19. ቂሣርያ እና ከሼረን እስከ ቀርሜሎስ ያለው ሜዳ
ወደ ጥንት የባህር ወደብ ከተማ ወደሆነችው ቂሣርያ እና ከሼረን እስከ ቀርሜሎስ ያለው ሜዳ ወደ ሰሜን ይመለከታል። ደግሞም በፎቶው ወደ ላይ ሲመለከቱ ቀርሜሎስ ተራራዎች ይታያሉ።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ኤልያስ የበኣል የሀሰት ነቢያትን በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ተቃወመ (፩ ነገሥ. ፲፰)። በጥንት ጊዜዎች አስፈላጊ መንገድ የነበረው ቪያ ማሪስ (የባህር መንገድ)፣ በቂሣርያ በስተምስራቅ በኩል ይገኛል። በኢዮጴ ከነበረው አስደናቂ ራዕይ በኋላ፣ ጴጥሮስ ቆርኔሌዎስ የሚባል የመቶ አለቃ በማስተማር በአህዛብ መካከል በቂሣርያም መስበክ ጀመረ (የሐዋ. ፲)። ፊልጶስ በእዚህ ሰበከ፣ ኖረ፣ እናም የተነበዩ አራት ሴት ልጆች ነበሩት (የሐዋ. ፰፥፵፤ ፳፩፥፰–፱)። ጳውሎስ በከተማዋ ለሁለት አመት ውስጥ ታስሮ ነበር (የሐዋ. ፳፫–፳፮)። ለፊልክስ፣ ለፊስጦስ፣ እና “በጥቂት ክርስቲያን ልታደርገኝ” ነበር ላለው ለሄሮድስ አግሪጳ ሁለተኛ ሰበከ (የሐዋ. ፳፮፥፳፰)።