3. የይሁዳ ምድረበዳ
የይሁዳ ምድረበዳ ከሙት ባህር እየወረደ በኢየሩሳሌም በስተምስራቅ በኩል ይገኛል።
ታላቅ ድርጊቶች፥ የይሁዳ ምድረበዳ በመጀመሪያው ታሪክ ብዙ ዘመናት ውስጥ አስፈላጊ መሸሸጊያ ነበረ። ዳዊት ከንጉስ ሳዖል ተደበቀ (፩ ሳሙ. ፳፮፥፩–፫)። ኢየሱስ ለአርባ ቀን እና ለአርባ ሌሊት ጾመ (ማቴ. ፬፥፩–፲፩፤ ማር. ፩፥፲፪–፲፫)። ኢየሱስ በይሁዳ ምድረበዳ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ያለውን መንገድ የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ ለመስጠት ተጠቀመበት፣ ምክንያቱም በዚህ አካባቢ ብቻቸውን የሚጓዙ በቀላል በአደጋ ላይ ስለሚወድቁ ነበር (ሉቃ. ፲፥፳፭–፴፯)። (ቅ.መ.መ. የሙት ባህር ተመልከቱ።)