ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፫


ክፍል ፻፳፫

በልብርቲ እስር ቤት ውስጥ እንደታሰረ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ቅዱሳን ከሚያሳድዷቸው ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት እንዲታወቅ የጻፈው። ይህ ክፍል በመጋቢት ፳፣ ፲፰፻፴፱ (እ.አ.አ.) ለቤተክርስቲያኗ ከተጻፈ ደብዳቤ ውስጥ የተወሰደ ነው (ክፍል ፻፳፩ ርዕስን ተመልከቱ)።

፩–፮፣ ቅዱሳን የተሰቃዩበትንና የተሰደዱበትን ታሪካቸውን ሰብስበው ያትሙ፤ ፯–፲፣ የሀሰት እምነትን የመሰረተው መንፈስ ቅዱሳንን እንዲሰደዱም ያደርጋል፤ ፲፩–፲፯፣ ከሁሉም እምነቶች መካከል ብዙዎች እውነትን ይቀበላሉ።

ደግሞም፣ ሁሉም ቅዱሳን በዚህ ስቴት ህዝብ የተሰቃዩባቸውን እና የተጎሳቆሉባቸውን ተጨባጭ ነገሮች እውቀት ሁሉ የመሰብሰባቸውን ትክክለኛነት እንድታስቡበት ሀሳብ እናቀርባለን፤

ደግሞም ንብረቶችን ሁሉ እና የደረሰባቸውን የጉዳት መጠን፣ የስም እና የግለሰብ ጉዳቶች እና የእውነተኛ ንብረቶች ጉዳት፤

ደግሞም፣ እስካገኟቸው እና ለይተውም እስከሚወጧቸው ድረስ፣ በዚህ ጭቆናቸው ወቅት ተሳታፊነት የነበሩ ግለሰቦችን ሁሉ ስም እናቀርባለን።

እና ምናልባት እነዚህን ነገሮች እንዲያገኙ፣ ደግሞም የምስክር ቃል እና የመሀላ ቃል እንዲወሰዱ፤ እና ደግሞም ስምን ለማጥፋት የተሰራጩትን ህትመቶችን ለመሰብሰብ ኮሚቴን መመደብ ይቻላል፤

እና በመጽሄቶች ውስጥ፣ እና በኢንሳይክሎፒዲያዎችም ውስጥ ሁሉ፣ እና የታተሙትን እና የሚጻፉትን ስም የሚያጠፉ ታሪኮችን ሁሉ፣ እና የጻፉትንም ሰዎች ስም ለመሰብሰብ፣ እና በእነዚህ ህዝብ ላይ የደረሱትን በዲያብሎስ በመነሳሳት የተደረጉትን ክፋቶች እና ተንኮል በግድ ህይወት የሚያጠፉትንም በሙሉ በማቅረብ—

ለአለም ሁሉ እንድናትመው ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ከተሰወረበት ስፍራ የሚጠራውን ቃል ኪዳን በሙሉ እና ፈጽመንም ለመውሰድ ከመቻላችን በፊት፣ እንደመጨረሻ ጥረት በሰማይ አባታችን እንደታዘዝነው፣ ለመንግስት መሪዎች ከጨለመ እና ከረከሰ አመለካከታቸው ጋር እንድናቀርባቸው፤ ደግሞም ሀያሉን ክንዱን ከመላኩ በፊት ህዝብ ሁሉ ምንም ምክንያት እንዳይኖራቸው እነዚህን ነገሮች ለመሰብሰብ ኮሚቴን ለመመደብ ይቻላል።

ለእግዚአብሔር፣ በፊቱ አብረውንም ለሚቆሙ መላእክት፣ እና ደግሞም ለራሳችን፣ እና ሀሰትን የወረሱትን የአባቶችን እምነት በልጆቻቸው ልብ ላይ አጥብቆ ባሰረው እና አለምን ግራ በመጋባት በሞላው፣ እና እየበረታም ባለው፣ እና የርኩሰት ሁሉ ዋና ምንጭ በሆነው፣ እና ምድርም ሁሉ በኃጢአቱ ሽከም በሚቃሰቱበት መንፈስ በተደገፉት በህይወትን በሚያጠፉ፣ በጨካኝ፣ እና በሚያሰቃዩ የኩነኔ ሀይላት ምክንያት በጥልቅ ሀዘን፣ በሀዘን፣ እና በሀሳብ ለተሰቃዩት ለሚስቶቻችን እና ልጆቻችን ባለእዳ መሆናችን አስፈላጊ ሀላፊነታችን ነው።

ይህም የብረት ቀንበር ነው፣ ይህም ጠንካራ ማስሪያ ነው፤ እነዚህም የሲኦል የእጅ ካቴናዎች፣ ሰንሰለቶችና የእግር ብረቶች፣ እና የእግር ብረት ሰንሰለቶች ናቸው።

ስለዚህ ይህም ለሚስቶቻችን እና ለልጆቻችን ብቻ ሳይሆን ለባልቴቶች እና አባት ለሌላቸው፣ ባሎቻቸው እና አባቶቻቸው ከብረት እጆች በታች ለተገደሉባቸው ያለብን አስፈላጊ የሀላፊነት እዳ ነው፤

እነዚህ ጥቁር እና የሚያጨልሙ ስራዎች ሲኦልም እንድትንቀጥቀጥ፣ እና በድንጋጤም እንድትዋጥ ደብዝዛም እንድትቆም፣ የዲያብሎስ እጆችም እንዲንቀጠቀጡ ለማድረግ ብቁ ናቸው።

፲፩ ደግሞም፣ ይህ ለሚመጡት ትውልዶች ሁሉ፣ እና ልባቸው ንጹህ ለሆኑት ሁሉ ያለብን አስፈላጊ የሀላፊነት እዳ ነው—

፲፪ በሁሉም ሀይማኖቶች፣ ቡድኖች፣ እና በሀይማኖት ክፍሎች ሁሉ መካከል ሰዎችን ለማታለል በሚደበቁበት የብልጠት ማጭበርበሪያዎች ምክንያት አይኖቻቸው የታወሩ፣ እና የት እንደሚያገኙትም ባለማወቃቸው ምክንያት እውነትን እንዳያገኙ የተደረጉ ብዙዎችም አሉ—

፲፫ ስለዚህ፣ ባወቅነው መጠን በጨለማ የተሰወሩትን ነገሮች ደግሞ ወደ ብርሀን ለማውጣት ህይወታችንን እናባክን እና ዋጋም እናሳጣ፤ እና እነዚህም በእውነት ከሰማይ የተገለጡ ናቸው—

፲፬ እነዚህም በትጋት ይከናወኑ።

፲፭ ማንም ሰው እነዚህን እንደትንሽ ነገሮች አይቁጠራቸው፤ ቅዱሳኑን በሚመለከት፣ በእነዚህ ላይ የሚመኩ፣ በወደፊት የሚኖሩ ብዙዎች አሉና።

፲፮ ወንድሞች፣ በጣም ግዙፍ መርከብ በማእበል ወቅት በደህንነት በነፋሱ እና በማእበሉ መካከል ይሄድ ዘንድ በጣም ጥቂት በሆነ የመርከብ መሪ ጥቅም እንደሚያገኝ ታውቃላችሁ።

፲፯ ስለዚህ፣ ውድ ወንድሞች፣ በሀይላችን ያሉትን ነገሮች ሁሉ በደስታ እናድርግ፤ ከዚያም በእርግጠኝነት የእግዚአብሔር የሚያደርገውን ማዳን ለማየት እንቁም እና የክንዱንም መገለጥ እንጠባበቅ።