የጥናት እርዳታዎች
16. ሴሎ


16. ሴሎ

ፎቶ ፲፮

በእዚህ የምዕራብ ትእይንት፣ ከመሀከል ወደ ግራ በኩል ያለችው የጥንት ሴሎ ከተማ ፍራሽ ይታያል።

ታላቅ ድርጊቶች፥ የእስራኤል ጎሳዎች ተሰበሰቡ እናም የተመደቡላቸውን ክልል ተቀበሉ (ኢያ. ፲፰–፳፪)። ድንኳኑ እና ታቦቱ በእዚህ ተቀምጠው ነበር እና ለብዙ መቶ አመቶችም በእዚህ ቆዩ (ኢያ. ፲፰፥፩)። በእዚህም ሐና ጸለየች እናም ልጇን ሳሙኤልን ለጌታ አገልግሎት ቀደሰች (፩ ሳሙ. ፩)። እስራኤላውያን ታቦትን ከሴሎ ወሰዱ እናም ታቦቱን በያዙት በፍልስጤማውያን ተሸነፉ (፩ ሳሙ. ፬፥፩–፲፩)።