ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፹፯


ከፍል ፹፯

በታህሳስ ፳፭፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል በከርትላንድ ኦሀዮ ወይም በአካባቢው የተሰጠ የጦርነት ራዕይ እና ትንቢት። በዚህ ጊዜ በዮናይትድ ስቴትስ ውስጥ ስለ ባርነት እና ሳውዝ ኬሮላይና የመንግስት ቀረጥ ስለመሰረዟ ክርክር በብዛት ይገኝ ነበር። የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ እንደሚገልጸው፣ “በሀገሮች መካከል ያለው ችግር ቤተክርስቲያኗ ከዱር የመውጣት ጉዞዋን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ከነበረው በላይ” ለነቢዩ “በግልፅ ይታይ” ነበር።

፩–፬፣ በሰሜን እና በደቡብ ስቴቶች መካከል ጦርነት ተተነበየ፤ ፭–፰፣ ታላቅ መቅሰፍት በምድር ኗሪዎች ላይ ይደርሳል።

እውነትም፣ ጌታ፣ በደቡብ ኬሮላይና ማመፅ በሚጀምረው፣ የብዙ ነፍሳት ሞት እና ስቃይ ውጤት ስለሆነው፣ በአጭር ጊዜ ስለሚመጣው ጦርነት እንዲህ ይላል፤

እናም፣ ከዚህ ስፍራ አንስቶ፣ በሁሉም ህዝብ ላይ ጦርነት የሚፈስበት ጊዜ ይመጣል።

እነሆ፣ የደቡብ ስቴቶቹ ከሰሜን ስቴቶቹ ጋር ይከፋፈላሉ፣ እናም የደቡብ ስቴቶች ሌሎች ሀገሮችን፣ እንዲሁም እንግሊዝ ተብለው የሚጠሩትንም ይጠራሉ፣ እናም እነርሱም፣ ከሌሎች አገሮች ራሳቸውን ለመጠበቅ፣ ሌሎች አገሮችን ይጠራሉ፤ እና ከዚያም ጦርነት በሁሉም ሕዝቦች ላይ ይፈሳል።

እናም እንዲህ ይሆናል፣ ከብዙ ቀናት በኋላ፣ ለጦርነት የተዘጋጁት እና የሰለጠኑት ባሪያዎች በጌታቸው ላይ ይነሳሉ።

እናም እንዲህ ይሆናል በምድሩ የሚቀሩትም ራሳቸውን ያዘጋጃሉ፣ እናም በጣም ይቆጣሉ፣ እናም አህዛብን በታላቅ ስቃይ ያሰቃዩአቸዋል።

በመሆኑም፣ በጎራዴ እና ደም በማፍሰስ የምድር ኗሪዎች ያዝናሉ፤ እናም፣ የክፉ ጥፋት ሕዝብን ሁሉ በፍጹም እንዲጠፉ እስከሚያደርጋቸው ድረስ፣ በረሀብ፣ እና ወረርሽኝ፣ እና በምድር መንቀጥቀጥ፣ እና በሰማይ ነጎድጓድ፣ እና በአስፈሪ እና በግልፅ መብረቅም የምድር ኗሪዎች ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርን እጅ ንዴት፣ እና ቁጣ፣ እና ግሰጻ እንዲሰማቸው ይደረጋሉ።

በጠላቶቻቸው ላይ እንዲበቀሉ የቅዱሳን እና የቅዱሳን ደም ወደሚጮኹበት ወደ ፀባኦት ጌታ ጆሮዎች መምጣትን ያቆማሉ።

ስለዚህ፣ የጌታ ቀን እስከሚመጣ ድረስ፣ በተቀደሱ ስፍራዎች ቁሙ፣ እናም አትነቃነቁ፤ እነሆ፣ በቶሎ ይመጣልና፣ ይላል ጌታ። አሜን።