የጥናት እርዳታዎች
17. ሴኬም


17. ሴኬም

ፎቶ ፲፯

የሴኬም የጥንት ቦታ። በፊት የሚታየው ገሪዛን ተራራ ነው፣ እናም ከዚያም በኋላ ጌባል ተራራ አለ። ሴኬም በእነዚህ ሁለት ተራራዎች መካከል ትገኛለች።

ታላቅ ድርጊቶች፥ አብርሐም በሴኬም ሰፈረ (ዘፍጥ. ፲፪፥፮–፯)። ያዕቆብ በእዚህ ሰፈረ እናም ቁራሽ መሬት ገዛ (ዘፍጥ. ፴፫፥፲፰–፳)። ገሪዛን ተራራ የበረከት ተራራ ሲሆን፣ ጌባል ተራራ የዕርግማን ተራራ ነው (ዘዳግ. ፳፯–፳፰)። በጌባል ተራራ ላይ፣ ኢያሱ የሙሴ ህግጋትን የያዘ ሀውልት ገነባ እና ከእዚያም በኋላ ህጉን ለእስራኤላውያን አነበበ (ኢያ. ፰፥፴–፴፭)። የዮሴፍ አጥንቶች በሴኬም ተቀበሩ (ኢያ. ፳፬፥፴፪)።