጌታ እጆች ውስጥ እንደ ያማይጎዳ ሃይለኛ ንፋስ ለማገልገል መወሰን እንችላለን። ልክ ያሬዳውያን ወደ ቃል ኪዳኑ ምድር እንስኪደርሱ ድረስ “ንፋሱ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር መንፈሱን በጭራሽ [እንዳላቆመው]” የእግዚአብሔርን በረከቶች በመቀበያ መንገዳቸው ላይ ሌሎችን መርዳት እንችላለን።
ከብዙ አመታት በፊት፣ ውድ ባለቤቴ ክሪስ እና እኔ ለኤጲስ ቆጶስ ለጥሪዬ ቃለ መጠይቅ ተደርገን ነበር፣ የካስማው ፕሬዝደንታችን አማካሪዎች የሚሆኑ ስሞችን በጸሎት እንዳስብ ጠየቀኝ። ያቀረብኩትን ስሞች ከሰማ በኋላ ስለ አንዱ ወንድም የተወሰነ ነገሮችን ማወቅ እንደለብኝ ተናገረ።
መጀመሪያ፣ ይህ ወንድም ማንበብ አይችልም። ሁለተኛ፣ አባሎችን ለመጎብኘት መኪና የለውም። ሶስተኛ፣ ሁሌም—ሁሌም—ቤተክርስቲያን ውስጥ የጸሃይ መነጽር ያደርጋል። ፕሬዚዳንቱ ሃቀኛ ስጋቶች ቢኖሩትም፣ አሁንም እንደ አማካሪዬ ማቅረብ እንዳለብኝ ጠንካራ የሆነ ስሜት ተሰማኝ እና ፕሬዚዳንቱም ደገፉኝ።
በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ እኔ እና አማካሪዎቼ ድጋፍ በተሰጠን እሁድ ቀን በአባሎች ላይ ይታይ የነበረው መገረም ግልጽ ነበር። ይህ ውድ ወንድም ከላይ የሚበሩ መብራቶች በሃይል የጸሃይ መነጽሩ ላይ እያንጸባረቁ ቀስ ብሎ ወደ መድረኩ ሄደ።
ከእኔ ጎን ከተቀመጠ በኋላ እንዲህ በማለት ጠየኩት፣ “ወንድም፣ የዕይታ ችግር አለብህ?”
“የለብኝም” ብሎ መለሰ።
“እና ለምንድን ነው በቤተክርስቲያን ውስጥ የጸሃይ መነጽር የምትጠቀመው?” ብዬ ጠየኩኝ። “ጓደኛዬ፣ አባሎች አይንህን ማየት ይፈልጋሉ አናም አንተም የበለጠ ልታያቸው ይገባል።”
በዚያን ወቅት፣ የጸሃይ መነጽሩን አወለቅ እንዲሁም ከዚያ በኋላ በቤተክርስቲያን አልተጠቀመውም።
ይህ ውድ ወንድም ከኤጲስ ቆጶስ እስክወርድ ድረስ ከአጠገቤ በመሆን አገለገለ። ዛሬ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ በታማኝነት ማገልገሉን ቀጥሏል እንዲሁም ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ላለን መሰጠት እና ቁርጠኝነት ምሳሌ ነው። ነገር ግን ከብዙ አመታት በፊት፣ በቤተከርሲያን የኋላ አግዳሚ ላይ ይቀመጥ የነበረ የተረሳ የማይታወቅ የጸሃይ መነጽር አድራጊ ነበር። ዛሬ ተረስተው የተቀመጡ ስንት አማኝ ወንድሞች እና እህቶች በመካከላችን አሉ ?እያልኩኝ ብዙ ጊዜ እጠይቃለሁ።
የምንታወቅም ይሁን የተረሳን፣ ፈተናዎች ወደ እያንዳንዳችን መምጣታቸው አይቀርም። ወደ አዳኙ ስንመለስ፣ “መከራ[ችንን] ወደ ጥቅ[ማችን] [መለወጥ]” እና መንፈሳዊ እድገታችንን በሚያመቻች ሁኔታ ለፈተናችን ምላሽ በመሥጠት ሊረዳን ይችላል። ለሞግዚት ቤት ነዋሪዎችም ይሁን፣ በስህተት የተፈረደበት የቤተክርስቲያን አባል ወይም ማንኛውም ሰው፣ ተስፋን በማምጣት እና ሊሎችን ወደ ቃል ኪዳኑ መንገድ በመምራት “መንፈሱን በጭራሽ [እንደማያቆመው ንፋስ]” መሆን እንችላለን።
ውድ ነቢያችን ፕሬዚዳንት ረስል ኤም. ኔልሰን፣ ለወጣቶች የሚያስደስት እና የሚያነሳሳ ግብዣ ያደረጉትእንዲህ ነበር፦ “ እያንዳንዱ ብቁ የሆነ፣ የሚችል ወጣት ወንድ ልጅ በሚስዮን ለማገልገል እንዲዘጋጅ እና እንዲያገለግል ጌታ እንደጠየቀ አበክሬ አረጋግጣለሁ። ለኋለኛው ቀን ቅዱሣን ወጣት ወንዶች፣ ሚስዮናዊ አገልግሎት የክህነት ሃላፊነት ነው። … እናንተ ወጣት እና የምትችሉ እህቶች፣ ሚስዮን ሃያል የሆነ፣ ነገር ግን በአማራጭነት የቀረበ፣ እድል ነው።”
በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች እና ሴቶች ለጌታ ትንቢታዊ ጥሪ ሚስዮናውያን በመሆን ለማገልገል ምላሽ ይሰጣሉ። ብሩህ ናችሁ፣ እንዲሁም ፕሬዚዳንት ኔልሰን እንዳሉት “ቀደም ካሉት ከየትኛውም ትውልዶች ይበልጥ በአለም ላይ ተጽእኖ አላችሁ።” በእርግጥ፣ ወደ ሚስዮን ማሰልጠኛ እግራችሁ ልክ እንደረገጥ የእራሳችሁ የተሻለ ሰው ትሆናላችሁ ማለት አይደለም።
በምትኩ፣ እንደ ኔፊ እንዲህ ሊሰማችሁ ይችላል፣ “ማድረግ [ያለባችሁን ነገሮች ቀድማችሁ ሳታውቁ በመንፈስ የምትመሩ]። ይሁን እንጂ፣ [እናንተም] ወደፊት [ሄዳችሁ]።”
ምናልባት ልክ እንደ ኤርምያስ ፍራቻ ሊሰማችሁ ይችላል እና ይህን ልትሉ ትችላላችሁ፣ “ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም።”
ግላዊ ድክመታችሁን በመመልከት እንደ ሙሴ እንዲህ ልታለቅሱ ትፈልጉ ይሆናል፦ “ጌታ ሆይ፣ እኔ አፌ ኮልታፋ ምላሴም ጸያፍ … ነው።”
ማንኛችሁም ውድ እና ሃያል ወጣት ወንዶች እና ሴቶች እንደዚህ አይነት ሃሳብ አሁን ካላችሁ፣ ጌታ ይህን መልስ እንደሰጠ አስታውሱ፣ “ወደምሰድህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና ብላቴና ነኝ አትበል” እናም ቃል ገብቷል፣ “እንግዲህ ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ”
ከተፈጥሮ ማንነታችሁ ወደ መንፈሳዊነት የምትቀየሩበት ሂደት “በትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ፣ በስርዐት ላይ ስርዐት” ይከሰታል። በቀን ተቀን ጸሎት፣ በእምነት፣ በትክክለኛ ታዛዥነት እና በጠንካራ ስራ በሚስዮን ላይ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል በቅንነት ስትጥሩ “[በተደጋጋሚ ታገኛላችሁ፣ ንስሃን ታስተምራላችሁ እናም የተለወጡትን ታጠምቃላችሁ]።”
የስም መለያን ብታደርጉም አንደ አንድ ጊዜ የማትታወቁ ወይም የተረሳችሁ መስሎ ሊሰማችሁ ይችላል። ይሁን እንጂ፣ በግል የሚያውቃችሁ ፍጹም የሆነ የሰማይ አባት እና የሚወዳችሁ አዳኝ እንዳላችሁ ማወቅ ይኖርባችኋል። ምንም ፍጹም ባይሆኑም በግል የመለወጥ ጉዟችሁ ላይ ሊመሯችሁ እንደ “መንፈሱን በጭራሽ [እንደማያቆመው ንፋስ]” የሚያገለግሉ የሚስዮን መሪዎች ይኖራችኋል።
“ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር” ውስጥ ሚስዮናችሁን ታገለግላላችሁ፣ በመንፈስ እንደገና ትወለዳላችሁ እናም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስትቀርቡ የእርሱ የእድሜ ልክ ደቀመዝሙር ትሆናላችሁ። መቼም እንዳልተረሳችሁ ታውቃላችሁ።
ምንም እንኳን አንድ አንዶች ለማረፍ “ብዙ ዘመን” ቢጠብቁም፣ ሊረዳቸው የሚችል “[ማንም] ሰው [ስለሌለ]” ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሰው በእርሱ እንዳልተረሳ አስተምሮናል። በተቃራኒው፣ በእያንዳንዱ ምዳራዊው አገልግሎቱ ውቅት አንዱን የመፈለግ ፍጹም ምሳሌ ነው።
እያንዳንዳችን እና በዙሪያችን ያሉት ሰዎች—በየቀኑ የሚዘፍቀንን የየራሳችንን የተቃርኖ ማዕበሎች እና የሙከራ ሞገዶች እንጋፈጣለን። ነገር ግን፣ “ንፋሱ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር መንፈሱን በጭራሽ አላቆመም … እናም ከንፋሱ ፊትም እንደዚህ [እንገፋለን]።”
እያንዳንዳችን የዚህ ንፋስ አካል መሆን እንችላለን—ያሬዳውያኖችን በጉዟቸው ላይ የረዳቸው ተመሳሳይ ንፋስ እናም በእኛ እርዳታ አማካኝነት የማይታውቁትን እና የተረሱትን የሚባርክ ተመሳሳይ ንፋስ ወደ እራሳቸው የቃል ኪዳን ምድራቸው ላይ እንዲደርሱ የሚረዳ።
ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ፊት አማላጃችን እንደሆነ እመሰክራለው። ህያው አምላክ ነው እናም በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ ሁሌም እንደሚመራን ጠንካራ ንፋሰ ይሆናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።