6. የይሁዳ ተራራማው አገር
የይሁዳ ተራራማው አገር ፳፭ ኪሎ ሜትር ረጅም እና ፳፯ ኪሎ ሜትር የሚሰፋ ነው። አብዛኛው መሬት በድንጋይ የተሞላ እና ለማረስ አስቸጋሪ ነበር። ተራራዎቹ ፍሬያማ በሆኑ ምድሮች ባሉት ሸለቆዎች ይከፋፈላሉ። የመጀመሪያው እስራኤላውያን ከሚወሯቸው ለመጠበቅ በመጠቀም በእነዚህ ተራራዎች ውስጥ ይኖሩ ነበር።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ጌታ ይህን ምድር ለአብርሐም እና ለዘሩ ቃል ገባ (ዘፍጥ. ፲፫፥፲፬–፲፰፤ ፲፯፥፰)። ሣራ እና አብርሐም በእርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ቦታ፣ በኬብሮን ተቀበሩ (ዘፍጥ. ፳፫፥፲፱፤ ፳፭፥፱)። ዳዊት ኢየሩሳሌምን ከኢያቡሳውያን መልሶ ያዘ (፪ ሳሙ. ፭፥፬–፱)። ብዙ የብሉይ ኪዳን ድርጊቶች በእነዚህ ተራራዎች ላይ ከሌሎች ቦታዎች ሁሉ በላይ እንደተደረጉ ተመዝግበዋል።