የአመፅ መሳሪያዎቻችንን መቅበር
በሕይወታችን ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ የሚነሳውን ማንኛውንም አመፅ—በጣም ጥልቅ በሆነ ቦታ ውስጥ—እንቀብር እና በፈቃደኛ ልብ እና በፈቃደኝነት አእምሮ እንተካው።
መጽሐፈ ሞርሞን በአጠቃላይ ከክርስቶስ ልደት ከ90 አመት በፊት የንጉስ ሞዛያ ልጆች ለ14 አመት ያህል የሚሆን ሚሲዮንን በላማናዊያን ምድር ላይ ጀመሩ። ለብዙ ትውልዶች የላማናዊያንን ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ አስተምህሮቶች እንዲያምኑ ለማድረግ ያልተሳኩ ጥረቶች ተደርገዋል። ሆኖም ግን፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በመንፈስ ቅዱስ ተአምራዊ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ላማናዊያን ተለውጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ሆነዋል።
“እናም ጌታ ህያው እንደሆነ፣ በርግጥም ብዙዎች እንዳመኑትም፣ ወይም በራዕይና በትንቢት መንፈስ፣ እናም በውስጣቸው ድንቅ ስራን በሚሰራው በእግዚአብሔር ኃይል መሰረት በአሞንና በወንድሙ ሰበብ ብዙዎች እውነቱን ወደ ማወቅ የሚመጡት—አዎን እንዲሁም እላችኋለሁ፣ ጌታ ህያው እንደሆነ፣ በስብከታቸው አምነው የነበሩ ላማናውያን ሁሉ፣ እናም ወደጌታ ተለውጠው የነበሩ፣ መንገዳቸውንም [እንዳልሳቱ]” እናነባለን።
የእነዚህ ሰዎች ዘላቂ መለወጥ ቁልፍ፣ በቀጣዩ አንቀጽ ላይ ተገልጻል፡- “እነርሱም ፃድቃን ህዝቦች ሆኑ፣ ከእንግዲህ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲሁም ከወንድሞቻቸው ጋር እንዳይጣሉ የአመፅ መሣሪያቸውን ጣሉ።”
ይሄ “የአመፅ መሳሪያ” የሚለው አገባብ፣ ቃል በቃል እና ምሳሌያዊ የሆነ ትርጉም አለው። ትርጉሙም ሰይፋቸውን እና ሌላ የጦርነት መሳሪያዎችን እንዲሁም ለእግዚአብሔር እና ለትእዛዛቶቹ አልታዘዝም ባይነት ማለት ነው።
የእነዚህ በወንጌሉ የተለወጡ ላማናዊያን ንጉስ እንዲህ ሲል ገልጾታል፦ “እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ … ለኃጢአታችን ሁሉ እንዲሁም በርካታ ግድያዎችን ለፈፀምንበት ንስሃ ለመግባት፣ እናም እነዚህን እግዚአብሔር ከልባችን እንዲያስወግድልን ለማድረግ፣ የምንችለውን ሁሉ ይህ ብቻ ስለነበረ፣ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት በበቂ ሁኔታ ንስሃ ገብተን እርሱም እድፋችንን ሊወስድ በሚችልበት ሁሉ ልናደርግ የምንችለው ሁሉ ይህ ነበርና።”
የንጉሱን ቃላቶች አስተውሉ—ያደረጉት እውነተኛ ንሰሃ ያመራው ለኃጢያታቸው ይቅር መባልን ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር የኃጢያታቸውን እድፍ እንዲሁም ኃጢያትን የማድረግ ፍላጎታቸውን ጨምሮ ከልባቸው ወስዶ ነበር። እንደምታውቁት፣ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ያላቸውን ማንኛውንም እድል አደጋ ላይ ከመጣል ይልቅ ጎራዴዎቻቸውን ቀበሩ። በተለወጠ ልብ የሚዳሰሱትን መሳስሪያዎቻቸውን ሲቀብሩ ሐጥያት ለመስራት ያላቸውን ፍላጎታቸውን ጨምሮ ቀብረውታል።
የኃጢያት እድፍ እንዲሁም ኃጢያትን የማድረግ ፍላጎታችን ከልባችን እንዲወሰድ “ነገሩ ምንም ይሁኑ ምን የአመጽ መሳሪያዎ[ቻችንን] ወደ መሬት ለመጣል” እና በወንጌሉ “ወደ ጌታ የተለወጥን” ለመሆን ይህንን ንድፍ ለመከተል ምን ማድረግ እንደምንችል እራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን።
አመጽ ንቁ ወይም ተገብሮ ሊሆን ይችላል። በፍቃደኝነት የማመፅ ትክክለኛ ምሳሌ ከዚህ ምድራዊ ህይወት በፊት በነበረው አለም ላይ የአባትን የቤዛነት እቅድ የተቃወመው ከዚያም ሌሎችም እንዲቃወሙ ያነሳሳው ሳጥናኤል ነው፣ “በዛም ቀን ብዙዎች ተከተሉት።” በእኛ ጊዜ የሱን የማያቋርጠውን የአመፅ ተጽእኖ መለየት ከባድ አይደለም።
በመፅሓፈ ሞርሞን ውስጥ ቅዱስ ያልሆነ ፀረ ክርስቶስ የሆኑ የሶስትዮሽ ቡድን ምሳሌ—ሼረም፣ ኒሆር እና ኾሪሆር እግዚአብሔር ላይ ንቁ የሆነ የማመፅ ምሳሌን ያሳያሉ። የኔሆር እና የቆሪሆር ዋናው ጥናት ኃጢአት የሚባል ነገር እንደሌለ ስለዚህም ንሰሓ መግባት አያስፈልግም አዳኝም የለም የሚል ነበረ። “እያንዳንዱ ሰው በተሰጥኦው ይበለፅጋል፣ እያንዳንዱም ሰው በጉልበቱ ያሸንፋል፤ እናም ማንም ሰው ያደርገው የነበረው ሁሉ ወንጀል አልነበረም።” ፀረ- ክርስቶስ ስረአቶችን እና ቃልኪዳኖችን በጥንት ካህናት ስልጣን ለመያዝ የሚደረጉ ናቸው በማለት ሓይማኖታዊ ስልጣንን ይቃወማል።”
በሓለኛው ቀን የንቁ አመፅ ምሳሌ የነበረ ነገር ግን መጨረሻው አስደሳች የሆነ የውልያም ደብሊው ፈልፕስ ታሪክ ነው። ፌልፕስ ቤተክርስቲያኗን የተቀላቀለው በ1831 (እ.አ.አ) ሲሆን እንደ የቤተክርስቲያኗ አሳታሚ ተመርጦ ነበር። ብዙ ቀደም ያሉ የቤተክርስቲያን እትሞችን እንዲስተካከሉ አድርጓል፣ ትላልቅ መዝሙሮችን ጽፋል እንዲሁም ለጆሴፍ ስሚዝ እንደ ጸሃፊ በመሆን አገልግሏል። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በሙዙሪ ውስጥ ለነብዩ መታሰር ሰበብ ሊሆን በቻለው በሙዙሪ ፍርድ ቤት ጆሴፍ ስሚዝ ላይ በሐሰት እስከመመስከር ድረስ ቤተክርስቲያኗን እና ነብዩን ተቃውማል።
በኋላም ፌልፕስ ለጆሴፍ የይቅርታ ደብዳቤ ጻፈ። “ያለሁበትን ሁኔታ አውቃለሁ፣ እናም እግዚያብሔርም ያውቀዋል እናም ጓደኞቼ የሚረዱኝ ከሆነ ለመዳን እፈልጋለሁ፡፡”
ነብዩም ለደብዳቤው ምላሽ ሲሰጥ እንዲህ ሲል አረጋገጠ፦ “ባንተ ጸባይ ምክንያት ብዙ እንደተሰቃየን እውነት ነው። … ነገር ግን፣ ጽዋው ተጠጥታል፣ የሰማይ አባታችን ፈቃድ ተፈጽማል፣ እና እስካሁን በህይወት አለን። … ጦርነቱ አልፏልና ወዲህ ና ውድ ወንድሜ፣ በመጀመሪያ ጓደኞች የሆንን በመጨረሻም እንደገና ጓደኞች እንሆናለን፡፡”
በእውነተኛ ንስሓ፣ ዊሊያም ፌልፕስ “የአመፅ መሳሪያውን ቀበረ፣” በድጋሚ እንደ የቤተክርስቲያን አባል ተቀባይነትን አገኘ፣ በድጋሚም ከቤተክርስቲያና ወጥቶ አያውቅም።
ምን አልባትም እግዚአብሔር ላይ ይበልጥ ግልጽ ያልሆነው አመፅ፣ በሕይወታችን ውስጥ ያለውን ፈቃዱን ችላ ማለት ነው። ንቁ ወይም ግልጽ የሆነ አመፅን የማይቀበሉ ብዙ ሰዎች መለኮታዊ ምሪትን ታሳቢነት ማድረግ ትተው የራሳቸውን መንገድ በመከተል የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና ፍላጎት ሊቃወሙ ይችላሉ። በሙዚቀኛው ፍራንክ ሲናትራ ከአመታት በፊት ታዋቂ የሆነው ፣ “I did it my way” [በራሴ መንገድ አደረኩት] የሚል ግጥም ያለውን ዘፈን አስታውሳለው። በእርግጠኝነት፣ በህይወት ውስጥ ለግል ፍላጎቶች እና ምርጫዎች የሚሆን ብዙ ቦታ አለ፣ ነገር ግን ደህንነትን እና የዘላለማዊ ህይወትን በተመለከተ፣ መሆን ያለበት የመዝሙራችን ዋና ሃሳብ “በእግዚአብሔር መንገድ አደረኩት” የሚለው ነው፣ ምክንያቱም በእውነት ሌላ መንገድ ስለሌለ ነው።
ለምሳሌ ጥምቀትን በተመለከተ ያለውን የአዳኙን ምሳሌ ውሰዱ። ለአባቱ ታማኝ መሆኑን በተግባር ለማሳየት እና ለእኛ ምሳሌ ለመሆን ለመጠመቅ ፈቃደኛ ሆነ።
“በስጋ መሰረት ለሰው ልጆች በአብ ፊት እራሱን እንዳዋረደ አሳይቷል፣ እናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ ለእርሱ ታዛዥ መሆኑን ለአባቱ መስክሯል። …
“እናም ለሰው ልጆች፣ እኔን ተከተሉኝ አለ። ስለዚህም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ የአብን ትዕዛዛት ለመጠበቅ ፈቃደኞች ከመሆን በስተቀር ኢየሱስን ልንከተለው እንችላለን?”
የክርስቶስን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ ከእርሱ በስተቀር “የእኔ መንገድ” የምንለው ሊኖር አይችልም። ወደ ሰማይ የተለየ መንገድ ለማግኘት መሞከር፣ ክርስቶስንና ማዳኑን ከመቀበል ይልቅ በባቢሎን ግንብ ላይ ከንቱ ስራን እንደመሥራት ነው።
በወንጌል የተለወጡት ላማናዊያን የቀበሩት ጎራዴ እና መሳሪያዎች የአመጽ መሳሪያዎች ነበሩ፣ ለዚህም ምክንያት የሆነው መሳሪያዎቹን የተጠቀሙበት መንገድ ነበር። ቤተሰባቸውን እና ነጻነታቸውን ለመጠበቅ በልጆቻቸው ጥቅም ለይ የዋሉት እነኚው መሳሪያዎች በጭራሽ በእግዚአብሔር ላይ የአመጽ መሳሪያዎች አልነበሩም። ይሄ በኔፋዊያንም እጆች ውስጥ ለነበሩት መሳሪያዎችም ተመሳሳይ ነው፥- “ይሁን እንጂ፣ ኔፋውያን የተነሳሱት በተሻለ ምክንያት ነበር፣ ምክንያቱም እነርሱ የሚዋጉት ለንግስናም ሆነ ለስልጣን ሳይሆን፣ ለሀገራቸውና ለነፃነታቸው፣ ለሚስቶቻቸውና ለልጆቻቸው እናም ላሉዋቸው ነገሮች ሁሉ፣ አዎን ለሚያመልኩበት ስርዓትና ለቤተክርስቲያናቸው ነበር።”
በዚሁ ተመሳሳይ መንገድ፣ በሕይወታችን ውስጥ ገለልተኛ ወይም በተፈጥሯቸው ጥሩ ሊሆኑ የሚችሉ ነገር ግን በተሳሳተ መንገድ ጥቅም ላይ ሲውሉ “የአመፅ መሳሪያዎች” የሚሆኑ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ፣ ንግግራችን ሊያንጽ ወይም ዝቅ ሊያደርጉ ይችላሉ። ያዕቆብ እንደተናገረው፦
“ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።
“በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።
“ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።”
ዛሬ ላይ በአደባባይ እና በግል ተንኮለኛ እና ክፉ መንፈስ ያለው ብዙ ተቃውሞ አለ። በወጣቶችም መካከል ቢሆን፣ ጸያፍ እና አሰዳቢ የሆነ ንግግር አለ። እንዲህ አይነቱ ስድብ ያለበት ንግግር “ገዳይ በሆነ መርዝ የተሞላ”፣ እግዚአብሔር ላይ “የሚያምፅ የጦር መሳሪያ” ነው።
በመሰረቱ ጥሩ ሆኖ ነገር ግን መለኮታዊ ምሪት ላይ ሊያምፅ የሚችል ሌላ ምሳሌን አስቡ—የግለሰብ ሙያ። አንደ ግለሰብ በሙያው፣ በህይወት ጥሪው ወይም በአገልግሎቱ እውነተኛ ደስታን ማግኘት ይችላል። ሑላችንም በብዙ የስራ ዘርፍ ላይ ታታሪ በሆኑ እና ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች በሰሩት እና በፈጠሩት ተጠቃሚዎች ነን።
ሆኖም ግን፣ ለሙያ መሰጠት የአንድ ግለሰብ ዋነኛ ትኩረት ሊሆን ይችላል። ከዚያም አዳኙ በህይወታችን ውስጥ የሚፈልገው ማንኛውም የጊዜያችን እና የችሎታችን ይግባኝን ጨምሮ ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሁለተኛ ይሆናሉ። ለወንዶች እና ለሴቶች፣ ለትዳር ሲሉ ህጋዊ እድሎችን መተው፣ ከትዳር አጋር ጋር አለመተባበር፣ ልጆችን አለመንከባከብ ወይም ለስራ እድገት ሲባል ሆን ብሎ ልጅን የማሳደግ በረከት እና ሀላፊነትን ችላ ማለት የሚመሰገን ስኬትን ወደ አመጽ ሊለውጠው ይችላል።
ሌላኛው ምሳሌ አካላዊ ጤንነታችንን ይመለከታል። ጳውሎስ እግዜአብሔርን በአካል እና በመንፈስ ማክበር እንዳለብን፣ እንዲሁም ይህ አካል የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ ያስታውሰናል። “ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፣ በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም።” ስለዚህ፣ በተቻለን መጠን ሰውነታችንን በመንከባከብ ጊዜ የማሳለፍ ፍላጎት አለን። ጥቂቶቻችን በቅርቡ የተመለከትናቸውን የኦሎምፒክ እና የፓራላይሚክ አትሊቶች የደረሱበትን የክንዋኔ መጨረሻ ላይ ልንደርስ እንችላለን። አንዳንዶቻችን ደግሞ የእድሜን ተጽእኖ ወይም ፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባላርድ እንደሚሉት “ማሰሪያዎቹ እየተፈቱ ያሉት ” አይነት ተሞክሮ ሊኖረን ይሆናል።
ሆኖም ግን፣ ፈጣሪያችን ለሰጠን ለዚህ ልዩ አካላችን የምንችለውን ያህል እንክብካቤ ስናደርግለት እርሱን እንደሚያስደስተው አምናለው። ሰውነትን ማበላሸት ወይም ማርከስ፣ አላግባብ መጠቀም ወይም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለመከተል የሚቻለውን አለማድረግ የአመፅ ምልክት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ከማምለክ ይልቅ የእግዚአብሔርን ስጦታ እንዲያመልክ የሚያመራው ይህ ከንቱነት፣ በአካል፣ በመልክ ወይም በአለባበስ ምክንያት ሙሉ ትኩረትን ማጣት ሌላኛው የዓመፅ ዓይነት ሊሆን ይችላል።
በስተመጨረሻም፣ እግዚአብሔር ላይ ያለንን የአመፅ መሳሪያዎቻችንን መቅበር ቀላል በሆነ አተረጋገም፣ ለመንፈስ ቅዱስ ግብዣ ፈቃደኛ መሆን፣ ተፈጥሮአዊውን ሰው መቀየር እናም “በጌታ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ መሆን” ማለት ነው። የመጀመሪያውን ትእዛዝ ማስቀደም ማለት ነው። ይህም እግዚአብሔር እንዲያሸንፍ መፍቀድ ማለት ነው ለእግዚአብሄር ያለን ፍቅር እና በሙሉ ልባችን፤ ኃይላችን፣ አዕምሮአችን እና ጉልበታች እርሱን ለማገልገል ያለን ቁርጠኝነት ነገሮችን በሙሉ የምንፈርድበት እና ውሳኔያችንን የምናደርግበት ዋና ምክንያታችን ከሆነ የአመፅ መሳሪያዎቻችንን ቀብረናል። በክርስቶስ ጽድቅ ምክንያት፣ እግዚአብሔር ኃጢያታችንን እና ያለፈውን አመፀኝነታችንን ይቅር ይለናል እንዲሁም በልባችን ውስጥ ያሉትን የእነዚህን የኃጢያት ቆሻሻ እና አመፀኝነት ይወስዳል። በጊዜው፣ ልክ ድሮ በወንጌሉ ተለውጠው እንደነበሩት ለላማናውያኖች እንዳደረገው፣ ምንም አይነት የክፋት ፍላጎቶችን ያስወግዳል። ከዚያም በኋላ፣ እኛም መንገዳችንን “በፍጹም [አንስትም]።”
የአመፅ መሳሪያዎቻችንን መቅበር ልዩ ወደሆነ ደስታ ያመራል። በወንጌሉ ወደጌታ ከተለወጡት ጋር በሙሉ የቤዛነትን ፍቅር መዝሙር ለመዘመር የተደረግን ነን።” የሰማይ አባታችን እና ልጁ፣ ቤዛችን፣ ለእኛ የመጨረሻ ደስታ ያላቸውን ፍጻሜ የሌለውን ድጋፋቸውን በታላቅ ፍቅር እና መስዋዕት አረጋግጠዋል። ፍቅራቸው በየዕለቱ ያጋጥሙናል። በእርግጥም፣ እናም ፍቅራችንን እና ታማኝነታችንን መልሰን ለመስጠት እንችላለን። በሕይወታችን ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ የሚነሳውን ማንኛውንም አመፅ—በጣም ጥልቅ በሆነ ቦታ ውስጥ—እንቀብር እና በፈቃደኛ ልብ እና በፈቃደኝነት አእምሮ እንተካው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።