የጥናት እርዳታዎች
25. የዮርዳኖስ ወንዝ


25. የዮርዳኖስ ወንዝ

ፎቶ ፳፭

የዮርዳኖስ ወንዝ በሰሜን በገሊላ ባህር ጀምሮ ወደ እዚህ ይፈሳሉ፣ እና ከእዚያም ወደ ሙት ባህር ይቀጥላል። ይህ ፎቶ የተነሳው ወንዙ ወደ ገሊላ ባህር በሚገባበት አጠገብ ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ሎጥ የዮርዳኖስን ሜዳ ለእራሱ መረጠ (ዘፍጥ. ፲፫፥፲–፲፩)። ኢያሱ እስራኤላውያን ወደ ቃል ኪዳን ምድር እንዲሻገሩ ውሀውን ከፈለ (ኢያ. ፫፥፲፫–፲፯፬፥፩–፱፣ ፳–፳፬)። ኤልያስ እና ኤልሳዕ ውሀውን ከፈሉ (፪ ነገሥ. ፪፥፭–፰፣ ፲፪–፲፬)። ናዕማን ከለምጽ ደዌ ተፈውሶ ነበር (፪ ነገሥ. ፭፥፩–፲፭)። መጥምቁ ዮሐንስ ከአዳኝ በተጨማሪ ብዙ ሰዎች አጠመቀ (ማቴ. ፫፥፩–፮፣ ፲፫–፲፮)። (ቅ.መ.መ. የዮርዳኖስ ወንዝ ተመልከቱ።)