የጥናት እርዳታዎች
23. የገሊላ ባህር እና የታላቅ ደስታ ተራራ


23. የገሊላ ባህር እና የታላቅ ደስታ ተራራ

ፎቶ ፳፫

ጨው የሌለው ሀይቅ ወደሆነው ገሊላ ባህር በሰሜን በስተምስራቅ በኩል የደቡብ ምስራቅ ትእይንት። በመካከል የሚታየው ኮረብታ በባህል የታላቅ ደስታ ተራራ ነው ተብሎ የሚታመንበት ነው። ቅፍርናሆም፣ ከፎቶው ውጪ በግራ በኩል ነው። ጥብርያዶስ ከምዕራብ ባህር ዳር ርቆ በደቡብ በኩል ይገኛል።

ታላቅ ድርጊቶች፥ አዳኝ አብዛኛውን የስጋዊ አገልግሎቱን ያሳለፈው በእዚህ ክልል ነው። በእዚህም አስራ ሁለቱን ሐዋሪያት ጠራ እናም ሾመ (ማቴ. ፬፥፲፰–፳፪፲፥፩–፬ማር. ፩፥፲፮–፳፪፥፲፫–፲፬፫፥፯፣ ፲፫–፲፱ሉቃ. ፭፥፩–፲፩)፣ የተራራ ስብከትን አስተማረ (ማቴ. ፭–፯)፣ እናም በምሳሌ አስተማረ (ማቴ. ፲፫፥፩–፶፪ማር. ፬፥፩–፴፬)። የሚቀጥሉትን ተዓምራት ፈጸመ፥ ለምጻሞችን ፈወሰ (ማቴ. ፰፥፩–፬)፣ ማዕበልን ጸጥ አደረገ (ማቴ. ፰፥፳፫–፳፯)፣ ከወጣት ሰው ወደ እሪያዎች ገብተው በባህር የሰመጡት አጋንንትን አስወጣ (ማር. ፭፥፩–፲፭)፤ ፭ ሺህ እና ፬ ሺህ መገበ (ማቴ. ፲፬፥፲፬–፳፩፲፭፥፴፪–፴፰)፤ ደቀመዛሙርቱ መረባቸን እንዲጥሉ አዘዛቸው፣ በእዚህም ብዙ አሳዎች አጠመዱ (ሉቃ. ፭፥፩–፮)፤ ብዙ ሰዎች ፈወሰ (ማቴ. ፲፭፥፳፱–፴፩ማር. ፫፥፯–፲፪)፤ እናም ከትንሳኤው በኋላ ደቀመዛሙርቱን ለማስተማር ታየ (ማር. ፲፬፥፳፯–፳፰፲፮፥፯ዮሐ. ፳፩፥፩–፳፫)። (ቅ.መ.መ. ገሊላ ተመልከቱ።)