ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺፮


ክፍል ፺፮

በሰኔ ፬፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የፅዮን ከተማ ወይም ካስማ ስርዓትን በማሳየት፣ በከርትላንድ ላሉት ቅዱሳን እንደምሳሌ የተሰጠ ራዕይ። ምክንያቱ የሊቀ ካህናት ጉባኤ ነበር፣ እና የሚታሰብበት ዋናው ርዕስ ቢኖር በከርትላንድ አጠገብ ቤተክርስቲያኗ ያላትን የፍሬንች እርሻ ስፍራ የሚባለውን ምድር ስለመሸጥ ነበር። ጉባኤው ማን የእርሻ ስፍራውን በሀላፊነት እንደሚወስድ መስማማት ስላልቻሉ፣ ሁሉም ጉዳዩን በመመልከት ጌታን ለመጠየቅ ተስማሙ።

፣ የከርትላንድ የፅዮን ካስማ ብርቱ ትሁን፤ ፪–፭፣ ኤጲስ ቆጶስ ውርሱን ለቅዱሳኑ ያካፍል፤ ፮–፱፣ ጆን ጆንሰን በትብብር ስርዓት አባል ይሁን።

እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ይህንን ጉዳይ እንዴት ለመስራት የምታውቁበት ይህም ጥበብ ይህ ነው፣ ለፅዮን ብርታት የመሰረትኳት ይህች ካስማ ጠንካራ ትሆን ዘንድ ለእኔ አስፈላጊ ነውና።

ስለዚህ፣ አገልጋዬ ኒወል ኬ ውትኒ ቅዱስ ቤቴን ለመገንባት ያለምኩበትን፣ የጠቀሳችሁትን ስፍራ በሀላፊነት ይውሰድ።

ደግሞም፣ በጥበብ መሰረትም፣ ውርስ ለሚፈልጉት ጥቅም ይሆን ዘንድ፣ በመካከላችሁ በምክር እንደሚወሰነው፣ በክፍልፋይ መሬቶች ይከፋፈል።

ስለዚህ፣ ይህን ጉዳይ እና፣ ቃሌን ለሰዎች ልጆች ለማምጣት አላማ፣ ስርዓቴን ለመጥቀም አስፈላጊ የሆነውን ክፍል ታሟሉ ዘንድ አስታውሱ።

እነሆም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የሰዎች ልጆች ልብ ለእናንተ ጥቅም በቁጥጥር ስር ለማዋል አላማ፣ ቃሌ ወደ ሰዎች ልጆች ይሄዱ ዘንድ ይህ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነው። እንዲህም ይሁን። አሜን።

ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ይህም ጥበብ እና በእኔ አስፈላጊ ነው፣ መስዋዕቱን የተቀበልኩለት፣ እና ጸሎቱን የሰማሁለት፣ ከዚህ ጀምሮ ትእዛዛቴን እስካከበረ ድረስ የዘለአለም ህይወት ቃል ኪዳን የምሰጠው አገልጋዬ ጆን ጆንሰን—

እርሱም የዮሴፍ ትውልድ ዘር እና ለአባቶቹ የተሰጡትን የቃል ኪዳን በረከቶች ተካፋይ ነውና—

እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን ለሰዎች ልጆች ለማምጣት ይረዳ ዘንድ እርሱ የስርዓቱ አባል መሆኑ በእኔ ዘንድ አስፈላጊ ነው።

ስለዚህ ለዚህ በረከት ሹሙት፣ እና በዚያም ይኖርበት ዘንድ በእናንተ መካከል ከተጠቀሰው ቤት ላይ ያሉትን እዳዎች ለመውሰድ በቅንነት ይፈልግ። እንዲህም ይሁን። አሜን።