የጥናት እርዳታዎች
9. የሄሮድስ ቤተመቅደስ


9. የሄሮድስ ቤተመቅደስ

ፎቶ ፱

ይህ ፎቶ በ፷፯ ዓ.ም. ውስጥ ምን ይመስል እንደነበር የሚታሰብበትን የሄሮድስ ቤተመቅደስ ሞዴልን ያሳያል (፩፥፶ ቅርፊት ማመዛዘኛ)። የቤተመቅደሱ ግድግዳ የቅድስት ቅዱሳን የተቀደሰ ቦታ ያለውን ህንጻ፣ ቅዱስን ቦታን እና ሶስት ታላላቅ ቤተ መንግስቶችን የሚከብ ነበር።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ዮሴፍ እና ማርያም ህጻኑን ኢየሱስ ወደ ቤተመቅደስ ወሰዱ (ሉቃ. ፪፥፳፪–፴፰)። አዳኝ በ፲፪ አመቱ በቤተመቅደስ ውስጥ አስተማረ (ሉቃ. ፪፥፵፩–፵፮)። አዳኝ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተመቅደስ አስወጣ (ማቴ. ፳፩፥፲፪–፲፫) እና ስለቤተመቅደሱ መደምሰስ ተነበየ (ማቴ. ፳፬፥፩–፪)። በኢየሩሳሌም ወደፊት ቤተመቅደስ ይገነባል (ሕዝ. ፵–፵፰ዘካ. ፰፥፯–፱)። (ቅ.መ.መ. ቤተመቅደስ፣ የጌታ ቤት ተመልከቱ።)