12. ጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ
ይህ የአረጀ የወይራ ዛፍ ፎቶ የተነሳው በባህል የጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ነው ተብሎ በሚታመንበት ቦታ ነው። አዳኝ በተካደበት ቀን ከከፍተኛው ክፍል ወጥቶ በዚህ አጠገብ ጸለየ።
ታላቅ ድርጊቶች፥ በእዚህ ቦታ ክርስቶስ ለሰው ዘር ኃጢያቶች መሰቃየትን ጀመረ (ማቴ. ፳፮፥፴፮–፵፬፤ ማር. ፲፬፥፴፪–፵፩፤ ት. እና ቃ. ፲፱፥፲፮–፲፱)። ከጸሎቱ በኋላ በአስቆሮቱ ይሁዳ ተካደ፣ እናም በአትክልት ስፍራው ከተያዘ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ለጊዜም ካዱት (ማር. ፲፬፥፶)። (ቅ.መ.መ. ጌቴሴማኒ ተመልከቱ።)