ክፍል ፴፯
ታህሳሥ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት፣ ኒው ዮርክ፣ አቅራቢያ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለስድኒ ሪግደን የተሰጠ ራዕይ። በዚህ ዘመን መሰባሰብን በተመለከተ የመጀመሪያው ትእዛዝ የተሰጠው በዚህ ውስጥ ነው።
፩–፬፣ ቅዱሳን በኦሀዮ እንዲሰባሰቡ ተጠሩ።
፩ እነሆ፣ ኦሀዮ እስክትሄዱ ድረስ መተርጎም መቀጠልህ ለእኔ አስፈላጊ አይደለም፣ እና ይህም የሚሆነው በጠላት ምክንያት እና ለአንተ ደህንነት ነው።
፪ እናም ዳግም እንዲህ እልሀለሁ፣ በእነዚያ ስፍራዎች ወንጌሌን እስክትሰብክ እናም ቤተክርስቲያኔ በሚገኝበት ስፍራ ሁሉ፣ በተለይም በኮስቪል የሚገኘውን እስከምታጠነክር ድረስ አትሄድም፤ እነሆም፣ በታላቅ እምነትም ወደ እኔ ይጸልያሉና።
፫ እናም ዳግም፣ አገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ ለሚመለስበት ጊዜ ለመዘጋጀት፣ በኦሀዮ አንድ ላይ መሰብሰባቸው አስፈላጊ እንደሆነ ትእዛዝን ለቤተክርስቲያኗ እሰጣለሁ።
፬ እነሆ፣ ጥበብ በእዚህ ይላል፣ እናም እኔ እስክመጣ ድረስ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ይምረጥ። እንዲህም ይሁን። አሜን።