ፈጽሞ የማይረሱ ቀናት
እነዚህ መጪዎቹ ጊዜያት የቤተክርስቲያኗ አባላት የምስራቹን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል ተጨማሪ እድሎችን ይሰጣሉ።
መግቢያ
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በዚህ ዘመን ያለው የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ በሚያስደንቅ ሁኔታ ጌታ ቤተክርስቲያኑን እንዴት እንደሚመራ በሚያሳዩ መለኮታዊ ልምዶች የተሞላ ነው። ከ1820 እስከ 1830 ያለው አስርት ዓመት፣ይህ በታሪካችን ውስጥ ያለው ዓሥር ዓመት፣ ከሌሎቹ ዓስርት አመታት የበለጠ አስደናቂ ነው። በ1820 (እ.አ.አ) የጸደይ ወቅት ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በተቀደሰ ጫካ ውስጥ እግዚአብሔር አብንና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የማየት ልምድ ካጋጠመው ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 6፣ 1830 (እ.አ.አ) የቀጠለው ያ አስርት አመት ከየትኛውም ጋር አይመሳሰልም።
እነዚህን አስደናቂ ክስተቶች አስቧቸው! ወጣቱ ነቢይ ከመልአኩ ሞሮኒ ጋር ተነጋገረ፣ የወርቁን ሰሌዳዎች ተረጎመ እንዲሁም መፅሐፈ ሞርሞንን አሳተመ! እርሱ የአሮናዊ እና የመልከ ጼዴቅ ክህነት ዳግም የተመለሰበት መሳሪያ ነበር፣ ከዚያም ቤተክርስቲያኗን አደራጀ። ኦሊቨር ካውድሪ ያንን ዘመን በሚገባ፦ “እነዚህ በምንም የማይረሱ ቀናት ነበሩ” ሲል ገልጿቸዋል። ተአምራዊ ክስተቶች ዛሬም ቀጥለዋል።
ዘንድሮ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ወደር የለሽ ምሥረታ በኋላ እንደታየው ሁሉ ጠቃሚ ሊሆን የሚችል አስርት ዓመት እንደጀመርን ለመጠቆም ደፋር ልሁን።
የእኛ አስርት አመት
ላብራራ። ከአሁኑ 2024 እስከ 2034 ባሉት ዓመታት ውስጥ፣ ለማገልገል፣ ከአባላት እና ከጓደኞቻችን ጋር አንድ ለመሆን እና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከምን ጊዜውም በላይ ለብዙ ሰዎች ለማስተዋወቅ አስደናቂ አጋጣሚዎች የሚፈጥሩ መንፈሳዊ ክስተቶችን እንለማመዳለን።
የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የ100ኛ ዓመት የልደት በዓልን በአሥር ሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር ስናከብር እውነተኛ ታሪካዊ ጊዜ ያለውን ሀይል ተመልክተናል።
Newsweek [የኒውስዊክ] መፅሔት ስለፕሬዚዳንት ኔልሰን የልደት ቀን ሪፖርት ሲያደርግ፣ “የዓለማችን አንጋፋ የሀይማኖት መሪ 100 ዓመት ሞላቸው” የሚል ርዕስ ያለውን ፅሁፍ ጽፏል። ከዚያም በዓለማችን ያሉ 10 አንጋፋ የእምነት መሪዎችን ዘርዝረዋል— በዚያም ውስጥ ፕሬዚዳንት ኔልሰን በመጀመሪያ ከዚያ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ እና ዳሊ ላማ ተካተዋል።
በNew York Times [በኒውዮርክ ታይምስ] መጣጥፍ ላይ የወጣው መግለጫ የአብዛኛውን የአለም አቀፍ ሽፋን አመለካከት ይወክላል፦ “በ[ዩናይትድ ስቴትስ] ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዑደት ውስጥ ስለ እርጅና እና አመራር ጥልቅ እና ውስጣዊ ማሰላሰልን ያነሳሳው፣ የአቶ ኔልሰን ወሳኝ ምዕራፍ ቢያንስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ባለ ሶስት አሃዝ ልደት ብዙ ብስጭት እንደሌለበት ይጠቁማል። ፕሬዚዳንታቸውን እንደ ሥራ አስፈፃሚ ብቻ ሳይሆን እንደ ‘ነቢይ፣ ባለ ራዕይ እና ገላጭ’ አድርገው በሚመለከቱት በቤተ ክርስቲያኗ አባላት ዘንድ አሁንም ተወዳጅነት አላቸው።
የፕሬዚደንት ኔልሰን ወሳኝ ምዕራፍ የሆነ ልደት ለአለም አቀፍ ታዳሚዎች የእግዚአብሔርን ነቢይ ለማስተዋወቅ እድል ስለሰጠን ምንኛ አመስጋኞች ነን ይህም ፈጽሞ የማይረሳበዓል ነው።
በዚህ ጸደይ መጀመሪያ ላይ፣ ቤተ ክርስቲያኗ እውቅና ያገኘችባቸውን ሀገራት የሚወክሉ አለም አቀፍ ባንዲራዎችን የሚያሳይ በቤተመቅደሱ አደባባይ ባለው የታደሰ ፕላዛ ላይ ተገለጠ። የፕላዛው መግቢያ እነዚህ ትንቢታዊ ቃላት ተፃፎበታል፦ “በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።”
በእርግጥም፣ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ የሚፈጸሙት ግዙፍ ክንውኖች ይህ የኢሳይያስ ትንቢት እየተፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ አንድ መገለጫ ሊሆን ይችላል።
በሚቀጥለው አስርት ዓመት ውስጥ ሊታይ የሚችለውን ታይቶ የማይታወቅ የአዲስ ቤተመቅደስ ጉብኝት እና ምርቃት፣ እንዲሁም የ164 እና ቁጥራቸውእየጨመረ ያሉ የሚገነቡ ቤተመቅደሶችን አስቡ። በአስር ሚሊዮኖች የምትቆጠሩት እናንተ እና ጓደኞቻችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትገቡ በዓይነ ሕሊናችሁ ተመልከቱ። የእነዚህ ክስተቶች ተምሳሌታዊ ማእከል የሶልት ሌክ ቤተመቅደስ እና ከእሱ ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎች እንደገና መቀደስ ይሆናል። እነዚህ ቀናት ፈጽሞ የማይረሱ ይሆናሉ።
የ2030 (እ.አ.አ) አመት የቤተክርስቲያኗን ምስረታ ሁለት መቶ አመት ለማክበር በአለም ዙሪያ እድሎችን ያመጣል። ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ ይህንን ወሳኝ ምዕራፍ እንዴት እውቅና እንደምትሠጠው ለመናገር በጣም ገና ቢሆንም፣ በእርግጥም ቤተሰቦችን፣ ጓደኞችን፣ የስራ ባልደረቦችን፣ እንዲሁም ታዋቂ እንግዶችን “መጥተው እንዲያዩ” እና በቤተክርስቲያኗ አባላት ህይወት ውስጥ ያለውን ሀይለኛ ተፅዕኖ በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ለመጋበዝ ያስችለናል።
በ2034 (እ.ኤ.አ) በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለሥልጣናት፣ ጎብኚዎች እና አትሌቶች የክረምት ኦሎምፒክ ውድድር የሚካሄድበትን የሶልት ሌክ ከተማ ጎዳና ያጥለቀልቃሉ። ምናልባት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከሚገለጠው የበለጠ የአለም አንድነት ማሳያ ላይኖር ይችላል። የዓለም አይኖች በቤተክርስቲያኗ እና በአባላት ላይ ይሆናሉ፣በጎ ፈቃደኝነት፣ማገልገል እና የምስራችን በደግ ስራዎች ለመካፈል ብዙ እድሎችን ይሰጣል—ፈጽሞ የማይረሳ ክስተት።
እነዚህ መጪዎቹ ጊዜያት የቤተክርስቲያኗ አባላት የምስራቹን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በቃልና በተግባር ለማካፈል ተጨማሪ እድሎችን ይሰጣል፣ ፈጽሞ የማይረሱ ዓስርት አመት።
የምስራች
ፕሬዚዳንት ኔልሰን ከልደታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ በነበረ ስብሰባ ላይ “የምስራች” የሚለውን ሐረግ ከፍ አድርገው የሚመለከቱበትን ምክንያት አጋርተዋል። ላይ ላዩን ሲታይ ደስታንና ሃሴትን እንደሚያስተላልፍ ገልጸዋል። ሆኖም “የምስራች” ከዚህ የበለጠ ብዙ ነገርን ያስተላልፋል። ይህ ሐረግ ከመጀመሪያው የግሪክኛ ቃል ዪኤንጂሊያን፣ የመጣ እንደሆነ ገልጿል፤ ፍችውም ትርጉሙ “ምሥራች” ወይም “ወንጌል” ማለት ነው። በዚህ እና በሚቀጥለው ህይወት ውስጥ ደስታ እና ሃሴት ሁል ጊዜ ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ጋር የተቆራኙ ናቸው። ስለዚህ “የምስራች” የሚለው ሐረግ ይህንን ድርብ ትርጉም በሚያስደንቅ ሁኔታ ይይዛል።
“ወንዶች (እና ሴቶች) ደስታም እንዲኖራቸው ዘንድ ነው።” የሰማይ አባት በበረከቶቹ አማካኝነት ደስታን የሚያስገኘውን የደስታ እቅድ አዘጋጅቷል። እነዚህም እንደ ቤተሰብ ለዘላለም በእርሱ መገኘት መኖርን ያካትታል። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ላለው እቅድ ዋና ክፍል ነው። የዘለአለምን ሕይወት ለማግኘት ወደ ክርስቶስ መምጣት አለብን። ይህን ስናደርግ “እና ሌሎችንም እንደዚሁ እንዲያደርጉ ስንረዳቸው፣ በእግዚአብሄር የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ላይ ተሳተፍን ማለት ነው።”
ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የምስራች መልእክት በምድር ላይ በጣም አስፈላጊው መልእክት ነው። እናም የቤተክርስቲያኗ ወጣቶች እና ጎልማሶች አስፈላጊ ሚና ያላቸው እዚህ ላይ ነው ።
ለወጣቶች ጥንካሬ
አሁን፣ ይህ መጪው አስርት ዓመት ለእያንዳንዱ የቤተክርስቲያኗ አባል ፈጽሞ መረሣት በማይገባቸው ቀናት ሊሞሉ ቢችሉም፣ ይህ በተለይ ለእናንተ ለመጪው ትውልድ እውነት ሊሆን ይችላል። አሁን እዚህ ምድር ላይ ያላችሁት አሁን እዚህ እንድትሆኑ ስለተመረጣችሁ ነው። ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ጥንካሬ እና ችሎታ አላችሁ።
ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኪ. ካነን እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፣ “እግዚአብሔር አለምንና የክፉውን ሀይል ሁሉ ለመጋፈጥ ድፍረት እና ቁርጠኝነት ያላቸውን መንፈሶች ለዚህ ዘመን ጠብቋል፣ [እናም]… ምንም አይነት ውጤቶችን ሳንፈራ የአምላካችንን ጽዮን እንገንባ” በማለት ተናግረዋል።
ለዚያም፣ በጭራሽ የማይረሳው የሚቀጥለው ዓስርት ዓመት ለእናንተምን ያህል አስደሳች ሊሆን እንደሚችል እንድታስቡ ለመጋበዝ ስለመጪው ትውልድ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። እንዲሁም በዚህ በሚቀጥለው አስርት ዓመት ውስጥ እናንተን የሚያበረታቱ ጥቂት ቀላል ምክሮችን እና ማበረታቻዎችን አቀርባለሁ።
እንደ ብዙዎቻችሁ፣ በአጋጣሚ እንዲሁም ጥያቄ ሳይቀርብለት፣ በአንድ የተወሰነ ቀን ላይ እያደረኳቸው የነበሩትን ነገሮች የሚያሳዩ ብዙ ፎቶዎችን አውጥቶ የሚያሣይ ስማርት ስልክ አለኝ። በጥቂት አመታት ውስጥ የእኔ እና የቤተሰቤ ነገሮች ምን ያህል እንደተቀየሩ ማየት ሁል ጊዜም ይገርማል።
የእናንተ ስልክ ከዛሬ ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረሥ የሚያሣያቸውን ፎቶዎች እስቲ አስቡት። ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወይም ከኮሌጅ ስትመረቁ የቤተመቅደሥ ቡራኬ ስትቀበሉ፣ ወደ ሚሲዮን ስትሄዱ፣ ትዳር ስትመሠርቱና የመጀመሪያ ልጃችሁን ስትወልዱ ልታዩ ትችላላችሁ። ለእናንተ በግል ይህ ፈጽሞ የማይረሣ አስርት አመት ይሆናል። ነገር ግን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የምስራች የእናንተን ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻችሁን፣ የጓደኞቻችሁን እና የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችሁን ሕይወት እንዴት እንደሚያበለጽግ እና እንደሚያጎለብት በማሣየት በዓለም ውስጥ ብርሃን ለመሆን በትጋት የምትጥሩ ከሆነ በእጥፍ ይሆናል።
ይህን እንዴት ማድረግ እንደምትችሉ እያሰባችሁ ይሆናል።
የእግዚአብሔር ነቢያት ይህ የሚደረገው በአራት ቀላል ተግባራት እንደሆነ አስተምረውናል፣ በአምላክ የተሠጡ ኃላፊነቶች ተብለው ይጠራሉ፦ በመጀመሪያ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መኖር፣ ሁለተኛ የተቸገሩትን መንከባከብ፣ ሦስተኛ ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ፣ እና አራተኛ ቤተሰቦችን ለዘለአለም ማጣመር ነው። በሚያስደንቅ ሁኔታ፣ እያንዳንዳቸው በተለመደው እና በተፈጥሯዊ መንገዶች ሊደረጉ ይችላሉ።
በአምላክ የተሠጡ ኃላፊነቶች
እነዚህን አራት በአምላክ የተሠጡ ኃላፊነቶች ከተቀበላችሁ ይህ ለእናንተ ፈጽሞ የማይረሣ አሥርት ዓመት እንደሚሆን ቃል እገባላችኋለሁ። ይህ ምን ሊያስከትል እንደሚችል እናስብ።
በመጀመሪያ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ኑሩ። የነቢያትን ቃል አጥኑ እና የሰማይ አባታችሁን መውደድን ተማሩ። ልባችሁን ወደ እርሱ ማዘንበል እና ቀጭን በሆኑት ጎዳናዎች ለመራመድ ጣሩ። ሽማግሌ ዩሊስስ ሶሬስ እንደገለጹት “በቃል ኪዳን መታመን” ከፍ በሉ። ይህ በራስ መተማመን የሚመጣው አዳኝ እንደሚያበረታችሁ እና እንደሚረዳችሁ በማወቅ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ቃል ኪዳኖችን በመግባት ነው።
ጓደኞቻችሁ በወንጌል በመኖራችሁ የሚሰማችሁን ደስታ እንዲመለከቱ አድርጉ ከዚያም እነርሡ የሚቀበሉት ምርጥ የወንጌል መልእክት ትሆናላችሁ።
ሁለተኛ፣ የተቸገሩትን ለመንከባከብ በርኅራኄ ደግፉ። የእናንተ ትውልድ ባልተለመደ ሁኔታ ትኩረቱን ዕድል በጠመመችባቸው ላይ እያደረገ ነው። በማንኛውም ጊዜ አደጋ በተከሰተ ጊዜ እና የቤተክርስቲያኗ አባላት ፍርስራሹን ለማስወገድ እና የተጎዱትን ለማፅናናት በሚጣደፉበት ጊዜ፣ “የእርዳታ እጆች” ቲሸርት የለበሱት አብዛኞቹ በአስራዎቹ እና በሃያዎቹየዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ይመስላሉ። “አንዳችሁ የአንዳችሁን ሸክም ቀላል እንዲሆኑ ዘንድ ለመሸከም” እና “መፅናናትን ለሚፈልጉም ካፅናናችኋቸው” ይህ ተፈጥሮአችሁ ነው። ይህን በማድረግ “የክርስቶስን ሕግ [እንፈፅም]።”
ኢቫን የተባለ ወጣት የመጀመሪያ ደረጃ ልጅ፣ ለአካባቢው የምግብ ባንክ ለመለገስ የኦቾሎኒ ቅቤ እና ጄሊ ሳንድዊች በመሰብሰብ የበጋ እረፍቱን ለማሳለፍ ወሰነ። ፕሮጀክቱን JustServe [በጄስትስርቨ] ድህረ ገጽ ላይ አገኝ። ወጣቱ ኢቫን ከ700 ጣሳ ጄሊ በላይ ለመሰብሰብ እንዲረዳው ሙሉውን የትምህርት ቤቱን ክፍል አስመዘገበ! የምታገለግሏቸው ሰዎች ለእነርሱ ያላችሁ ትኩረት ለእግዚአብሔር ባላችሁ ፍቅር እና ባልንጀራችሁን እንደ ራሳችሁ ለመመልከት ባላችሁ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንዲያውቁ አድርጉ።
ሦስተኛ፣ ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ ጋብዟቸው። በዚህ አመትየሙሉ ጊዜ ሚስዮኖችን ለማገልገል የሚፈልጉትን ሁሉ ለማስተናገድ 36 አዳዲስ ሚሲዮኖችን በአለም ዙሪያ ከፍተናል። በርካታ ወጣቶች መደበኛ ከሆኑ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ በሚወጡበት ዘመን ይህ አስደናቂ ከመሆኑም በላይ ያላችሁን ምሥክርነትድንቅ ባሕርያት ያንጸባርቃል ። የሙሉ ጊዜ አገልግሎት እየሠጣችሁ ሆነም አልሆነ፣ እባካችሁን እኩዮቻችሁን ስትወዱ፣ ስታካፍሉ እና የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲመረምሩ ስትጋብዙ ተጽእኖ ለማድረግ ታላቅ ብቃት እንዳላችሁ እወቁ።
አራተኛ፣ ቤተሰቦችን ለዘለአለም ማጣመር። በአለም ዙሪያ ያሉ ቤተመቅደሶችን ስጎበኝ፣ ማጥመቂያው ጋር ባለውየመጠበቂያ ክፍል ብቻ ቦታ በሚጠብቁት የወጣቶች ብዛት እና የስርዓት ሰራተኞች በመሆን በሚያገለግሉት የወጣት ጎልማሶች ቁጥር ተደንቄያለሁ። በቅርቡ ከስኮትላንድና ከአየርላንድ የመጡ ከ600 የሚበልጡ ቡድኖች ወደ ፕሬስተን ኢንግላንድ ቤተመቅደስ በመጓዝ ከ4 ሺህ በላይ ሥርዓቶችን አከናወኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ለሞቱ የግል ቅድመ አያቶቻቸው ነበር! በቤተሰብ ታሪክ ውስጥ እንድትሣተፉ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ ጊዜ እንድታሳልፉ፣ እና በቤተመቅደስ ውስጥ በእኩል ደረጃ ብቁ የሆነ ጓደኛ ለማግባት የተዘጋጀችሁ አይነት ወንድ ወይም ሴት ለመሆን እራሳችሁን እንድትዘጋጁ እመክራችኋለሁ። ቤተመቅደስን የዘወትር የህይወታችሁ ክፍል ለማድረግ አሁኑኑ በህይወታችሁ ውስጥ አንድ ዓይነት ንድፍ አውጡ።
ማጠቃለያ
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ውድ ወጣት ጓደኞቼ፣ ወደፊት በእያንዳንዳችን ላይ ችግሮች ሊኖሩብን ይችላሉ። ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት ታይቶ በማያታወቀው በዚህ በመጪው አሥርት ዓመት ውስጥ ስንገባ አኗኗርን፣ አሳቢነትን፣ መጋበዝና አንድ ላይ መሰብሰብን ጨምሮ ቀላል እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ምሥራቹን እንናገር። ይህን ስናደርግ፣ ፈጽሞ መረሳይ በማይገባቸው ልምዶችን ጌታ ይባርከናል።
በቅን ልባችሁ እና ከእውነተኛ ፍላጎት፣ የአዳኝን ስም በከንፈራቸው እና በነፍሳቸው ውስጥ ላለው መንፈስ ቅዱስ ወደ ጌታ የሚቀርቡ፣ ይህን ታላቅ እና ክብራማ መንፈሳዊ ጉዞ ለሚቀጥሉት፣ የከበሩ የሰለስቲያል በረከቶችን እንደምትገነዘቡ እና እንደምትለማመዱ እና እግዚአብሔር እንደሚሰማችሁ፣ እንደሚያውቃችሁ እና እንደሚወዳችሁ ምስክርነት እንደምትቀበሉ እመሰክራለሁ። ፈጽሞ የማይረሱ ቀናትን ታገኛላችሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።