አጠቃላይ ጉባኤ
ፈቃዳችንን ከእርሱ ጋር ማስማማት
የጥቅምት 2024 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


15:20

ፈቃዳችንን ከእርሱ ጋር ማስማማት

የጌታን ፈቃድ በሕይወታችን ውስጥ መከተላችን በዓለም ላይ እጅግ ውድ የሆነውን ዕንቁ ማለትም የሰማይን መንግሥት እንድናገኝ ያስችለናል።

በምሳሌው ላይ፣ አዳኝ “መልካምን ዕንቁ” ስለሚሻ አንድ ነጋዴ ሰው ተናግሯል። ነጋዴውም በፍለጋ አንድ “ታላቅ እንቁ” አገኘ። ቢሆንም ይህን አስደናቂ እንቁ የራሱ ለማድረግ ሰውየው ንብረቱን ሁሉ መሸጥ ነበረበት፣ እና ይህን በደስታ አደረገ።

በዚህ አጭርና አስተማሪ በሆነ ምሳሌ አማካኝነት፣ አዳኙ መንግስተ ሰማይን በዋጋ ሊተመን ከማይቻል ዕንቁ ጋር በማመሳሰል፣ በእውነትም ከሁሉ በላይ ሊፈለግ የሚገባ እጅግ ውድ ሀብት እንደሆነ ውብ በሆነ መንገድ አስተምሯል። ነጋዴው ያን ውድ ዕንቁ ለማግኘት ወዲያውኑ ንብረቱን በሙሉ መሸጡ፣ አእምሯችንንና ፍላጎታችንን ከጌታ ፈቃድ ጋር ማስማማት እንዳለብን፣ እንዲሁም በምድራዊ ኑሮአችን የእግዚአብሔርን መንግስት ዘለአለማዊ በረከቶች ለማግኘት የምንችለውን ሁሉ በፈቃደኝነት ማድረግ እንዳለብን በግልጽ ይጠቁማል።

ለዚህ ታላቅ ሽልማት ብቁ ለመሆን፣ እራሳችንን እንድናስቀድም የሚያደርጉ ሩጫዎችን ለመተው የተቻለንን ጥረት ማድረግ እና ለጌታችንና ቅዱስ እና ሃያል ለሆኑት መንገዶቹ ሙሉ በሙሉ ቆራጥ እንዳንሆን ወደ ኋላ የሚያስቀሩንን የትኞቹንም አይነት ትስስሮችን መተው ይኖርብናል። ሐዋሪያው ጳውሎስ እነዚህን አይነት የተቀደሱ ትጋቶች “የክርስቶስ ልብ” ብሎ ገልጿቸዋል። ኢየሱስ በምሳሌ እንዳሳየው፣ ይህም ማለት በህይወታችን ውስጥ “ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር [እናደርጋለን]” ወይም ሌሎች ሰዎች በዚህ ቀናት እንደሚሉት፣ ይህ “ለጌታ የሚሰራውን እናደርጋለን።”

በወንጌል አገላለጽ ደግሞ፣ ጌታን “ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር [የምናደርገው]” የእኛን ፈቃድ ለእርሱ ፈቃድ ስናስገዛ ነው። አዳኙ ደቀ መዛሙርቱን ትእዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ፣ የዚህን መርሕ አስፈላጊነት ጠቃሚ በሆነ መልኩ አስተምሯል፦

“ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።

“ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው።

ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”

አዳኙ ፈቃዱ በአብ ፈቃድ እንዲዋጥ በመፍቀድ ለአብ የመገዛትን ፍጹም እና መለኮታዊ ደረጃን አግኝቷል። አዳኙ “የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም” በማለት በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር። ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ስለ አዳኙ የሀጢያት ክፍያ ጭንቀትና ስቃይ ሲያስተምር እንዲህ አለ፦

“እነሆ፣ ንስሀ ከገቡ እንዳይሰቃዩ ዘንድ እኔ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለሁሉም ተሰቃይቻለሁ፤ …

“ይህም ስቃይ የሁሉም ታላቅ የሆንኩትን እኔን እግዚአብሔርን፣ ከስቃዩ የተነሳ እንድንቀጠቀጥ እናም ከእያንዳንዱ ቀዳዳ እንድደማ እናም በአካል እና በመንፈስ እንድሰቃይ እናም መራራውን ጽዋ እንዳልጠጣ እንድፈልግ እና እንድሸማቀቅ ያደረገኝን ነው።

“ሆኖም፣ ለአብ ክብር ይሁን፣ እናም ጠጥቼዋለሁ እናም ለሰዎች ልጆችም ዝግጅቴን ጨርሻለሁ።”

በምድራዊ ህይወት ቆይታችን ጊዜ፣ የሰማይ አባት በትክክል የሚያውቀውን፣ ለዘለአለም የተሻለውን እና በእቅዱ ውስጥ ለልጆች ፍፁም የሆነውን ነገር ለመረዳት ከመጣር ይልቅ እናውቃለን ብለን ከምናስበው የተሻለ ከምንለው እና ለእኛ ይሰራል ብለን ከምንገምተው ነገር ጋር ብዙ ጊዜ እንታገላለን። በተለይም ለእኛ ዘመን በቅዱሳን መጽሐፍት የተነገሩትን ትንቢቶች ግምት ወስጥ ስናስገባ፣ ይህ ታላቅ ትግል ውስብስብ ሊሆን ይችላል፦ “ነገር ግን በመጨረሻው … ቀን ይህን እወቅ … ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፣ … ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ።”

የዚህም ትንቢት መፈጸም አንዱ ምልክት ሊሆን የሚችለው በአሁን ሰዓት በዓለም ውስጥ የታወቀ ልምድ ሲሆን፣ በብዙሃንም ተቀባይነትን አግኙቷል፣ ሰዎች በራሳቸው አዕምሮ ተውጠዋል፣ አብዝተውም የሚያውጁት፣ “የትኛውም ነገር ይሁን፣ በእራሴ እውነት እኖራለሁ ወይም ለራሴ የሚመቸኝን አደርጋለሁ” የሚለውን ሃሳብ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው፣ “ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።” የእንዲህ አይነት አስተሳሰብ ብዙ ጊዜ የራስን ጥቅም ብቻ በማሳደድ፣ የግል ምርጫዎችን ላይ በማተኮር ወይም ከአምላክ የፍቅር እቅድና ለእነርሱ ካለው ፈቃድ ጋር የማይጣጣሙ አንዳንድ የባሕርይ ዓይነቶችን አስመስለው ለማቅረብ በሚፈልጉ ሰዎች “ትክክለኛ” ተደርጎ ይወሰዳል። ልባችን እና አዕምሮአችን የዚህን አይነት አስተሳሰብ እንዲቀበል ከፈቀድን፣ እግዚአብሔር ለልጆቹ በፍቅር ያዘጋጀውን እጅግ ውድ የሆነ ዕንቁ—የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ለራሳችን ጉልህ የሆኑ መሰናክሎችን መፍጠር እንጀምራለን።

ምንም እንኳን እያንዳንዳችን በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ ልባችንን እና አእምሯችንን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ያማከልን ለማድረግ እየጣርን ቢሆን እንዲሁም ግላዊ በሆነ የደቀመዝሙርነት ጉዞ እየተጓዝን እንደሆነ እውነት ቢሆንም፣ በሕይወታችን በዚህ ዓይነቱ ዓለማዊ ፍልስፍና እንዳንፈተን መጠንቀቅ እና ዘወትር ንቁ መሆን ይኖርብናል። ሽማግሌ ክውንተን ኤል ኩክ እንዳሉት “በቅንነት ክርስቶስን መምሰል እውነተኛ ከመሆንም የበለጠ ጠቃሚ ግብ ነው።”

የተወደዳችሁ ጓደኞቼ፣ በሕይወታችን ውስጥ ለራሳችን ከምንሮጥላቸው ነገሮች ይልቅ እግዚአብሔር ታልቅ ምሳሌያች እንዲሆን ስነፈቀድ፣ በደቀ መዝሙርነት እያደግን እንሄዳለን እንዲሁም ልባችንንና አዕምሮአችንን በአዳኙ ላይ የማቀናጀት አቅምን እጨምራለን። በሌላ በኩል፣ የእግዚአብሔር መንገድ በሕወታችን ወስጥ እንዲያሸንፍ የማንፈቀድ ከሆነ፣ ለራሳችን አሳልፈን እንሰጣለን፣ የእግዚአብሔርም ምሪት ስለማይኖረን የምንሰራውንም ሆነ የማንሰራውን ነገሮች ሁሉ ለማመካኘት እንጥራልን። በተጨማሪም “በራሴ መንገድ ነገሮችን እያደረግሁ ነው” በማለት ነገሮችን በራሳችን መንገድ በማድረግ ለራሳችን ሰበብ ልንደረድር እንችላለን።

በአንድ ወቅት፣ አዳኙ ትምህርቱን በሚያውጅበት ጊዜ፣ አንዳንድ ሰዎች በተለይም ራሳቸውን ጻድቅ አድርገው የሚቆጥሩት፣ መልዕክቱን ቸል በማለት እና በድፍረትም የአብርሃም ልጆች መሆናቸውን በማወጅ የእነርሱ የዘር ሃረግ በእግዚአብሄር ፊት የተለየ ተቀባይነትን እንደሚያስገኝላቸው ገልጸው ነበር። እንደዚያ አይነቱ አስተሳሰብ በራሳቸው ማስተዋል ላይ እንዲደገፉ እና አዳኙ የሚያስተምረውን ትምህርት እንዳያምኑ አድርጓቸዋል። ፈሪሳውያን ለኢየሱስ የሰጡት ምላሽ በትዕቢት የተሞላው ባህሪያቸው ለአዳኙ ቃላት እና ለእግዚአብሄር መንገድ ልባቸው ውስጥ ቦታ እንዲኖር አለማድረጉ ግልጽ የሆነ ማስረጃ ነው። በምላሹ፣ ኢየሱስ በጥበብ እና በድፍረት እውነተኛ የአብርሃም ልጆች ከሆኑ፣ የአብርሃምን ሥራዎች ይሠሩ እንደነበር በተለይ የአብርሃም አምላክ በፊታቸው ቆሞ በዚያው ቅጽበት እውነትን እያስተማራቸው እንደሆነ ሲታሰብ።

ወንድሞችና እህቶች፣ እንደምታዩት፣ “ለእኔ የሚጠቅመኝ” እና “ዘወትር ለጌታ ደስ የሚያሰኝን” በሚሉ ከንቱ የአዕምሮ ትግሎች ላይ መስራት በዘመናችን የተለየ አዲስ ዝንባሌ አይደለም። ይህ ለዘመናት የዘለቀ አስተሳሰብ ብዙውን ጊዜ በራሳቸው አስተያየት ጠቢባን የሆኑትን የሚያሳውር፣ እንዲሁም ግራ በማጋባት ብዙዎቹን የእግዚአብሄር ልጆች የሚያዳክም ነው። እንዲያውም ይህ አስተሳሰብ ከድሮ የነበረ የጠላት ማታለያ ነው፤ የእግዚአብሔርን ልጆች ከእውነተኛውና ከታማኙ የቃል ኪዳን መንገድ በጥንቃቄ የሚያርቅ አሳሳች መንገድ ነው። እንደ ስነ ባህርይ፣ አካባቢ፣ አካላዊና የአእምሮ ችግሮች ያሉ የግል ሁኔታዎች በጉዟችን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቢሆኑም፣ ዋናው ቁም ነገር ግን ጌታ ለሕይወታችን ያዘጋጀውን ንድፍ ለመከተል ወይም ላለመከተል ለመወሰን ለመምረጥ ነፃ የምንሆንበት ውስጣዊ ቦታ መኖሩ ነው። በእውነት፣ “መንገዱን አመላክቷል ጎዳናውንም መርቷል፣ እያንዳዱም መመሪያ [ይገልጸዋል]።”

የክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንደመሆናችን፣ በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት ለእኛ ባዘጋጀልን መንገድ መራመድ እንፈልጋለን። ፈቃዱን እና እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም እርሱን ለመምሰል እንፈልጋለን። ለገባነው ቃል ኪዳን ሁሉ ታማኝ ለመሆንና እንዲሁም “ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ፣” ለመኖር ስንጥር ከእነዚያ ውድ ዕንቁዎች እንድንርቅ ከሚያደርጉን ኃጢያቶች እና ስህተቶች—የፍልስፍና እና የሀሰት የአስተምህሮ ሰለባ እንዳንሆን እንተጋለን።

የክርስቶስን ደቀመዝሙርት የሆኑ የሚሰሩትን ለማድረግ እና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን ለማድረግ በመምረጣቸው እና ለእግዚአብሔር መንፈስ ራሳቸውን ማስገዛታቸው በህይወታቸው ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ በግሌ ትልቅ መነሳሳት ሆኖኛል። አንድ ወጣት ሚስዮን ለመሄድ መወሰን ያቃተው፣ ግን የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ መሪ ስለ ራሱ የግል ምስክርነት እና ሚስዮናዊ አገለግሎት ቅዱስ ልምዶችን ያካፈለበትን ሲያዳምጥ ጌታን ሄዶ ለማገልገል መነሳሳቱን አውቃለሁ።

አሁን የተመለሰ ሚስዮናዊ የሆነው ይህ ወጣት፣በራሱ ቃላት፣ “የአዳኙን የኢየሱስ ክርስቶስን ሐዋርያ ምስክርነት ሳዳምጥ፣ እግዚአብሔር እንደሚወደኝ ተሰምቶኝ ስለነበር ይህን ፍቅር ለሌሎች ለማካፈል ፈለግሁ። በዚያ ወቅት ፍርሃት፣ ጥርጣሬና ጭንቀት ቢያድርብኝም ሚስዮናዊ ሆኜ ማገልገል እንዳለብኝ ተገነዘብኩ። እግዚአብሔር ለልጆቹ በሰጣቸው በረከቶች እና ቃል ኪዳኖች ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ እንደሆንኩኝ ተሰማኝ። ዛሬ፣ እኔ አዲስ ሰው ነኝ፤ ይህ ወንጌል እውነት እንደሆነ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር እንደተመለሰች ምስክርነት አለኝ።” ይህ ወጣት የጌታን መንገድ መርጦ በሁሉም ዘርፍ የእውነተኛ ደቀ መዝሙር ምሳሌ ሆነ።

አንዲት ታማኝ ወጣት በምትሠራበት የፋሽን ድርጅት ውስጥ ከሚኖረው የሥራ ክፍፍል ጋር እንዲስማማ ስርዓት የሌለው አለባበስ እንድትለብስ በተጠየቀች ጊዜ አቋሟን ላለመቀየር ወሰነች። አካሏ የሰማይ አባታችን ቅዱስ ስጦታና መንፈሱ የሚኖርበት ስፍራ መሆኑን በመረዳት፣ ከአለም በላይ በሆነ መስፈርት ለመኖር ተነሳሳች። በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እውነት ስትኖር ያዩአት ሰዎች እንዲተማመኑባት ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለአፍታም ቢሆን አደጋ ላይ የነበረውን ስራዋን ጠብቃለች። ለአለም ደስታ ከመስራት ይልቅ በጌታ ፊት ደስ የሚያሰኘውን ለመስራት ፈቃደኛ መሆኗ በአስቸጋሪ ምርጫዎች መካከል ቃል ኪዳኗን እንድትተማመን አድርጓታል።

ወንድሞችና እህቶች፣ በዕለት ተዕለት ጉዟችን ተመሳሳይ ውሳኔዎች ሁልጊዜ ያጋጥሙናል። ራሳችንን ለእግዚአብሔር የማስገዛት አቅማችንን ሊያጎድፍብን የሚችል በህይወታችን ውስጥ የሥጋ ድክመቶች እንዳሉ አምነን ለመቀበል ቆም ብለን እና በገርነት መንፈስ ለመከታተል በመጨረሻም ከራሳችን ይልቅ የእርሱን መንገድ ለመቀበል መወሰን ድፍረትና ፈቃደኝነት ይጠይቃል። የደቀመዝሙርነታችን የመጨረሻ ፈተና የሚገኘው አሮጌውን ማንነችንን ለመተውና ለማጣት እንዲሁም ልባችንንና ሙሉ ነፍሳችንን ለእግዚአብሔር ለማስገዛት ፍቃደኞች መሆናችን ነው።

በጣም አስደናቂ ከሆኑት የምድራዊ ህይወት ጊዜያት አንዱ የሚከሰተው “የሚጠቅሙትን እና ጌታን ደስ የሚያሰኙትን” እና “እኛን የሚጠቅሙንን“ የሚሉትን እኚህን ሁለት አንድ ላይ እኛ ስናጣምራቸው የሚመጣው ደስታ ነው! የጌታን ፈቃድ የራሳችን ለማድረግ ውሳኔያዊና የማይጠራጠር ደቀመዝሙርነትን ይጠይቃል! በዚህ አስደናቂ ወቅት፣ ለጌታ የተቀደስን በመሆን ፍቃዳችንን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ አሳልፈን እንሰጣለን። እንዲህ ያለው መንፈሳዊ ተገዥነት ግሩም፣ ኃይልና ለውጥ የሚያስገኝ ነው።

የጌታን ፈቃድ በሕይወታችን ውስጥ መከተላችን በዓለም ላይ እጅግ ውድ የሆነውን ዕንቁ ማለትም የሰማይን መንግሥት እንድናገኝ እንደሚያስችለን እመሰክርላችኋለሁ። እያንዳንዳችን፣ በጊዜአችን እና በተራችን፣ በቃል ኪዳን በመተማመን፣ ለሰማይ አባታችን እና ለአዳኛችን ለኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ ደስ የሚያሰኛችሁ፣ እኔንም ደስ ያሰኘኛል”፣ ብለን እናውጅ ዘንድ ጸሎቴ ነው። እነዚህን ሁሉ የምለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።