27. ናዝሬት
ወደ ሰሜን ወደ ናዝሬት ከተማ የሚመለከት ትእይንት። ናዝሬት በመፅሐፍ ቅዱስ ዘመን ትንሽ መንደር ነው።
ታላቅ ድርጊቶች፥ ኔፊ በራዕይ የአዳኝን እናት በናዝሬት አያት (፩ ኔፊ ፲፩፥፲፫–፳፪)። መላእኩ ገብርኤል ማርያምን አዳኝን እንደምትወልድ ነገራት (ሉቃ. ፩፥፳፮–፴፭)። ገብርኤል ዮሴፍ ማርያምን እንዲያገባና ልጇን ኢየሱስ ብሎ ስም እንዲሰጠው ነገረው (ማቴ. ፩፥፲፰–፳፭)። ኢየሱስ በናዝሬት አደገ (ማቴ. ፪፥፲፱–፳፫፤ ሉቃ. ፪፥፬–፵፤ ፬፥፲፮)። በምኩራብ ውስጥ ሰበከ እናም መሲህ እንደሆነ አወጀ (ሉቃ. ፬፥፲፮–፳፩)፣ ነገር ግን የናዝሬት ሰዎች አስወገዱት (ማቴ. ፲፫፥፶፬–፶፰፤ ሉቃ. ፬፥፳፪–፴)። (ቅ.መ.መ. ናዝሬት ተመልከቱ።)