2. የሲና ተራራ (ኮሬብ) እና የሲና ምድረበዳ
ከእነዚህ ሁሉ የሚታወቁ ተራራዎች የሲና ተራራ ነው። አንዱ የባህል ቦታም፣ በዚህ ፎቶ የሚታየው ጀቤል ሙሳ (የሙሴ ተራራ) ነው።
ታላቅ ድርጊቶች፥ እግዚአብሔር በሙሴ ታየ እናም አስሩን ቃላት ሰጠው (ዘፀአ. ፲፱–፳)። ሙሴ፣ አሮን፣ ሁለቱ የአሮን ወንድ ልጆች፣ እና ፸ ሽማግሌዎች እግዚአብሔርን አዩ ግንኙነትም ነበራቸው (ዘፀአ. ፳፬፥፱–፲፪)። እግዚአብሔር ለሙሴ ታቦት የመገንቢያውን መመሪያ ሰጠው (ዘፀአ. ፳፭–፳፰፤ ፴–፴፩)። እስራኤላውያን አሮን እንዲሰራላቸው የገፋፉትን የወርቅ ጥጃ አመለኩ (ዘፀአ. ፴፪፥፩–፰)። ኤልያስ ንግስት ኤልዛቤል ከምትኖርበት ከኢይዝራኤል ሸለቆ ወደ እዚህ ምድር ሸሸ (፩ ነገሥ. ፲፱፥፩–፲፰)። ይህም ኤልያስ ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገረበት ቦታ ነው (፩ ነገሥ. ፲፱፥፰–፲፱)። (ቅ.መ.መ. የሲና ተራራ ተመልከቱ።)