የጥናት እርዳታዎች
15. ኢያሪኮ


15. ኢያሪኮ

ፎቶ ፲፭

ይህ ፎቶ አሁን በኢያሪኮ የሚገኙትን ሳር ቅጠል ያሳያል። በጥንት ጊዜ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ የሚገኝ በግምብ የተከበበች፣ ከባህር በ፪፻፶፪ ሜትር ዝቅ ያለች ከተማ ነበረች። ዘንባባ እና የቡርትካን ዛፎች በደንብ የሚያድጉበት የእርሻ ቦታ ነበረች። በኋላውም የባህል የፈተና ተራራ ይታያል (ማቴ. ፬፥፩–፲፩)።

ታላቅ ድርጊቶች፥ በእዚህ ቦታ አካባቢ፣ ኢያሱ እና የእስራኤል ልጆች ወደ ቃል ኪዳን ምድር በመግባት የዮርዳኖስ ወንዝን ለመጀመሪያ ጊዜ ተሻገሩ (ኢያ. ፪፥፩–፫፫፥፲፬–፲፮)። ጌታ ግንቡ በእስራኤል ሰራዊት ፊት በተአምራት እንዲወድቅ አደረገ (ኢያ. ፮፤ ደግሞም ዕብ. ፲፩፥፴ ተመልከቱ)። ኢያሱ በከተማዋ ላይ እርግማን ጣለ (ኢያ. ፮፥፳፮)፣ ይህም ተፈጸመ (፩ ነገሥ. ፲፮፥፴፬)። ኤልሳዕ የኢያሪኮን ውሀ ፈወሰ (፪ ነገሥ. ፪፥፲፰–፳፪) አዳኝ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ፣ አይነ ስውር የሆነውን በርጤሜዎስን በመፈወስ እናም ከቀራጩ ዘኬዎስ ጋር በመቆየት፣ በዚህች ከተማ አለፈ (ማር. ፲፥፵፮–፶፪ሉቃ. ፲፰፥፴፭–፵፫፲፱፥፩–፲)። በመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ ውስጥ ከኢያሪኮ ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደው መንገድ ተጠቅሷል (ሉቃ. ፲፥፴–፴፯)። (ቅ.መ.መ. ኢያሪኮ ተመልከቱ።)