የጥናት እርዳታዎች
4. ቃዴስ በርኔ


4. ቃዴስ በርኔ

ፎቶ ፬

ይህ ቃዴስ በርኔ የሚገኝበት (ደግሞም ዋዲ ተብሎ የሚጠራው) የታላቁ የበረሀ ሸለቆ የሰሜን ምስራቅ እይታ ነው። በዝናብ ዘመን በዚህ የሚፈሰው ትንሽ ወንዝ ይህን በደንብ ውሀ የጠጣ እና የምድረበዳው ፍሬያማ ቦታ አድርጎታል።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ይህ ሙሴ ፲፪ ሰዎች የከነዓን ምድርን እንዲሰልሉ የላከበት ቦታ ሳይሆን አይቀርም (ዘኁል. ፲፫፥፲፯–፴)። እስራኤላውያን በምድረበዳ በተንከራተቱበት ፵ አመት ውስጥ ለ፴ አመት ይህ ቦታ እንደ ዋና ስፍራቸው ያገለግል ነበር (ዘዳግ. ፪፥፲፬)። ማርያም በዚህ ቦታ ውስጥ ሞታ ተቀበረች (ዘኁል. ፳፥፩)። የቆሬ አመጽ፣ የህዝቡ ማጉረምረም፣ እና የአሮን በትር እንቡጥ ማፍራት የነበሩት በዚህ ቦታ ነበር (ዘኁል. ፲፮–፲፯)። ከዚህም በሚቀርብ ቦታ ሙሴ ድንጋይን መታና ውሀ መጣ (ዘኁል. ፳፥፯–፲፩)።